Get Mystery Box with random crypto!

በኢንዶኔዥያ አንድ ክርስቲያን ዩቲዩበር የ10 አመት እስራት ተፈረደበት። ክርስትያን ዩቲዩበሩ የ1 | CALVARY gospel ministry

በኢንዶኔዥያ አንድ ክርስቲያን ዩቲዩበር የ10 አመት እስራት ተፈረደበት።
ክርስትያን ዩቲዩበሩ የ10 አመት እስራት የተፈረደበት አብዛኛ ሙስሊም በሆነባት ኢንዲኔዥያ ሰዎችን ያስከፋ ነው የተባለን ቪዲዮ በዮቲዩ ቻናሉ ላይ በመለጠፉ ነው ተብሏል።
መሀመድ ካሴ የተባለው ቀድሞ የእስልምና እምነት ተከታይ የነበረውና እ.ኤ.አ. በ2014 ወደ ክርስትና በመጣው በዚህ ሰው ላይ በኢንዶኔዥያ ምዕራብ ጃቫ በሚገኘ ፍርድ የ10 አመት እስር የፈረደበት የቀድሞ እምነቱን የሚተች ቪዲዮ በዩቲዩብ ቻናሉ ሲጭን ነበር ተብሎ ነው።
ክርስቲያን ቱዴይ እንደዘገበው መሀመድ ካሴ በእስር ቤት ውስጥ በሙስና ክስ ተይዞ በነበረ ናፖሊዮን በተባለ የፖሊስ ባለስልጣን ድብድባና ስቃይ የደረሰበት ሲሆን በኢንዶኔዥያ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት የአምልኮ ቤቶች ግንባታ ለማደናቀፍ ከሚሞክሩ ቡድኖች ተቃውሞና እንግልት የሚደረሰባቸ መሆኑም ይነገራል።