Get Mystery Box with random crypto!

የፀጋ ዓላማ #ብቁ_አድርጎ_ማቆም °°°ፀጋ ማለት የማይገባ ሞገስ ማለት ሲሆን ከሰማይ እስከ ም | 🗣ወንጌል ለአለም ሁሉ🗣

የፀጋ ዓላማ

#ብቁ_አድርጎ_ማቆም

°°°ፀጋ ማለት የማይገባ ሞገስ ማለት ሲሆን ከሰማይ እስከ ምድር ማለትም በመለኮት ዓለም ቢሆን በፍጥረት ዓለም ውስጥ የበቃችሁ አድርጎ የሚያቆማችሁ የእግዚአብሔር ጥበብ ነው።

°°°ፀጋ እናንተ እናንተ የምታስቆጥሩት አይደለም።እናንተ በአመናችሁ ጊዜ ሙሉ እንደሆናችሁና እከን የሌሽ አድርጎ የሚያስቆጥራችሁ የእግዚአብሔር አሠራር ነው።


“መጽሐፍስ ምን አለ? አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።”ሮሜ 4፥3


ሮሜ 4
²³ ነገር ግን፦ ተቈጠረለት የሚለው ቃል ስለ እርሱ ብቻ የተጻፈ አይደለም፥ ስለ እኛም ነው እንጂ፤
²⁴-²⁵ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቈጠርልን ዘንድ አለው።

#ብቃትን_መስጠት_ነው

የእግዚአብሔር ፀጋ ዓላማ ብቁ አድርጎ ማቆም ብቻ አይደለም።ለተፈለጋችሁበት መለኮታዊ ፕሮግራም ብቃትን ይሰጣችኋል።

°°°ብቁ አድርጎ ማቆም ማለት የሚፈለግባችሁን ማንነት ማላበስ ማለት ሲሆን ብቃትን መስጠት ማለት የእግዚአብሔርን ችሎታ መለገስ ወይም ከተፈጥሮ በላይ የሆነው ዓለም በእናንተ እንዲሰራ ማድረግ ማለት ነው።

“በተነ፥ ለምስኪኖች ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።” 2ኛ ቆሮ 9፥8-9

°°°ፀጋው ወደ ህይወታችሁ ሲመጣ ድርጊታችሁ በሙሉ ከእናንተ አቅምና ችሎታ የሚወጣ አይሆንም።ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ ላይ የፀጋውን ጉልበት ማሳየት ይፈልጋል ከሁሉ ይልቅ ደክሜያለሁ ይልና ዳሩ ግን እኔ ሳልሆን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ፀጋ ነው እንጂ ይላል።

“ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም ከሁላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ፥ ዳሩ ግን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።"1ኛ ቆሮንቶስ 15፥10


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───

SHARE SHARE SHARE
   JOIN US

@christ_mossion
@christ_mossion
@christ_mossion