Get Mystery Box with random crypto!

በአሜሪካ በኮነቲከት ግዛትም የታገዘ ራስን ማጥፋት ሕጋዊ ለማድረግ የተዘጋጀው ረቂቅ ህግ ድጋሚ ው | CALVARY gospel ministry

በአሜሪካ በኮነቲከት ግዛትም የታገዘ ራስን ማጥፋት ሕጋዊ ለማድረግ የተዘጋጀው ረቂቅ ህግ ድጋሚ ውድቅ መደረጉ ተነግሯል፡፡
ላይፍ ኒውስ እንደዘገበው 5B 88 የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ህግ ባለፈው መጋቢት ወር በግዛቱ የህዝብ ጤና ኮሚቴ በኩል ያለፈ ሲሆን ረቂቅ ህጒ ወደ ዳኝነት ኮሜቴ እንዳይሄድ የታገዘ ራስን ማጥፋት ሎቢ ቡድን ጥረት ቢያደርግም ህጉ በዳኞች ኮሜቴ ታይቶ ውድቅ እንዲሆን ተደረጓል ተብሏል፡፡
በተመሳሳይ ዜና የታገዘ ራስን ማጥፋት መፈቀድን በተመለከተ ሊደረግ የነበረን ህዝበ ውሳኔ የጣሊያን ፍርድ ቤት ማገዱም ተሰምቷል፡፡
ዘ ክርስቲያን ቱዴይ እንደዘገበው በመሞት መብት መከበር ላይ ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ከ 750 ሺ በላይ ጣልያናዊያን የድጋፍ ፊርማ የተሰበሰበበት አቤቱታ የቀረበ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል፡፡
የጣሊያን የህገመንግስት ፍርድ ቤት ግን ጥያቄው በህገመንግስት የተቀመጠውን አስፈላጊን የሰው ልጅ ህይወትና ለደካሞችና ለአደጋ ለተጋለጡ ሰዎች የሚደረግ ዝቅተኛ ጥበቃን አያከብርም ብሏል፡፡
የካቶሊኩ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ይህንን ረቂቅ ህግ ‘ተቀባይነት የሌለው የግድያ ህግ ‘በማለት ተችተውት የነበረ ሲሆን ድርጊቱ ሰብአዊም ክርስቲያናዊም አይደለም ብለውታል፤የህገመንግስታዊው ፍርድ ቤት ህጉን ውድቅ በማድረጉ አድናቆታቸውን አግኝቷል፡፡
በጣሊያን ህግ አንድ ሰው እራሱን እንዲያጠፋ የሚረዳ ማንኛውም ሰው ከአምስት እስከ 12 አመት እስራት ይጠብቀዋል።