Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፶ @yanetmasra እ | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፶
@yanetmasra

እቤት ከገባሁ በሗላ ምናለ መሽቶ በነጋ ብዬ ተቁነጠነጥኩ ትንሽ ፍርሀት ፍርሀት ቢለኝም አንድ ችግር ስለቀለለልኝ ደስታም ተስምቶኛል ግን ደሞ የእውነት ትምህርት ላቋርጥ ነው ብዬ አሰብኩ ማመን ቢከብድም ፣ ቅር ቅር ቢለኝም አምኜ መቀበሌ ለኔ ግድ ነው። ስራውን እስካገኝ ድረስ ሀሳቤ ስራው ላይ እንጂ የትምህርት መንገዴ ቁርጥ ብሎ የሚቋረጥበት ቀን ነው ብዬ አላሰብኩም ነበር የዛን ቀን ግን አሰብኩት አይምሮዬን ማሳመን እንዳለብኝ ተሰማኝ ምክንያቱም ስራ መጀመሬ እንኳን ቢታወቅ እንዴት እኔ ሳላምንበት እነሱን አሳምናቸዋለሁ እነሱ በስራዬ እንዲያምኑ ትምህርት ማቋረጤን እንዲረዱ እና እንዲቀበሉ ማድረግ አለብኝ

  ከእቤት በጊዜ እየተጣደፍኩ ወጣሁ እንዳላረፈድኩ ተስፋ በማድረግ  ወደካፌው ስገባ ገና እየከፋፈቱ  ነበር ባለቤቱን እና ሁለት አስተናጋጆችን አገኘው ቀስ ብዬ በመጠጋት " አስታወሱኝ ጋሼ የትላንትናው ልጅ ነኝ " አልኳቸው ምን እንደምላቸው ጠፍቶኝ እንጂ መቼስ ይረሱኛል ማለት ዘበት ነው " አዎ እንደምነህ ጥሩ ሰአት ነው የመጣኸው መአዛ የምትሰራውን ታሳይሀለች " ብለው ከሁለቱ ሴቶች መካከል አጠር ያለችውን ጠርተው የምሰራውን እንድታሳየኝ ነገሯት ከዛም ወደኔ መጥታ " ሰላም መአዛ እባላለሁ " ብላ ንግግሯን ጀመረች እኔም " ሰላም ነኝ ዩሀንስ እባላለሁ " አልኳት " እሺ ዩሀንስ ጋሼ እንደነገሩህ ፅዳት ነው የምትሰራው ጠዋት ትመጣና ቤቱን ጠርገህ ትወለውላለህ ጠረጴዛውንም እንደዛው ከዛ ደንበኛ መቶ በሄደ ቁጥር ለሌላ ተስተናጋጅ ጠረጴዛውን አፅድተህ ወንበሩን ታሰናዳለህ ስራህ ይሄነው አሁን አብረን እንሂድና የማፅጃ እቃዎቹን ላሳይህ ፤ የመውጫ ሰአትህ ጋሼ እንዳሉኝ 11 ሰአት ነው " አለቺኝ የምትለኝን ሁሉ አዳምጬ እሺ በማለት ተከተልኳት



የእቃዎቹን ቦታ እያሳየችኝ ፅዳቱን ጀመርኩ የመጀመሪያ ቀኔ ስለሆነ አብራኝ በማፅዳት ተባበረቺኝ ደንበኛ ይመጣል ይሄዳል እኔም እንደተባልኩት የጠረጴዛውን ጨርቅ ይዤ ለመወልወል እሄዳለሁ የምሰራው ስራ ከበደኝ ማለት አልችልም እቤት ውስጥ ስራ መስራቴ የጠቀመኝ ይመስለኛል ቀኑን በመልካም አሳለፉኩ እንደተባልኩት 11 ሰአት ላይ ወጣሁ ፤ እየበረርኩ እቤት ሄጄ የሊስትሮ እቃዬን ይዤ መልሼ ደሞ በቀረችው ሰአት ጫማ ለመወልወል ወጣሁ አርፍጄባቸው ስለነበር አስቀድመው እህቶቼ እዛው ደርሰዋል ቀድማ ያየችኝ ፍቅር ስለነበረች " ዩሀንስ የት ሄደህ ነው እስካሁን ካለወትሮህ ስትቆይ እኮ አስጨነቅከን በሱፈቃድንም ስጠይቀው እንደውም ቀኑን ሙሉ  እንዳላየህ ነው የነገረኝ ፤ የሰሞኑ ሁኔታህ ግን ልክ ነው የሆነ ያስጨነቀህ ነገር ያለ እና ብቻህን እየተብሰለሰልክ ያለህ ይመስለኛል "አለቺኝ በሱፈቃድን እና ፍቅርተን መዋሸት እንደማይቻል ነው የገባኝ ነገሮችን ጥልቅ ብለው የማሰብ እና የማስተዋል ብቃት አላቸው  " አይ ምንም የለም ከትምህርት ቤት ወጥቼ ጓደኛዬ ጋር ሄጄ ነው የቆየሁት " አልኳት ጥያቄዋ ግን አያበቃም " የትኛው ጓደኛህ ከበሱፈቃድ ውጪ ሌላ ጓደኛ እንዳለህ እስከዛሬ አላውቅም ነበር " አለቺኝ " አንድ ክፍል ነን እና በቅርቡ ነው የተግባባነው ብቸኛ ስለሆነ ጓደኛ አድርጌው ነው ዛሬ ቤቴ ካልወሰድኩክ ሲለኝ እምቢ ማለት አልቻልኩም ለዛ ነው " ብዬ በፍጥነት ካካባቢዋ ልሰወር ስል " አይመስለኝም ባለፈው ቆሎ መሸጥ ስንጀምር ለጥቂት ቀን ብቻ ነው የሆነ መፍትሄ አመጣለሁ ብለኸኛል እንዲሁ ከመሬት ተነስተህ አይመስለኝም እባክህ ንገረኝ ውሸት ይብቃህ እውነት እንዳልሆነ ንግግርህ ከፊትህ ይነበባል  " አለቺኝ ከዛ በላይ ማስመሰሉ ሊሳካልኝ እንደማይችል ስለተረዳሁ " ደረቅ እኮ ነሽ እሺ በቃ እነግርሻለሁ ግን ሚስጥር ነው ለማንም እንደማትናገሪ ቃል ጊቢልኝ " አልኳት ፈጠን ብላ  " ቃል እገባለሁ " አለች " ስራ ስፈልግ ነበር ሰሞኑን ፤እና ትላንት አጊንቼ ዛሬ ጀምርያለሁ ለዛ ነው ያረፈድኩት አሁን የተሻለ ስለሚሆን የማገኘው እናንተ ትምህርታችሁን መማር ትችላላችሁ እኔ ቀን ካፌ ወደ አመሻሽ ደሞ ጫማ እየጠረግኩ በማመጣው ገቢ መኖር ትችላላችሁ አውቃለሁ ሙሉ ለሙሉ ችግራችንን ባይቀርፍም ከእጅ ወደ አፍ ለሆነ ኑሮ ግን  ይበቃል " አልኳት እንዳሰብኩት አልተደሰተችም " ምን ! ትምህርትህስ ! በፍፁም አታደርገውም " ብላ አምባረቀችብኝ ብላት ብሰራት አልሰማ ብላ ክችች አለች አስቀድማ ቃል ስለገባችልኝ ብቻ ለማንም እንዳትናገር ቃሏ አሰራት " ወይኔ ወንድሜ ለኛ ብለህ ህይወትህን መስዋት ልታደርግ ነው እንድንማር ብለህ ላትማር ነው በቃ " እያለች ተንሰቅስቃ አለቀሰች ላባብላት ሞከርኩ እየባሰ ቢመጣ ግን ሀዘኗ ሀዘኔን ሰርስሮ እምባዬን ሊያመጣው ሞከረ ብቻ እንደምንም ብዬ ገታሁት....ይቀጥላል
#share

ምዕራፍ ፩ በዚሁ አበቃ ምዕራፍ ሁለትን በቅርቡ ይዘንላችሁ የምንቀርብ ይሆናል ።


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur