Get Mystery Box with random crypto!

-Leaving Egypt Behind ' የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ፤ | የክርስቶስ ደቀመዝሙር ✞

-Leaving Egypt Behind

" የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ፤ ማኅበሩም ሁሉ። በግብፅ ምድር ሳለን ምነው በሞትን ኖሮ! ወይም በዚህ ምድረ በዳ ምነው በሞትን ኖሮ! "
(ኦሪት ዘኍልቍ 14:2)

"2 And all the children of Israel murmured against Moses and against Aaron: and the whole congregation said unto them, Would God that we had died in the land of Egypt! or would God we had died in this wilderness!"
(Numbers 14:2)

**

በዚህ ስፍራ እስራኤላዊያን እግዚአብሔር ወዳዘጋጀላችው የተስፋይቱ ምድር ሲጓዙ የገጠማቸውን ነገሮች እንመለከታለን፡፡ ሕዝቡ በ ምዕራፍ 13 ላይ በሰሙት አሉታዊ ሪፖርት ምክኒያት ፈርተው፣ ተሸብረው ለነፍሳቸው ሰግተው ከተስፋይቱ ምድር ይልቅ ወደኀላ የባርነት ዘመን መመለስን ናፍቀዋል፡፡

እኛም በሕይወታችን ከዙሪያችን ካሉ ሰዎች በምንሰማቸው መጥፎ ነገሮችና ከሚገጥሙን ችግሮች የተነሳ እግዚአብሔር ካዘጋጀልን የተስፋ ምድርና ቃል ብዙ ጊዜ እምነት በማጣትና ስጋዊ በኾነ ሀሳብ በመታሰር ወደፊት ከመገስገስ ወደኀላ መመለስን እንሻለን፡፡ ሰይጣንም እግዚአብሔር ወዳዘጋጀልን ከፍታ እንዳንደርስ በዙሪያችን ብዙ አሉታዊ ሰዎችን ያሰማራል፡፡

ወደ ሀገራችንም ስንመለከትና ቆም ብለን ስናስብ የሀገራችን የሕዝብ ኹኔታ እንዲህ የኾነ ይመሰልላል፡፡ ብዙ ሰው በፍርሀትና ተስፋ በመቁረጥ የቀደመውን ነገር ይናፍቃል፡፡

****

አላማኞች ኹልጊዜ በበረሀ ይቀራሉ አልያም ወደኀላ ተመልሰው ዳግም በግዞት ይኖራሉ፡፡
እኛ ግን ማወቅ ያለብን ነገር የሚመጣውና ተስፋ የተገባልን ምድር ከቀደመው እጅግ የሚልቅና አሁን የምናልፍበትን አባጣ ጎርባጣ መንገድ የሚያስረሳ ነው፡፡ ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ቃል የተገባልንን የተስፋ ምድር በእምነት ለመውረስ እንትጋ፡፡
***
ዘወትር የእግዚአብሔርን ተስፋ ቃል በማመን በመንፈስ መመላለስና ወደተገባልን የተስፋ ምድር በእምነት መገስገስ ይኹንልን