Get Mystery Box with random crypto!

የአማኞች ጋሻ

የቴሌግራም ቻናል አርማ byshakheliyasahmed — የአማኞች ጋሻ
የቴሌግራም ቻናል አርማ byshakheliyasahmed — የአማኞች ጋሻ
የሰርጥ አድራሻ: @byshakheliyasahmed
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 43

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2020-06-12 09:17:28 .
.
.
ሸርሁ አጅሩሚያ ኪታብ ሙምቲእ ደርስ

የተጠናቀቀ ደርስ
|
በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል ኬሚሴ

https://t.me/YeteqeruKitabochBicha/101
https://t.me/YeteqeruKitabochBicha/101
135 views06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-05-24 06:12:58
https://t.me/sadamnassir/1897
153 views03:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-05-24 05:39:56 عيدكم مبارك

تقبل الله منا ومنكم

ከወንድማቹ #ሳዳም
130 views02:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-05-23 12:46:12 (1)ኛ

ጥያቄ ቁ. 6 (ላሚያ)
አምስተኛው ቤት ከላሚየቱ ኢብኑ ተይሚያ ስለምንድን ነው የምያወራው?
السؤال السادس: البيت الخامس من لامية ابن تيمية عن ماذا تتحدث؟
اختبار سري
٥ إجابات

መልስ ለማግኘት
https://t.me/sadamnassir/1822



(2)ኛ

የአስር ምዕራፍ ትንታኔ
በሸይህ አብዱል አዚዝ ቢን ባዝ

ሙሉ ፅሁፉን ለማግኘት
https://t.me/sadamnassir/1816


(3)ኛ

(ተመይዩዝ)= ችላ የተባለው ሐቅ!!
ወሳኝ ወቅታዊ ጉዳይ

ፅሁፉን ለማግኘት
https://t.me/sadamnassir/1818


(4)ኛ

(ቲያንሶች) እንጠንቀቅ
የወቅቱ የሚዲያ ሌቦች እንራቅ!!

ሙሉውን
https://t.me/sadamnassir/1815


(5)ኛ

عقيدة أهل السنة والجماعة

የአህለሱና ወልጀመዓ አቂዳ (እምነት)

አዘጋጅ ሸይኽ #ኢብኑ_ኡሰይሚን

በኡስታዝ #ሙሐመድ_አሚን

በሸዋሮቢት ከተማ የተሰጠ ትምህርት

ከክፍል 1-39



ከ1-39
ለማግኘት ይጫኑ
https://t.me/sadamnassir/1773


(6)ኛ

በራስ የመደነቅ ክፋት
መጨረሻው የአላህ ፀጋ እስከ መካድ ይደረሳል

ሙሉውን
https://t.me/sadamnassir/1771


(7)ኛ

#የዘካተል ፊጥር ብይን

በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)

ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ

https://t.me/sadamnassir/1770


(8)ኛ

የደሴው የአደባባይ ደዕዋ!!!
የድምፅ ፋይሉን

https://t.me/sadamnassir/1769


(9)ኛ

ረመዳን ቀን 27ን
ሰሃባ
አንድ ዱአ!!

በውዱ ኡስታዝ ሳዳት ከማል

https://t.me/sadamnassir/1766


(10)ኛ

ረመዳን ቀን 26
አሞራ፣ ሰው
ሁለት ዱአዎች

በሳዳት ከማል

https://t.me/sadamnassir/1764


(11)ኛ

የኢድ ሶላት አስመልክቶ የተለቀቀ ወቅታዊው ሙሃደራ

https://t.me/sadamnassir/1759


(12)ኛ

(በደሴ አደባባይ ከተደረጉ ደዕዋዎች ውስጥ እነሆ አንዱን ላቋድሳቹህ)

እኛ እንኳ አልቀዳንውም ነበር ድምፃችን ከሰለለ ቡሃላም ቢሆን በርቀት ሆኖ ከፊሉን የቀዳው ሰው አግኝተናል

እናም በዚህ ድምፅ ፋይል ውስጥ ወደ እየሱስም ወደመላኢካም ወደጦሳ ተራራም ወዘተ አንጠጋም የሚል መልእክት ተላልፎበታል

ድምፁን
https://t.me/sadamnassir/1756


(13)ኛ

በሀገራችን ውስጥ የሃዳዲያን አስተሳሰብ የሚያራምዱ ሰዎች ዋና ዋናዎቹ ድንበር ያለፉባቸው ነጥቦች!!

ክፍል ሁለት ፅሁፉን ለማግኘት
https://t.me/sadamnassir/1753


(14)ኛ

የሃገራችን ታማኝና አቋማቸው ማይቀያየረው ዱአቶች

ከአመት በፊት የተፃፈ
https://t.me/sadamnassir/1750



(15)ኛ

የሃዳዲያ መለስተኛ ሜቴክ
ፅሁፉን
https://t.me/sadamnassir/1749


(16)ኛ

የጥሬ ዘካ በተመለከተ በሸይኽ አቡዘር ሀሰን ሃፊዘሁላህ

ድምፁን
https://t.me/sadamnassir/1744


(17)ኛ

የሙስጠፋ አብደላህ
ኮተት (አንድ)

https://t.me/sadamnassir/1824


(18)ኛ

كَيفِيَّةُ صَلَاةِ الْعِيدِ فِي الْبُيُوتِ (خلال 4:21 دقيقة)

የዒድ ሶላት አሰጋገድ በቤት ውስጥ (በ4:21 ደቂቃ ውስጥ)



https://t.me/sadamnassir/1829


(19)ኛ

የኢድ ሶላት አሰጋገድ በቤት ውስጥ!!

https://t.me/sadamnassir/1827
152 views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-05-01 21:36:08 https://t.me/sadamnassirr/1499

አሰደሳች ዜና ከትምህርት ገበታ ለተገለሉ ልጆች። አዲስ የአቂዳ ኪታብ በውዱ ኡስታዝ አቡ-ሙስሊም አል አሩሲ።
የኪታቡ ስም:- ላሚየቱ ኢብኑ-ተይሚያህ

ጆይን ብለው ይቀላቀሉ።
ቴሌግራም
@abumuslimChildern

Abu muslim Childern
دروس العقيدة للأطفال بالأستاذ أبي مسلم العروسي
https://t.me/abumuslimChildern

ዩ-ቲዩብ
Youtube/Abumuslim Umer



Abu muslim Childern
دروس العقيدة للأطفال بالأستاذ أبي مسلم العروسي
https://t.me/abumuslimChildern


https://t.me/sadamnassirr/1499
135 views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-02-17 14:38:14 http://t.me/sadamnassirr
230 views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-02-15 14:50:22 fb ላይ like and comment ያድርሱኝ። እቀበላለሁ።!!!!

https://www.facebook.com/ela.nassir
29 views11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-01-24 09:03:30 ሁለንም ለየ ብቻ ለማግኘት

ሊንክ ብቻ

@onlylinki


ተውሒድ የ2 ሃገር የስኬት ቁልፍ

@Byibnumunewer


መንዙማ የኡዝታዝ የሳዳት መፅሐፍ

@Abumeryemmm


የአማኛች ጋሻ የሸይኽ ኢሊያስ አህመድ መፅሐፍ

@Byshakheliyasahmed


ጋብቻዎች በኡስታዝ ሙሃመድ አሊ ዳውድ

@gabichawooch


የሶላት መስፈርቶች በኡስታዝ ሁሴን ሽፋ

@yesolatmesfertoch


ተውሒድ

@yetewhidmetsaf




ሁሉም በአንድ ላይ
http://t.me/sadamnassirr
343 views06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-01-01 07:19:33 #የአማኞች.ጋሻ
#ክፍል 62

#2ኛ- ጥርጣሬን.ለሚያስተናግዱ


መሠረቱ የተጠናከረ ርዕሰ-ጉዳይ ላይ ለሚነሱ አላፊ ውዥንብሮች ትክክለኛ ምላሽን አለማወቅህ/ሽ በጉዳዩ ላይ ጥርጣሬን አያጭርም! ምክንያቱም መሠረታዊ እርግጠኝነት በቅርንጫፋዊ ጥያቄ ሊናወጥ አይገባምና! በዚህ ላይ ደግሞ አንተ ልትፈታው ያልቻልከውን የጥርጣሬ ቋጠሮ ሌላ አዋቂ በአላህ ፈቃድ ይፈታዋል!
«ልቦናህን ለአላፊ ሃሳቦችና ውዥንብሮች እንደ እስፖንጅ አታድርገው! - እነሱን መጥጦ ከነሱ ሌላ የሚተፋው አይኖረውምና! ነገር ግን እንደ ጠንካራ መስታወት አድርገው፦ ውዥንብሩ ከላይ በኩል ያልፋል፤ ወደ ውስጥ ግን አይዘልቅም! በጥራቱ አሳልፎ ያያቸዋል፤ በጥንካሬውም ይቋቋማቸዋል! የሚያጋጥምህን ውዥንብር ሁሉ ለልብህ የምታግተው ከሆነ ግን የውዥንብር መጠራቀሚያ ይሆናል!»(1)

#3ኛ- እውነቱን.ለተረዱ






እውነትን ለማወቅ አላህ የረዳው ሰው እርሱን ሊያመሰግንና በዚያ ላይ እንዲያፀናው ሊማፀነው ይገባል። ሌሎችን በንቀት አይን ከማየትም ራሱን ሊጠብቅ የግድ ይላል።

በተረፈ እውነታውን ለማመላከት የምናደርገው ጥሪ ሁልጊዜ በጥበብና በእውቀት ላይ የተገነባ ይሁን! የተረዳ ሁሉ ሌላን ሊያስረዳ እንደማይችልም አይዘንጉ! ከፍሬ-ቢስ ክርክር መራቅም አንድ ብልሃት ነው! ከሁሉ በላይ ውድ ንብረታችን እምነታችን ነውና እንዳይበከል እንጠብቀው፤ እንንከባከበው!



አላህ ሁላችንንም ወደ ቀጥተኛው ጎዳና ይምራን!





(1) ከሸይኹ’ል-ኢስላም ኢብኑ ተይሚይ-ያህ ወርቃማ ምክሮች አንዱ ነው። “ሚፍታሑ ዳሪ’ስ-ሰዓዳህ” ሊ’ብኒ’ል-ቀይ-ዪም (1/140) ይመልከቱ።



ጨርሻለሁ!




#በአላህ.ፍቃድ.የሸይኽ.ኢሊያስ.አህመድ.የአማኞች.ጋሻ.ተጠናቀቀ።


ሙሉውን ለማግኘት
ከክፍል #አንድ እስክ ክፍል #ስድሳ.ሁለት
(1-62)
ይጫኑ
@Byshakheliyasahmed


በተወዳጅ የሱና ኡስታዞቻችን የተፃፉ መፅሐፎች ለማግኘት፡፡

ሌሎችንም የተውሒድ ዕውቀት ለመሠብሠብ join


በ telegram

t.me/sadamnassirr s.


በዋትሳት

https://chat.whatsapp.com/Dyebl8aTWjmDeTcIBrdoC3
231 views04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-12-20 22:30:33 #የአማኞች.ጋሻ
#ክፍል.61

#ማስጠንቀቂያ
ማስጠንቀቂያ







በተለያዩ ሊቃውንት አንደበት የአላህን ባህሪያት ማፋረስ ክህደትን (ኩፍርን) መፈፀም እንደሆነ የሚያስገነዝቡ ጥቅል ፍርዶችን መስፈርቶች ሳይሟሉ በቀጥታ በግለሰቦች ላይ ተፈፃሚ ማድረግ አይፈቀድም! ምክንያቱም በጥቅል ገለፃ “ይህንን የሰራ ካፊር ይሆናል!” ሲባል በዋነኝነት የሚፈለገው ተግባሩ የክህደት ተግባር (ኩፍር) እንደሆነ ማመላከት እንጂ ይህንን በየትኛውም ምክንያት የተገበረ ሁሉ ያለ ቅድመ-ሁኔታ ከኢስላም ይሰናበታል ማለት አይደለምና!



አሁንም ሸይኹ'ል-ኢስላም ኢብኑ ተይሚይ-ያህ እንዲህ ይላሉ፦

"...እንደነዚያ መሃይማንና መሰሎቻቸው ያልሉ ግለሰቦችን በተመለከተ አንዳቸው ነብያትን የተፃረረ መሆኑ የሚገለፅበት መለኮታዊ ማስረጃ ከፀናበት በኋላ ካልሆነ በቀር ከከሃዲያን እንደሚመደብ በመፍረድ በ"ኩፍር" ወደ መፈረጅ ማምራት አይፈቀድም! - ንግግሩ ያለምንም ጥርጥር የክህደት ንግግር ቢሆን እንኳ! ከፊል ቢድዓዎች ከከፊሉ የባሱ ከመሆናቸውና ከፊል የቢድዓህ አራማጆች ከፊሎቹ ዘንድ የሌለ (የተሻለ) እምነት ያላቸው ከመሆናቸው ጋር ይህ ገለፃ ማንኛውንም ግለሰብ በከሃዲነት መፈረጅን የተመለከተ ነው!




እናም ማንም ሰው ከሙስሊሞች አንዱ ቢሳሳት እንኳ ማስረጃው ፀንቶ እስኪደርሰውና እውነተኛው መንገድ እስኪገለጥለት ድረስ በከሃዲነት የመፈረጅ መብት የለውም! አማኝነቱ በርግጠኝነት የፀደቀ ሰው ይህ (አማኝነቱ) በጥርጣሬ አይወገድም፤ ይልቁንም ማስረጃው ከፀናበትና ውዥንብሩ ከፀዳለት በኋላ እንጂ አይወገድም!»(1 )
ይህንን ሚዛናዊ የአህሉ’ስ-ሱን-ናህ አካሄድ የሚፃረር ፅንፈኛ አቋም የሚያንፀባርቁት ግለሰቦችና ቡድኖች ዋነኛ ስህተት ሁለት እርከኖች አሉት፦




አንደኛው፦ ጥፋት ያልሆኑ ነገሮችን እንደጥፋት በመቁጠር፣ ወይም ጥፋት ቢሆኑ እንኳ ለክህደት ጭራሽ የማያበቁ ጉዳዮችን በማጋነን በክህደት መፈረጅ ሲሆን፤
ሁለተኛው፦ የኩፍር ወይም የሽርክ መገለጫዎችን የፈፀሙ ግለሰቦችን ወይም ቡድኖችን መስፈርቶች መሟላታቸውንና የብይኑን ተፈፃሚነት የሚያግዱ ምክንያቶች አለመኖራቸውን ሳያረጋግጡ በቀጥታ በከሃዲነት መፈረጅ ነው።




አንድ የኩፍር አቋም ያንፀባረቀ ግለሰብ በከሃዲነት እንዳይፈረጅ ሊያግዱ ከሚችሉ ምክንያቶች መካከል አለማወቅ፣ መሳሳት፣ መገደድና የመሳሰሉት ይገኛሉ።
ብዙ የቢድዓህ ጎጠኞች ሁለቱንም የስህተት እርከኖች በመፈፀም ህዝበ-ሙስሊሙን ሲያውኩና ሲከፋፍሉ እንደኖሩ የሚያረጋግጡ እማኞች በታሪክ ማህደር የሰፈሩ ሲሆን በነባራዊው ሂደት አንዳንዶቹ ዘንድ በተጨባጭ የምናየው የ“ተክፊር” ግንፍልተኝነትም በቂ መስካሪ ነው!(2 ) የሚደንቀው ግን ከላይ ያሳለፍነው የአህሉ’ስ-ሱን-ናህ ሚዛናዊ ብይን በተለያዩ ፅሁፎቻቸው ከመብራራቱ ጋር እነርሱን በተቃራኒው የተክፊር ጥማት ያለባቸው አድርጎ ለመሳል የሚደረገው ያላሰለሰ መፍጨርጨር ነው፤ የማንን ለማን?!







#መዝጊያ

#እንግዲህ አንባቢ ሆይ!


የአማኞች ጋሻ

1- እውነታው ግልፅ ነው! አላህ ለራሱ በቁርኣኑ ወይም በመልዕክተኛው አንደበት ያፀደቀውን ሁሉ ያለ ማመሳሰልና ያለ ትርጉም ማጣመም እንቀበላለን፤ ለርሱ ልቅና በሚገባ መልኩ የባህሪያቱን ጥቅል መልዕክት እናረጋግጣለን። ይህ ነው የነብያትና የተከታዮቻቸው ጎዳና! ይህ ነው ውዝግብን የሚፈታው ቀላሉ የመፍትሄ አካሄድ!




2- ሁል ጊዜም ቢሆን የነብያት ተከታዮች የሚጓዙበት መንገድ በህሊና ሰላምና በልቦና ስክነት የታጀበ ነው! ተፃራሪው ደግሞ በንትርክና በጥርጣሬ የተወሳሰበ ነው።
3- በአንዳንድ ሁኔታዎች የጥመት አቀንቃኞች በርዕሱ ላይ የሚያንፀባርቁት ትክክለኛ አቋም ካልለ ቀድሞውኑ በቁርኣንና በሐዲሥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሰፈረና የእውነት ተከታዮች ዘንድ የታወቀ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፤ ስለዚህ ከነርሱ የሚከጀል አዲስ እውነታ የለም። እውነትን ከገጠሙባቸው ውጭ ያሉ ንግግሮቻቸው ደግሞ የቁርኣንም ይሁን ሌሎች አእምሯዊ መረጃዎች ላይ የተመረኮዙ አይደሉም፤ ሆኖም የሐቅ ተከታዮችን የሚጋፈጡባቸው ስልቶች በአብዛኛው ከሚከተሉት አራት ምድቦች አይወጡም፦








ሀ- አዳዲስ የቢድዓህ ፈሊጦችን መፈልሰፍና እነርሱን እንደ መመዘኛ ማቅረብ፤ ለ- ፅኑ እውነታዎች ላይ ማጠራጠሪያ ጥናቶችን ማቅረብ፤ ሐ- እነ “እገሌ”ን በጭፍን መከተል፤(1)



መ- እውነተኞችን በሀሰት ለማጥላላት መቅጠፍ! ይህንን አስተዋዮች አያጡትም!

---

(1) አላህ እንዲህ ይላል፦
 «ከጌታችሁ ዘንድ ወደናንተ የወረደውን ተከተሉ፤ ከርሱ ውጭ ሌሎች ረዳቶችን አትከተሉ!»[አል-አዕራፍ 3]


#ሶስት.ምክሮች


1ኛ- ትክክለኛውን ጎዳና ለሳቱ አላህ እንዲህ ይላል፦
 «“እኔ የምገስፃችሁ በአንዲት ነገር ብቻ ነው!” በላቸው! ፡- ለአላህ ብላችሁ ሁለት ሁለት ሆናችሁና ለየብቻ ተነስታችሁ ከዚያ እንድታስተውሉ!..»[ሰበእ 46]




ያስተውሉ! ተጨባጩ ዓለም እንደሚመሰክረው ብዙ ሰዎች በተሰበሰቡበት አጋጣሚ እውነታን አጣርቶ የሚያሳይ ውይይት መፈፀም እጅግ አስቸጋሪ ነው - በተለይ በእምነት ጉዳይ ላይ! ምክንያቱም በአብዛኛው ንፁህ እሳቤን የሚያደፈርሱና ጭፍን ወገንተኝነትን የሚቀሰቅሱ ሁኔታዎች መንፀባረቃቸው አይቀርምና! በአንቀፁ ላይ እንደተመለከተው ሁለት ሆነው አንዱ የደረሰበትን እውነታ ለሌላው በማቅረብ በቅንነት መወያየት ለአስተውሎት አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል! ለብቻው የሆነም ሰው ባልተረበሸ ልቦና መረጃዎችን የማገናዘብ እድል ይኖረዋል።(3 )




ከዚህ ጋር አላህ ቀጥተኛውን መንገድ እንዲመራን መማፀን ሊዘነጋ የሚችል ጉዳይ አይደለም!




(1) “መጅሙዑ’ል-ፈታዋ” (12/500-501)

(2) “አሕባሾች” ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆናሉ! በርካታ ዑለማዎችን ጨምሮ ብዙዎችን ያለ አግባብ በከሃዲነት (በካፊርነት) እንዲፈርጁ ምክንያት የሆኗቸውን ግድፈቶች ከነእርማቶቻቸው በአጭሩ ለመቃኘት “ፊርቀቱ’ል- አሕባሽ” የተሰኘውን ጥናታዊ ፅሁፍ ከ(2/645) ጀምሮ ይመልከቱ።

3 ) “አል-በሕሩ’ል-ሙሒጥ” (ተፍሲር አቢ ሐይ-ያን) (7/290-291) ይመልከቱ።


ኢንሻአላህ ይቀጥላል.......
በተወዳጅ የሱና ኡስታዞቻችን የተፃፉ መፅሐፎች ለማግኘት፡፡

ሌሎችንም የተውሒድ ዕውቀት ለመሠብሠብ join


በ telegram

t.me/sadamnassirr s.


በዋትሳት

https://chat.whatsapp.com/Dyebl8aTWjmDeTcIBrdoC3
219 views19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ