Get Mystery Box with random crypto!

ምን ያማል አትይም ከጦሩ ጫፍ ይልቅ በልብ ከተሰካው ቆዳ ዘልቆ ገብቶ ሆድ ከተረተረው ከህመሙ በላ | ጨረቅረቃ

ምን ያማል አትይም
ከጦሩ ጫፍ ይልቅ በልብ ከተሰካው
ቆዳ ዘልቆ ገብቶ ሆድ ከተረተረው
ከህመሙ በላይ
አስታማሚው ያማል ደርሶ አዳኝ ነኝ ባይ
እሱ ነው የሚያመው ከወጊ አስታማሚ
ከጦሩ ሚታገል አላዋቂ አካሚ
ህመም የሚያባብስ ደርሶ እያላወሰ
እሱ ነው 'ሚያቆስል ከስለቱ የባሰ
#እሙ_ሠላም