Get Mystery Box with random crypto!

ከራስ ጋር ትግል ተከታታይ ልብወለድ ምዕራፍ=ሁለት ክፍል=53 | CHRIST TUBE - ETH🇪🇹

ከራስ ጋር ትግል
ተከታታይ ልብወለድ
ምዕራፍ=ሁለት
ክፍል=53
ሳባ ካሳሁን

ከወዲያ ወዲህ እጄን ሳወራጭ ሊዱዬ ቢኒና ናሆሜ የሉም በጣም ደነገጥኩ ሁኔታውን መቀበል እስኪያቅተኝ ሰውነቴ ከዳኝ ፍርሀት ውስጤን ረብሾት ማሰብ እስኪከብደኝ ተርበተበትኩ "ከኋላዬ የያዘኝ ሰው ምን አስቦ ነው? እነ ሊያ የት ናቸው? ምናልባት የቅድሞቹ ሰዎች ይሆኑ? አሁን ምን ልናደርግ ነው?" እያልኩ የጭንቀትና የድንጋጤ ዕምባዬን ማውረድ ጀመርኩ አፌንና እጄን ከያዘኝ በኋላ የትንፋሽ እንኳን ምንም አይነት ድምፅ በቤት ውስጥ አልነበረም። ሰከንዶች እየተዟዟሩ ደቂቃን በሰጡን ቁጥር ልቤም ፍርሀቱ እየጨመረበት አካሌ ከንቱ ሆኖ እየከበደኝ የታፈነ አፌ ለማውራት መታገሉ እየደከመው ሲመጣ ተስፋ ቆርጬ ሳለ ናሆም ከየት መጣ ሳልለው በለቅሶና በሲቃ ድምፁን ስስ አድርጎ "ሜሪ!! ሜሪ!! ቢኒዬ!! የት ናችሁ? ሜሪ!" እያለ መጣራት ጀመረ በዚህ ሰዐት ድምፁን ስሰማው በደስታ ጭላንጭል ተስፋ ብቅ አለልኝ በልቤ "እንዴ!! ናሆሜ!! ናሆሜ አለ ብቻዬን አይደለሁም!" ብዬ ድምፄን እንዲሰማውና መኖሬን እንዲያውቅ ያለ የሌለኝን አቅሜን እያወጣሁ የያዘኝን ጠንካራና ልረታው ያልቻልኩትን ግዙፍ ሰው በእግሮቼ እየተወራጨሁ "እም!! እም! እም!" እያልኩ መኖሬን አሳወኩት ነገር ግን ናሆሜ ፍፁም መልስ ሊሰጠኝ ካለሁበትም ዳስሶ ሊመጣ አልቻለም ይባስ ከፋኝ ማውራቴ ነፃነቴ ሳቄ ናፈቀኝ "ለምን ያዙን?? ለምን ተዘጋብን? ለምን ያሰቃዩናል?" እያልኩ ይበልጥ ማልቀሴን ቀጠልኩ ማውራት ብቻ ሳይሆን የሚያወራ ሰው አጓጓኝ "ምናለ ከኛ ምን እንደሚፈልጉ ቢነግሩን?" እያልኩ ዝምታን ጠላሁት በተደጋጋሚ የተዘጋው በር ሲከፈት ሰማለሁ የሚወጡና የሚገቡ ሰዎች ኮቴያቸው ያስታውቃል ሁኔታው እውነት እስከማይመስል ልጅ እያለን አስፈሪ ፊልም አይተን እንደሚያቃዠን ልክ እንደዛ የሚመስል አይነት ነበር።

በዚያ ክፍል ውስጥ እርግጠኛ የሆንኩበት ነገር እኔ በሰውየው መያዜን ብቻ ነው "ሊዱዬ የት ነች? ቢኒ የት ነው? ናሆሜ የት ገባ?" ላውቅ ብታገልም አልቻልኩም ከብዙ ዝምታ በኋላ አንድ ነገር ተፈጠረ ይኸውም የእልህ እልሁን ድርቅ ብሎ እጄን ወደኋላ ጎትቶ የያዘኝና አፌን በእጆቹ ለጉሞ ትንፋሼን ያመቀው ሰው ድንገት ወደ በሩ ወሰደኝ ልክ ስንደርስም በሩን በቀስታ ከፍቶ በፍጥነት ወጣ ከሁሉ በፊት ድንጋጤዬ ስላለቀቀኝ ለደቂቃዎች አፍኖት በነበረው አፌ ለጉድ እያለከለኩ ብርሀን አሳይቶኝ ድጋሚ የነሳኝን የተዘጋውን በር እየደበደብኩ በእምባ ስቃይ ተሞልቼ "እርዱኝ!! እርዱኝ!! ሰው የለም?!! እባካችሁ ጓደኞቼን አገናኙኝ እባካችሁ!" እያልኩ በበሩ ላይ ድፍት ብዬ ቀረሁ ይህን ጊዜ ከቤቱ ጥግ ጋር አንድ ልክ እንደኔ አፉ የተለጎመ ማውራት እየፈለገ በእምባ የተሞላ የእኔን እርዳታ ወይ ለኔ መከታ ሊሆን የሚፈልግ አንድ ሰው ድምፁን አሰማኝ እኔም በጣም ደንግጬ በመሬቱ ላይ እየተንፏቀቅኩ ሄጄ ከአጠገቡ ደረስኩ በቤቱ ጭራሽም ብርሀን ስላልነበር ፍፁም መለየትና ማወቅ ከበደኝ እሱ ግን የታፈነ ድምፁን ማሰማቱን አላቆመም ወደሱ እየቀረብኩ "ማነህ? ማነህ? እጄን ያዘኝ" እያልኩ እጄን ስዘረጋለት ያዝ አደረገኝና አፉ ላይ እንዳያወራ የታሸገውን ትልቅ ላስቲክ አስነካኝ አሁንም መርበትበቴን ላቆም አልቻልኩም "እሺ! እሺ አስረውህ ነው? ቆይ! ቆይ አንዴ" ብዬ እየተንቀጠቀጥኩ ላስቲኩን በዳበሳ አነሳሁለት ልክ እሱም እንደኔ በሀይል እየተነፈሰ "ሜሪዬ!!" አለኝ ይህን ጊዜ ከልቤ ተደሰትኩ ከአራታችን አንዱ መከታችንን ቢኒን አገኘሁት በደስታ ተሞልቼ "ቢኒዬ አለህ? አንተ ነህ?" እያልኩ አቀፍኩት እሱም ደስ ብሎት እምባውን እየጠራረገ "አለሁ አለሁ" አለኝ በመሀል ግን አንድ ሌላ የእርዱኝ ወይ አለሁኝ የማያ ሳይሆን የድካምና የህመም የሚመስል ድምፅ የቱ ጋር እንደው በማናውቅበት ቦታ ሰማን አሁንም በድንጋጤ ሁለታችንም በመሬቱ ላይ ተንበርክከን እየተንፏቀቅን ድምፁን ላሰማን ሰው ልንደርስለት በተለያየ አቅጣጫ መፈለግ ጀመርን ብዙም ሳይቆይ ቢኒ በጣም ጮክ ብሎ "ሜሪ ሜሪ ይኸው እዚህ ጋር አገኘሁት ናሆሜ ነው! ሜሪ ናሆሜ ነው!! ናሆሜ ናሆም ናሁዬ" እያለ ጠራው ድምፁ ወደሚሰማኝ እየሮጥኩ ሄጄ ስጠጋቸው ናሆሜም ልክ እንደኛ አፉ ተሸፍኖ የትግል ድምፅ ማውጣቱ ልቡን አድክሞት ተስፋ ቆርጦ ወድቋል እግራችን ላይ ጭንቅላቱን ዘመም አድርገን ደጋግመን ስንጠራው የእኛን መምጣትና የአፉን መፈታት ያላመነው ጓደኛችን ቀና ብሎ "መጣችሁልኝ? ጓደኞቼ!!" ብሎ በግራና በቀኝ እቅፍ አደረገን ወዲያው ግን ፀጉሬን መደባበስ ጀመረ ከጠዋት ጀምሮ በገጠሙን ነገሮች ግን ልስት የነበረው ራሴን መቆጣጠር ስላቃተኝ ሁኔታውን አላስተዋልኩም ናሆሜ በቅፅበት ተስፈንጥሮ ተነስቶ "እንዴ! እንዴ ሊዱስ! የታለች?" አለን ይህን ቃሉን ስሰማ ሰማይ ከምድር ተደባልቆ ነውጥ የተነሳ ያህል ልክ እንደዛ ጭንቅላቴም ሊፈነዳ ያህል ተሰማኝ በጭለማ ውስጥ ለኛ ብርሀንን የምትሰጠን ቡቻዬን የት ረሳናት? ማሰብና ማስተዋል ተሳነኝ. ራሷን ስታ ይሆን? ድንገት ተነስቶ ምጥ የሚሆንባት የልቧ ህመም አገኛት ይሆን? ብዬ እግሮቼ መሄድ እስኪያቅታቸው ተሳስረውብኝ በእንብርክክ አልቆም ባለው እምባዬ እየተንሰቀሰኩ እንደእብድ ወለሉን ስዳብስ ናሆምና ቢኒ እየተዘዋወሩ ስሟን ደጋግመው እየጠሩ በጭለማው ዕርስ በዕርሳቸው እየተጋጩ ሲፈልጓት ግን ሊዱ ዬን ፍፁም ልናገኛት አልቻልም በቤቱ ውስጥ እንደሌለች ካወቅንም በኋላ ቢኒ "ሊዱ ዬ ቀልድ ነው በይኝ አለሁላችሁ በይን!" እያለ በለቅሶ ቢለምናትም "አቤት ወዬ መጣሁላችሁ" አላለችንም አሁን ይበልጥ ነገሩ ተወሳሰበብኝ የጠዋቱን ነገር አሁን ካለንበት ነገር ጋር ሳገጣጥመው በፍርሀት ተወረርኩ ልክ እንደ አንድ "በቃ ለየለት" እንደሚባል ሰው በቤቱ ጠርዝ ጋር ሽጉጥ ብዬ ዐይኔን ግድግዳ ላይ እንደተከልኩ ደርቄ ቀረሁ ናሆምና ቢኒ ግን በሀይልና በጩኸት "ሊዱን ልቀቋት!! ወንድነት ካላችሁ ኑ እኛን ውሰዱን!! አንድ ነገር ብትሆን ከፀጉሯ አንዲት ዘለላ ብትነካ አንለቃችሁም!!" እያሉ በተደጋጋሚ ሳይሰለቹ በሩን እየደበደቡ ተናገሯቸው።
ነገሩን እንዲህ ጀመሩልን የነቢኒን ማቆሚያ የሌለው ጩኸት የታከታቸውና እልህ ውስጥ ያስገባቸው ይመስሉ ነበር የእኔ ዝምታ ሲያስጨንቃቸው እነ ናሆሜ ቀረብ ብለውኝ ሊያበረቱኝ እየሞከሩ ሳለ ለሰዐት የተዘጋብን በር ተበረገደ ሆን ተብሎ ይመስል ብርሀኑ እጅጉን ሀያል ነበር ሁላችንም ዘለን ተነስተን ወደ ውጪ ለማየት ስንሞክር ስንመጣ አግኝተናቸው የነበሩት እነዚያ ትላልቅ ልጆች መሀላቸው ሌላ አንድ ሰው አድርገው ወደኛ መጡ ልቤ በጣም እየፈራ ምቱ እየጨመረ የናሆሜን ኮት አጥብቄ ያዝኩትና በጉጉት እጠብቅ ጀመር ልጆቹ ወደኛ እየተቃረቡ አጠገባችን ሊደርሱ ትንሽ ሲቀራቸው ፍፁም ያልጠበቅነው ጭራሽም ያላሰብነው ነገር አየን መሀላቸው ያለችው ሰው ሊያ ነበረች. . .
. . .ይቀጥላል. . .
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
ቻናሉን ይቀላቀሉ
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRIST_TUBE
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!