ዝም ያለ ሲመስለን እግዚአብሄር ረስቶ ዝም ያለ ሲመስለን: እኛን ወዲያ ብሎ ጭራሹን የጣለን: ሀጥያተኛ ደልቶት ሞልቶት እየኖረ: ባልጣረው ባለፋው ሁሌ እየከበረ: ፃድቅ ሰው ሲያቅተው የሀጥያን ዱላ: በዙሪያው ሲያጣ ሚሆነው ከለላ: አምላኬ ሆይ! አረ ከወዴት ነህ ምንስ እያየህ ነው: በፅድቄ ስጨቆን አይተ ዝም ያልከው: እያለ ሲያቃስት ሲጮህ ወደ አምላኩ: እርሱ ሁሉን ያውቃል ሀጥያተኛም ቢሆን አያልፍም አልኩ: እሱ የተሳሳተ ዝም ያለ ቢመስልም: በፍርዱ ልክ ነው ከቶ አይሳሳትም: የደላቸው መስለው ለጊዜው ቢፋፉ: በዛው ላይቀጥሉ ሊሄዱ ሊጠፉ: የሚሆን መስሏቸው በከንቱ ቢለፉ! ፃድቅ ሰው ሲራብ ዘሩ እህል ሲለምን: በድሜዬ አላየሁም ውድቀቱ ሲፈጥን: ይልቅ ይህን ልበል እግዚአብሄር ይፈርዳል: የፃድቃንን ጩሀት ሰምቶ ይመልሳል! ነፃነት ዋቲሮ(@Netsiychrist) SHARE | @CHRIST_TUBE SHARE | @CHRISTFAMILY 1.7K viewsNetsi, edited 17:04