Get Mystery Box with random crypto!

በስህተት ወደ ሌላ ሂሳብ የገባ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ለባለቤቱ ተመለሰ። ============= | CBE NOOR ሲቢኢ ኑር

በስህተት ወደ ሌላ ሂሳብ የገባ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ለባለቤቱ ተመለሰ።
===================

አቶ ሲሳይ ተስፋዬ በስልካቸው አንድ መልእክት ይደርሳቸዋል፡፡ በወቅቱ ሀሰተኛ መልእክት ስለመሰላቸው ብዙም ትኩረት አልሰጡትም፡፡ በጡረታ ላይ የሚገኙት አቶ ሲሳይ ዘመድም ወዳጅም ይህን ያደርጋል ብለው የሚጠብቁት ነገር ስላልሆነ በሂሳባቸው ብር 501,840.00 መግባቱን የሚናገረውን መልእክት ሀሰተኛ ነው ብለው አምነዋል፡፡

ከጥቂት ቀናት በኋላ ሂሳባቸውን በኤ.ቲ.ኤም ሲያዩ ግን እውነትም ብር 501,840.00 ወደ ሂሳባቸው ገብቷል፡፡ አቶ ሲሳይ በጡረታ ዘመኔ ያገኘሁት ሲሳይ ነው ብለው አልተደሰቱም፡፡ ይልቁንስ በስህተት የገባ ገንዘብ መሆኑ ስለገባቸው የገንዘቡን ባለቤት ማፈላለግ ጀመሩ እንጂ፡፡

ወደ ባንክ በመሄድ የሂሳብ ዝርዝር አስወጥተው ገንዘቡን ወደ ሂሳባቸው ያስገባውን ሰው ስም አገኙ፣ የውጭ ሀገር ዜጋ ነው፡፡ ስልኩን ከባንኩ ተቀብለው ደወሉለት፡፡ እውነትም በስህተት የገባ ገንዘብ መሆኑን አረጋገጡ፡፡ አስፈላጊውን ማጣራት አድርገው የገንዘቡ ትክክለኛ ባለቤት መሆኑን ሲያረጋግጡም ገንዘቡን በታማኝነት መለሱ፡፡

ገንዘቡ ህይወታቸውን ሊለውጥ ቢችልም ህሊናቸውን ግን ሊለውጥ እንደማይችል የተናገሩት አቶ ሲሳይ፣ ገንዘቡን ሲመልሱ የተሰማቸው ደስታ ወደር የለውም፡፡ የሰው ገንዘብ በፍፁም እንደማይፈልጉ እምነታቸው አድርገው የኖሩት አቶ ሲሳይ፣ አጋጣሚው የሚሉትን በተግባር ሆነው ያገኙበት ሆኖ ማለፉን ተናግረዋል፡፡

ገንዘቡ በስህተት ገቢ የተደረገበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን ቅርንጫፍም ለአቶ ሲሳይ ተስፋዬ ታማኝነት እና አራያነት ያለው ተግባር የምስጋና እና የአድናቆት ደብዳቤ ሰጥቷቸዋል፡፡