2019-12-11 18:35:25
#የአማኞች.ጋሻ
#ክፍል 59
#ክፍል ሰባት
#የማንቂያ.ደወል!
በቁርኣንና በትክክለኛ ሐዲሦች በግልፅ ሂደት የፀደቁትን የአላህ
ስሞችና ባህሪያት ለርሱ ልቅና በሚገባ መልኩ እንዳሉ ማረጋገጥ
አማራጭ የሌለው ግዴታ መሆኑ በተለያዩ ማስረጃዎች
ተብራርቷል!
ይሁንና አብዛኛዎቹን የአላህ መገለጫዎች ለፈጣሪ የማይገባ
ጉድለትን እንደሚያንፀባርቁ በማመን ሳይታክቱ አንድ በአንድ
የሚያፋርሱና ትርጓሜያቸውንም የሚጠመዝዙ ጎራዎች እንዳሉ
አውቀናል። ይህ አካሄዳቸው በተዘዋዋሪ የሚያንፀባርቀው መልዕክት
እጅግ አደገኛ ነው! ሆኖም አብዛኛዎቹ አይረዱትም!
ከዚህ በፊት እንደተገለፀው የአንድ ተናጋሪ ንግግር በተወሰኑ
ርዕሶች ላይ ሁል ጊዜ አሻሚና የተድበሰበሰ የሚሆነው፦
- ወይ ስለ ጉዳዩ ካለው እውቀት ማነስ ነው፤
- ወይ ደግሞ ከአገላለፅ ችሎታው ማነስ ነው፤
- አሊያም እውነታውን የመግለፅ ፍላጎት (ቅንነት) ካለመኖር ነው!
ከእነኚህ ሶስት እንከኖች አንዱም በአላህና በመልዕክተኛው ንግግር
ወስጥ ፍፁም ሊኖር እንደማይችል ደግሞ የማይታበል እውነታ
ነው።(1)
በዚህ መሠረት እነዚያ የ‘ተዕጢል’ አራማጆች ካሉበት ሰመመን
ይነቁ ዘንድ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እናቀርብላቸዋለን፦
1- የቁርኣን አንቀፆችና የመልዕክተኛው አስተምህሮቶች እነዚያን
የተለያዩ የአላህ ባህሪያት ደግመው ደጋግመው በሚያፀኑ የተለያዩ
አገባቦች የሚያወሱት ለምንደነው?
1.1- አላህና መልዕክተኛው ለጌታ የሚገባውን መገለጫ
‘እንደናንተ’ የማያውቁ ሆነው ነው?!
1.2- ወይስ እናንተ በምታዘወትሯቸው ቃላት እውነታውን
መግለፅ ተስኗቸው?!
1.3- ወይስ ሆን ብለው ጉዳዩን በማድበስበስ ሙስሊሞችን
ለማሳሳት ነው?!
መልሳችሁ “አረ በፍፁም..!” የሚል እንደሆነ እንጠብቃለን!
ታዲያ ምነው ለነዚያ ግልፅ መለኮታዊ መመሪያዎች እጅ መስጠት
ተሳናችሁ?!
2- አላህ ስለ ቁርኣን ወደ እውነት የሚመራ ብርሃን፣ የተብራሩ
አንቀፆችን ያዘለ፤ ለግንዛቤ የቀለለ፤ በግልጽ ዐረብኛ ቋንቋ የወረደ
እና የመሳሰሉት መገለጫዎችን የተላበሰ እንደሆነ የሚነግረን ሁሉ
እውነት አይደለም ማለት ነው?!
መቼም “እውነት ነው እንጂ!..” ማለታችሁ አይቀርም! ታዲያ፦
2.1- የጌታን ህልውና በሚመለከተው በዚህ ታላቅ መሠረት
ላይ ቁርኣን የሚያንፀባርቀው ጉልህ መልዕክት ክህደትን
የሚያስገነዝብ ሊሆን ይችላል?!(2) 2.2- ወይስ አላህ በተዟዟረ ዘይቤ ራሱን ለማወደስ በቀጥታ
ጉድለትን የሚያስተላልፉ ገለፃዎችን ደጋግሞ ያሰፍራል?
2.3- እንዴትስ የቁርኣን አንቀፆች እርስ በርስ የሚቃረኑ
ግልፅና ድብቅ መልዕክቶችን አጣምረው ያስተላልፋሉ? እንዲያ
ከሆነ ቁርኣን ሰምና ወርቁ ከሚያደናግር የቅኔ ፈተና የባሰ
እንቆቅልሽ ነው ማለት አይደል?!
3- በዚህ ጉዳይ ላይ ሰዎች ምራቻን የሚያገኙት እናንተ
በምትዳክሩበት “አእምሯዊ” መንገድ ከሆነ ቁርኣን የመውረዱ
ፋይዳ ምንድነው?
3.1- እንዲያውም እንደናንተ አባባል ቁርኣን ብዙ ቦታዎች
ላይ ስለ አላህ መገለጫዎች የሚያንፀባርቀው ጉድለትን ስለሆነ
አማኞች እነዚህን ገለፃዎች ተከትለው በገፍ “ከሚጠሙ”
ጭራሹኑ ባይወርድ አይሻልም ነበር?!
3.2- ወይስ ዓላማው በውስጡ ያሉትን የአላህ መገለጫዎች
በግሪክ ፈላስፋዎች መርሆ መሠረት እንደምንም ማፋረስና
መልዕክታቸውን በተገኘው መሳሪያ መቆልመም የሚችለው
“ጮሌ” ማን እንደሆነ እድሜ በማይፈታው የእንቆቅልሽ
ፈተና መለየት ነው?!
3.3- ውዝግባችንን ሁሉ ወደ አላህና መልዕክተኛው
አስተምህሮት እንድንመልስ በቁርኣን ውስጥ በአፅኖት
የታዘዝነውስ “እንቆቅልሹን” ይባስ ለማወሳሰብ ነው?!
አንዳንዶች ከነዚህ ፅኑ ጥያቄዎች ለመገላገል የሚመዙት አንድ
ደካማ መልስ አለ፦ «እነዚህን አንቀፆች ያወረደው ሊፈትነን
ነው!» ይላሉ!
ይህ በዚህ ቦታ በፍፁም የማይገጥም መልስ ነው፤ ምክንያቱም፦
ሀ- አላህ ሰዎችን የሚፈትነው እውነቱን ከጥመቱ በግልፅ የሚለዩ
መመሪያዎችን ካወረደ በኋላ ብቻ ነውና! አላህ እንዲህ ብሏል፦
«አላህ ህዝቦችን ከመራቸው በኋላ የሚጠነቀቁትን ግልፅ
እስኪያደርግላቸው ድረስ የሚያጠማቸው አይደለም!» [አት-ተውባህ 115]
በነዚህ ሰዎች ግንዛቤ መሰረት ግን እርሱ አምሳያ እንደሌለው
በደፈናው ከሚጠቁሙ ጥቂት አንቀፆች በቀር ባህሪያቱ በዝርዝር
የተወሱባቸው አንቀፆችን ጉልህ መልዕክት መቀበል እንደማይገባ
በቁርኣንም ይሁን በመልዕክተኛው አንደበት አንድም ግልፅ መረጃ
ሳያስተላልፍልን የራሱን ቃል ተከትለን መንገድ ከሳትን በኋላ
ለቅጣት ሊዳርገን ነው ማለት ነው!
ለ- ይህ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እጅግ ያመዘነና አብዛኛውን አማኝ
ለጥመት የሚዳርግ ፈተና ይሆን ነበር፦ ለመሆኑ እነኚህን ግልፅ
መልዕክት ያዘሉ አንቀፆችና ነብያዊ አስተምህሮቶች በ“ዒልመ’ል-
ከላም” መርሆዎች ገልብጠው መረዳት የሚችሉት “ሙስሊሞች”
ስንት ናቸው?!
ሐ- ይህ ከላይ እንደተብራራው የቁርኣንና የሐዲሥ አስተምህሮት
ግልፅነትን የሚቃረን አባባል ነው!
መ- ይህ በቁርኣንና በሐዲሥ የተወደሱት ቀደምት ትውልዶች
የማያውቁት አዲስ ፍልስፍና ነው፤ እውነት ቢሆን ከሌሎች በፊት
አውቀውት ለተከታዩ ትውልድ በገለፁት ነበር።
ሌሎች ምክንያቶችንም መጥቀስ ይቻላል..
4- የአላህ መልዕተኛ (صلى الله عليه وسلم (ዘንድ ኢስላምን ለመማር አዋቂውም
አላዋቂውም፣ ከተሜውም አገሬውም፣ ትልቁም ትንሹም ሁሉም
ከተለያየ የግንዛቤ ደረጃቸው ጋር ሲመጡ እርሳቸው አንዱን
ከሌላው ሳይለዩ የአላህን ባህሪያት ያዘሉትን ቁርኣናዊ አንቀፆችና
ነብያዊ አስተምህሮቶች ያለ “ማስጠንቀቂያ” በገሀድ ያስተላልፉ
ነበር። ታዲያ፦
4.1- ግልፅ መልዕክቶቻቸው የተፈለጉ ባይሆን ኖሮ
የ“ተእዊል” ማብራሪያዎችን በማከል ተከታዮቻቸውን
ከውዥንብር እንዳያድኑ ምን ከለከላቸው?!
4.2- እንዴትስ ሙዐጥ-ጢላዎች ዘውትር እንደሚያደርጉት
ባህሪያቱን በግልፅ ባያፋርሱ እንኳ ቢያንስ አንድ ቀን እንኳ
ቀጭን ጥቆማ ሳያስተላልፉ አለፉ?
5- በአላህና በመልዕክተኛው አንደበት የተወደሱት ሰሓቦችና
ተከታይ ትውልዶች የሙስሊሙ ህብረተሰብ ቀዳሚ ተምሳሌትና
አርዓያ መሆናቸው ይታወቃል። ታዲያ፦
5.1- ይህን መሠረታዊ “እውነታ” እነኚህ ምርጥ ትውልዶች
ሳይረዱት ቀርተው ከጊዜ በኋላ የመጡት የከሃዲያን ፍልስፍና
አቀንቃኞችና የእምነት ኋላ ቀሮች ደረሱበት ማለት ነው?!
5.2- ወይስ ሰለፎች እናንተ እንደምታደርጉት አጋጣሚ
ሲመቻችም ሳይመቻች የእነዚህን መረጃዎች መልዕክት ለማፋረስና ለመቆልመም ያልታደሉት ለዲን ‘እንደ እናንተ’
የሚቆረቆሩ ስላልነበሩ ነው?!
5.3- ይልቁንም በቁርኣንና በሐዲሥ የፀደቁትን የጌታ ባህሪያት
በቀጥታና በተዘዋዋሪ የሚያረጋግጡ ግልፅ ንግግሮችን ይሰነዝሩ
የነበረውስ ሆን ብለው ጉዳዩን ለማድበስበስ ነበር?!
---
#በመጨረሻም አላህ ራሱን የገለፀባቸውን ባህሪያት ማፋረስን እንደ
መሠረታዊ እምነት በመቁጠር በተለያዩ ውዥንብሮች የሙስሊሙን
ህብረተሰብ ሰላም ለሚያደፈርሱት ወገኖች የሚከተለውን ስጦታ
አበረክታለሁ፦
#ታሪካዊ.ውይይት
“ቁርኣን ፍጡር ነው!” የሚለውን የአላህን የመናገር ባህሪ
የሚያፋርስ የክህደት አቋም ባለመቀበላቸው ታስረው የነበሩ አንድ
በእድሜ ጠና ያሉ ዓሊም ከአሕመድ ኢብን አቢ ዱኣድ
(3) ጋር
ኸሊፋው አል-ዋሢቅ (232 ዓ.ሂ) ባለበት ያደረጉትን ምልልስ
በአጭሩ እንደሚከተለ
104 views15:35