Get Mystery Box with random crypto!

#SPHMMC በ2014 ዓ.ም የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የሕክምና ትምህርት | Campus Students

#SPHMMC

በ2014 ዓ.ም የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የሕክምና ትምህርት ለመማር የተመረጣችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ግንቦት 15 እስከ 17/2014 ዓ.ም ሪፖርት እንድታደርጉ ተብሏል።

ወደ ኮሌጁ በምትሄዱበት ጊዜ፦

የ1ዐኛ እና 12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሰርተፊኬት ዋና እና ኮፒ

ከ9-12 ክፍል የተማራችሁበትን ትራንስክሪፕት ዋና እና ኮፒ

8 ፓስፖርት ሳይዝ ፎቶግራፍ

አንሶላ፣ ብርድልብስ እና የትራስ ልብስ

የስፖርት ልብስና ጫማ ይዛችሁ እንድትሄዱ።

ከላይ ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጡ ተማሪዎችን ኮሌጁ የማናስተናግድ መሆኑን አስታውቋል።

ለተጨማሪ መረጀ 0118965125 / 976 መጠየቅ ይቻላል፡፡

ምንጭ፦ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ሬጅስትራርና አልሙናይ ማናጅመንት ዳሬክቶሬት

@campus_group_ethiopia
@campus_group_ethiopia