Get Mystery Box with random crypto!

ኢየሱስ ይመጣል (የዮሐንስ ራእይ ምዕ. 22) ---------- 20፤ ይህን የሚመሰክር። አዎን፥ | CALVARY gospel ministry

ኢየሱስ ይመጣል

(የዮሐንስ ራእይ ምዕ. 22)
----------
20፤ ይህን የሚመሰክር። አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።

21፤ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።

ስለዚህ እናንተ በእርሱ ስራ
ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃኑ የተጠራችሁ
ቅዱሳን
ለእርስቱ የተለየ ወገን የሆናችሁ

የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ ተጠርታችኃል ይህም በመስቀል ላይ ዋጋ ከፍሎ ፍቅር ግድ ብሎት ከሰማያት ወርዶ እኛን ያደነበትን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንድትሰብኩ ነው።

(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕ. 2)
----------
9፤ እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤

10፤ እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።

በዚህ ወንጌል፦
ወገን ያልነበርነው የእግዚአብሔር ወገን
ሆነናል
ምህረት ያላገኘን የነበርን ምህረት
አግኝተናል
በበደላችን ሙታን የነበርን በእርሱ ስራ
ህይወትን አግኝተናል
ከእግዚአብሔር ርቀን የነበርን በእርሱ ስራ
ቀርበናል
ልጆች ተደርገናል
ቤዛነታችንን አግኝተናል
እግዚአብሔር ርስታችን ሆኗል
በመንፈሱ ታትመናል
ጨለማ የነበርን ብርሃን ሆነናል .....

ይህን በጎነቱን በስፍራ ሁሉ በቤተሰቦቻንን በትምህርት ቤት በስራ ቦታ በጎረቤት በአደባባይ ... እናውራ ሙሽራው ኢየሱስ ይመጣል ለዘላለም ከእርሱ ጋር ሊያኖረን ይወስደናል። ከዚህ የሚበልጥ ምን ደስታ አለን።

ስለዚህ እርሱ ለአንድ ነፍስ መዳን ወዶ ይታገሳልና ያንንም የማስታረቅ ቃል በአንተ በአንቺ ውስጥ አኑራልና ወንጌልን በስፍራ ሁሉ በመስበክ እንዲሁም ሙሽራውን በሚጠባበቅ በተዘጋጀ ህይወት በመኖር ጌታ ሆይ ና ማራናታ እንበል።

ሉቃስ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁷ ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል ቀርቦም ያገለግላቸዋል።
³⁸ ከሌሊቱም በሁለተኛው ወይም በሦስተኛው ክፍል መጥቶ እንዲሁ ቢያገኛቸው፥ እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው።
³⁹ ይህን ግን እወቁ ባለቤት በምን ሰዓት ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ፥ ቤቱም እንዲቆፈር ባልፈቀደም ነበር።
⁴⁰ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።

በኢየሱስ ስም አናፍርም የተሰቀለውን ኢየሱስን በስፍራሁ ሁሉ እንጠራለን እንሰብካለን መዳን በሌላ በማንም የለምና።

እየሱስ ይመጣል
CALVARY EVANGELISM