Get Mystery Box with random crypto!

#ፈጣኑ_ለውጥ ' ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታን። ጌታ ሆይ፥ ካለኝ ሁሉ #እኵሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ፤ | የክርስቶስ ደቀመዝሙር ✞

#ፈጣኑ_ለውጥ

" ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታን። ጌታ ሆይ፥ ካለኝ ሁሉ #እኵሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ፤ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደ ሆንሁ #አራት_እጥፍ እመልሳለሁ አለው።" (የሉቃስ ወንጌል 19:8)

"8 And Zacchaeus stood, and said unto the Lord; Behold, Lord, the half of my goods I give to the poor; and if I have taken any thing from any man by false accusation, I restore [him] fourfold."
(Luke 19:8)

***
መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ስፍራ ዘኬዎስ ስለተባለ የቀራጮች አለቃ ታሪክ ይናገራል፡፡

ዘኬዎስ ጌታን ለማየት እጅግ ከፍተኛ ጉጉት የነበረው ሰው ሲኾን ጌታን እንዳያይ የሚከልሉትን ነገሮች ኹሉ አልፎ በዛፍ ላይ በመውጣት ጌታን በጉጉት ተመልክቷል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስም ፈጣን የሕይወት ለውጥ ካሳዩ ሰዎች መካከልና ኢየሱስን ባገኘ ቀን ሕይወቱና ድርጊቱ የተለወጠ ሰውነው፡፡

የለውጡ ምንጭ ኢየሱስን ለማግኘት የነበረው ጉጉትና ከኢየሱስ የተካፈለው ፍቅር ነበር፡፡ ዛሬም ብዙ ሰው "ክርስቲያን" ነኝ ቢልም የተለወጡ ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡ የዘኬዎስ ታሪክ ብዙ የሚያስተምረን ይመስለኛል፡፡
የእኛ ጉጉት
የተካፈልነው ፍቅር

@Christdisciples