Get Mystery Box with random crypto!

#SamaraUniversity በ2014 ዓ.ም ወደ ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀ | Campus Students

#SamaraUniversity

በ2014 ዓ.ም ወደ ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ግንቦት 13 እና 14/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ምዝገባ የሚከናወነው ከግንቦት 15 እስከ 17/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

• የ8ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው
• የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው
• ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
• 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ (8)
• ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርሲቲውን ድረ-ገጽ፦ www.su.edu.et መጎብኘት ትችላላችሁ፡፡

@campus_group_ethiopia
@campus_group_ethiopia