Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፵፰ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፵፰
@yanetmasra

አንዳንድ ጊዜ የምትናገረው ነገር ወሽመጥ ነው የሚቆርጠው እኔማ ወሽመጤ ተቆርጦ ተቆርጦ ወሽመጥ አልባ ልሆን ምንም አልቀረኝም " ግን እኮ ከባድ ነው ብዙ ወንዶች ይተናኮሏቸዋል ካልሆነ ሌላ ስራ ፈልጌ እኔ እገባለሁ " አልኳት እሺ ትላለች ብዬ በማሰብ እሷ ግን " እስከዛ እራብ እንሙትልህ አንተ እንደሆንህ አይገድህ እዛው ትሰለቅጣለህ ይብላኝ እንጂ ለኛ " ብላ ወደ ጓዳ ገባች መናደዴ ሲበዛ ቤቱን ጥዬ ወጣሁ ሂዱም አትሂዱም አላልኳው ብቻ ከነገሮች ለመራቅ ይመስል የተጠቀምኩበት አማራጭ ብቻዬን ሆኜ እራሴን የማዳምጥበትን መንገድ መፈለግ ነው ። ከአንድ ዛፍ ስር ብዙ ሠዎች ለመረማመድ ወደማያዘወትሩበት ቦታ ሄጄ ቁጭ አልኩ አንዳንድ ጊዜ ድህነት ሽንፈት የሚመስልበት ሁኔታ አለ የምናሳልፈው ችግር ፈተና መሆኑን ስንዘነጋ ነው እንደሱ የምናስበው እኔም ታድያ ይሄኔ ብር ቢኖረኝ እንደዚህ አልሆንም ብዬ ቁጭት ተሠማኝ ትምህርት የማቋረጥን ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ  በልቤ የፀነስኩት ያን ለት ነበር ለማንም ግን ልናገር አልወደድኩም ምክንያቱም ለትምህርት ያለኝን ቦታ እና ውጤቴን ስለሚያውቁ የእብድ ሀሳብ ነው ብለው ነው የሚያስቡት ። ትምሀርት ለመውደዴ ምክንያት የምትሆነው እናቴ ናት " ሠው ከተማረ ትልቅ ቦታ ይደርሳል  " ብላ የማሰቧ ነገር እሷ መማር ባትችልም ልጆቿን ግን እንድታስተምር አድርጓታል ማቋረጤ ያስከፋታል ብዬ ሳላስብ ቀርቼ ሳይሆን ሰርቼ መገኘቴ በዛን ሰአት ለቤተሰቦቼ በተለይም ለእህቶቼ ምንያህል ጠቃሚ እንደሆነ በማሰብ ነው ። ቢያንስ አይምሮአቸውን ሰብስበው መማር ይችላሉ ። በወቅቱ የነበረው ማህበረሰብ የተማረ የሚባል አይደለም በቀለም ትምህርት ሲመዘን ፤ እንዲሁም የትምህርት ጥቅም ያልገባው ይበዛል እንደውም 12ኛ የደረሰ እንደኛ አይነት ተማሪ ሁሉ የሚሰጠው አመለካከት ልዩ ነው ልክ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ጭላንጭል ብርሀን ሲታይ አድርገው ነው የሚቆጥሩት



ሁለተኛ ላስብ የቻልኩት አንድ ነገር ቢኖር ለጊዜው መስራታቸው ካልቀረ ሌላ የተሻለ እና ደና ስራ እስካገኝ  ድረስ እኔ ጫማ የምጠርግበት አካባቢ መሸጥ እንደሚችሉ እና በአይኔ ልከታተላቸው እና ባስካለ ነገር ልጠብቃቸው እንደምችል ተገነዘብኩ ይሄን ማሰቤ ትንሽ እረፍት ሰጠኝ ለካ ነገሮችን በችኮላ እና በቶሎ ከመወሰን በተረጋጋ ስሜት እራስን ማዳመጥ ለመፍትሄ እንደሚያደርስ ተረዳሁ ዋናው ነገር ደሞ " ሠው ያስብ እግዚአብሔር ይፈፅም "  እንደሚባለው ሀሳቤ እንዲፈፀም የእግዚአብሔር ጥላ እና ከበባ በኔ እና በቤተሰቤ ላይ እንዲሆን ፀለይኩ ።

  በንጋታው እህቶቼን ሳገኛቸው እንደ ትላንቱ ልቆጣቸው መስሏቸው ከፊታቸው ላይ የመሸማቀቅ ስሜት ተመለከትኩባቸው ነገር ግን ቀለል አድርጌ " ከዚህ በሗላ ለተወሰነ ጊዜያት አብረን በመሆን እኔም ጫማ እጠርጋለሁ እናንተም ቆሎ ትሸጣላችሁ ስለዚህ ስንሄድም አብረን ስንመጣም አብረን ነው የሚሆነው እኔ ካለሁበት አካባቢ ትሸጣላችሁ " አልኳቸው ፍቅርተ ከአፌ ቅብል አድርጋ " ማለት ትላንት ከልክለኸን አልነበር አሁን ፍቃደኛ መሆንህን እየገለፅክልን ነው እንዴ " አለቺኝ በጥርጣሬ መንፈስ እየገረመመቺኝ " አዎ አልቀለድኩም በዚሁ ውጥረት ውስጥ እያለን ለመቀለድ የሚያስችል አቅም የለኝም አማራጭ የሌለው ምርጫ ባይሆንብኝ ኖር ይሄን አልወስንም ነበር ክፉ ቀን እስኪያልፍ መተጋገዛችን ግድ ነው ግን አታስቡ ለጥቂት ቀን ብቻ ነው እግዚአብሔር እረድቶኝ የሆነ መፍትሄ አመጣለሁ " አልኳቸው ያልኩት ነገር ቢዋጥላቸውም ባይዋጥላቸውም ዝም ብለው እኔ ባልኩት ነገር ለመስማማት ሞከሩ ከዛ ከዛኑ ቀን ጀምሮ አብረን እኔ ከምሰራበት አካባቢ ሄድን የዛን ቀን የመጀመሪያ ቀናችን ስለሆነ ነው መሠለኝ ትኩረቴን ሰብስቤ ስራዬን መስራት አልቻልኩም አይኖቼ ወደዚህ ወደዛ እያሉ ቆሏቸውን ይዘው ወደላይ ወደታች ከሚንከራተቱት እህቶቼ ላይ ተተከለ....ይቀጥላል
#share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur