Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረ ክፍል ፳፭ @yanetmasra የ | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረ
ክፍል ፳፭
@yanetmasra

የዛን ሰአት የተናገሩኝ ንግግር ውስጤን ስርስር አድርጎ ገባ ልክ ነበሩ እንድልና የእናቴ ዋጋ እንዲገባኝ አደረጉኝ በፊት ለኔ የነበራትን አመለካከት እና ቀረቤታ አሁን ካላት ጋር አነፃፀርኩት የተገላቢጦሽ ሆነብኝ በፊት ለኔ መልካም እና እሩሩ ነበረች አሁን ግን በተቃራኒው እናት ሳትሆን የእንጀራ እናት ነው የሆነችብኝ ውስጤ ቢከፋባትም ልረዳት ሞከርኩ እሷ ግን እኔን እንደማትረዳኝ ግልፅ ነው እናቴ ግን ጌታን አምና የዳነች ቀን ደስታዬ የሚሆነው ወሰን አልባ ነው እኔ በመዳኔ ከተደሰትኩት በላይ እጥፍ ድርብ አድርጌ ነው የምደሰተው " እውነት ለመናገር እርሷ ያሰቡትን ያህል ጥቂትም ቢሆን አስቤ አላውቅም ነበር ። እንደውም እናቴ ሆና ይሄን ያህል ለምን ጨከነችብኝ ብትናደድብኝ እንኳን እንደዚህ መጨከኑ ለምን አስፈለገ ብዬ ከማሰቤ የተነሳ ቀን በቀን በተተካ ቁጥር ልቤ ውስጥ ቂም መቋጠሬ አልቀረም አሁን ግን የተጋረጠውን አይነ ልቦናዬን ገልጠውልኛል እሷም ብትሆን ያመነችውን እንዳምንና ያድነኛል የምትለው እንዲያድነኝ ካላት ፍላጎት የተነሳ ነው እውነት ስለመልካም ሀሳቦ እና ስለምክሮ አመሠግናለሁ " አልኳቸው "አይ አንተ! ይሄ ምስጋና የሚያስፈልገው ነገር አደለም ደሞ ማሰብ ያለብህ ከቤተሰብ በላይ አብዛኛው  ማህበረሰብ በእምነትህ ምክንያት እንደሚጠላህ በማወቅ አንተ ግን እነሱን መውደድ ነው ። እናትህ እኮ ግፋ ቢል ብትጮህብህ ከዛ ከዘለለም እንደ ልጅ ብትገርፍህ ነው ። ውጪ ላይ ያሉ አብዛኞቹ ህብረተሰቦች ደሞ ቢገሉህም ደስተኛ ናቸው ። ስንት መከራ በአማኙ ማህበረሰብ ላይ እንደሚያደርሱባቸው ላንተ አልነግርህም ምክንያቱም የአደባባይ ሚስጥር ስለሆነ ነው ታድያ የሚጠሏችሁን  ውደዱ ስለተባለ የሚጠሉህን ለመውደድ ዝግጅ ነህ እየደበደቡህ ትወዳቸዋለህ ? ቢሰድቡህና ሊገሉህ ቢሞክሩስ ትወዳቸዋለህ ? ይሄን ራስህን ጠይቀው መልስህ አዎን ከሆነ እውነትም አንተ



ወንጌል ገብቶሀል ክርስቶስን መስለህ ትኖራለህ ከዛ ግን ራስህ ላይ መስራት አለብህ ወንጌል ሊለውጥህ ይገባል ገና ከዚ የባሰ መከራ ከፊትህ ይጠብቅሀል ለዛ ደሞ ጠንካራ ሆነህ ማለፍ አለብህ በዚ መልኩ ለሞተልህ ፣ ዋጋ ለከፈለልህ ታማኝ ሆነህ ትገኛለህ " አሉኝ መልሶም ትካዜ ገባኝ የጠየቁኝን ጥያቄ እራሴን ጠየቅኩት እውነት እወዳቸዋለሁ ወይስ ጠላቶቼ ብዬ እጠላቸዋለሁ ? ሀጥያተኛ ሆኜ ሳለሁ ተወድጄ ተመርጬ ከዳንኩ በሗላ ሀጥያተኛ ብዬ ያልዳኑትን እጠላለሁ ወይስ የመስቀሉ ስራ የእውነት ገብቶኝ የሚጠሉኝን አብዝቼ እወዳለሁ ? መልሴ እኔንጃ አላውቅም ቢሆንም መሆን ያለበት ስለገባኝ እንደዛ አይነት ሰው ለመሆን እራሴ ላይ መስራት እንዳለብኝ ተረዳሁ " ዝግጅ መሆኔን ባላውቅም ዝግጁ ለመሆን እጥራለሁ " አልኳቸው "እንድትጨነቅ ብዬ ሳይሆን እንደዚህ ያልኩህ ነገሮችን በብዙ መልኩ እንድታይና እነሱንም በመልካም እንድትመለከት ካለኝ ፍላጎት የተነሳ ነው " ብለው ተነሱ እኔም መልሼ " አሁንም ሊወጡ ነው እነሱን ፍለጋ ? "አልኳቸው " አይ አይደለም በባዶ ሆድህ በወሬ ይዤህ እንደራበህ እርግጠኛ ነኝ የሚበላ ነገር ላዘጋጅልህ ነው " አሉኝ ከዛ ወደ ጓዳ ገቡ እኔም ተመልሼ ጋደም እንዳልኩ የለበስኩትን ልብስ ተጠቅልዬ አይኔን ለእንቅልፍ ጋበዝኩት ከምኔው እኔደሆነ ባላወቅኩበት ድብን ያለ እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ የነቃሁት በሱፈቃድ እና አባት እቤት መጥተው ደህንነቴን ለማወቅ ከተኛሁበት ሲቀሰቅሱኝ ነው ....ይቀጥላል


ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur