Get Mystery Box with random crypto!

#የአማኞች.ጋሻ #ክፍል 62 #2ኛ- ጥርጣሬን.ለሚያስተናግዱ መሠረቱ የተጠናከረ ርዕሰ-ጉዳይ ላ | የአማኞች ጋሻ

#የአማኞች.ጋሻ
#ክፍል 62

#2ኛ- ጥርጣሬን.ለሚያስተናግዱ


መሠረቱ የተጠናከረ ርዕሰ-ጉዳይ ላይ ለሚነሱ አላፊ ውዥንብሮች ትክክለኛ ምላሽን አለማወቅህ/ሽ በጉዳዩ ላይ ጥርጣሬን አያጭርም! ምክንያቱም መሠረታዊ እርግጠኝነት በቅርንጫፋዊ ጥያቄ ሊናወጥ አይገባምና! በዚህ ላይ ደግሞ አንተ ልትፈታው ያልቻልከውን የጥርጣሬ ቋጠሮ ሌላ አዋቂ በአላህ ፈቃድ ይፈታዋል!
«ልቦናህን ለአላፊ ሃሳቦችና ውዥንብሮች እንደ እስፖንጅ አታድርገው! - እነሱን መጥጦ ከነሱ ሌላ የሚተፋው አይኖረውምና! ነገር ግን እንደ ጠንካራ መስታወት አድርገው፦ ውዥንብሩ ከላይ በኩል ያልፋል፤ ወደ ውስጥ ግን አይዘልቅም! በጥራቱ አሳልፎ ያያቸዋል፤ በጥንካሬውም ይቋቋማቸዋል! የሚያጋጥምህን ውዥንብር ሁሉ ለልብህ የምታግተው ከሆነ ግን የውዥንብር መጠራቀሚያ ይሆናል!»(1)

#3ኛ- እውነቱን.ለተረዱ






እውነትን ለማወቅ አላህ የረዳው ሰው እርሱን ሊያመሰግንና በዚያ ላይ እንዲያፀናው ሊማፀነው ይገባል። ሌሎችን በንቀት አይን ከማየትም ራሱን ሊጠብቅ የግድ ይላል።

በተረፈ እውነታውን ለማመላከት የምናደርገው ጥሪ ሁልጊዜ በጥበብና በእውቀት ላይ የተገነባ ይሁን! የተረዳ ሁሉ ሌላን ሊያስረዳ እንደማይችልም አይዘንጉ! ከፍሬ-ቢስ ክርክር መራቅም አንድ ብልሃት ነው! ከሁሉ በላይ ውድ ንብረታችን እምነታችን ነውና እንዳይበከል እንጠብቀው፤ እንንከባከበው!



አላህ ሁላችንንም ወደ ቀጥተኛው ጎዳና ይምራን!





(1) ከሸይኹ’ል-ኢስላም ኢብኑ ተይሚይ-ያህ ወርቃማ ምክሮች አንዱ ነው። “ሚፍታሑ ዳሪ’ስ-ሰዓዳህ” ሊ’ብኒ’ል-ቀይ-ዪም (1/140) ይመልከቱ።



ጨርሻለሁ!




#በአላህ.ፍቃድ.የሸይኽ.ኢሊያስ.አህመድ.የአማኞች.ጋሻ.ተጠናቀቀ።


ሙሉውን ለማግኘት
ከክፍል #አንድ እስክ ክፍል #ስድሳ.ሁለት
(1-62)
ይጫኑ
@Byshakheliyasahmed


በተወዳጅ የሱና ኡስታዞቻችን የተፃፉ መፅሐፎች ለማግኘት፡፡

ሌሎችንም የተውሒድ ዕውቀት ለመሠብሠብ join


በ telegram

t.me/sadamnassirr s.


በዋትሳት

https://chat.whatsapp.com/Dyebl8aTWjmDeTcIBrdoC3