Get Mystery Box with random crypto!

መጋቢት 2/2015 የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የዕቅድ እና በጀት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ከ20 | Bule Hora University

መጋቢት 2/2015
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የዕቅድ እና በጀት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ከ2016 እስከ 2018 ዓ.ም በሚተገበረዉ ዕቅድ ዙሪያ ለሠራተኞች ሥልጠና ሰጠ፡፡

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የዕቅድ እና በጀት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ከ2016-2018 ዓ.ም ለተከታታይ ሦስት ዓመት በምተገበረዉ ዕቅድ ዙሪያ ለሠራተኞች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡
የዕቅድ እና በጀት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዱቤ ቁምቢ እንደገለፁት የሥልጠናዉ መሰጠት ዋና ዓላማዉ ቀደም ሲል በዕቅድ አዘገጃጀት፤በበጀት አጠቃቀም፤በሪፖርት አደራረግና በመሳሰሉ ተያያዥ ጉዳዮች ጋር የሚታዩትን ችግሮች ለመቅረፍ እንደሆነ አስረድቷል፡፡

በመሆኑም በቀጣይ ለሦስት ዓመት በምተገበረዉ ዕቅድ ላይ ከወዲሁ አስፈላጊዉን ዝግጅት በማድረግና ተቋሙ እስካአሁን በነበረዉ ሂደት ያለበትን ጠንካራ ጎን እና ድክመትን በመፈተሽ እንዲሁም በዕቅዱ ዙሪያ የሚመለከታቸዉን ባለ ድርሻ አካላት በማሳተፍ የዕቅድ ዝግጅቱ መከናወን እንዳለበት አስገንዝቧል

በተጨማሪም በመድረኩ ላይ በበጀት አጠቃቀም ዙሪያ ሥልጠናዉን የሰጡት የበጀት ባለሙያ ወ/ሮ ዮርዳኖስ ግዛቸዉ እንደተናገሩት አንድ ዕቅድ ሲታቀድ ከበጀት ጋር የተያያዘ በመሆኑ በመ/ቤቱ ዉስጥ የተመደበዉን የበጀት ድልድል ታሳቢ በማድረግ ዕቅዶቻቸዉን ማቅረብ እንደሚገባ ተናግሯል፡፡
ባለሙያዋ አያይዛም በፕሮግራም በጀት አጠቃቀም እና ለኦዲት ግኝት መንስኤ በሚሆኑት ጉዳች ላይ አጠር ያለ ገለፃ በማድረግ ከተሣታፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥቷል፡፡

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍቃዱ ወ/ማርያም በዕለቱ በሥልጠና መድረኩ ላይ በመገኘት በዕቅድ አዘገጃጀት ዙሪያ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለፃ ከሆነ የአንድ ተቋም ስኬት መነሻ ሊሆን የሚችለዉ ግልጽ እና አሣታፊ በሆነ መልኩ የተዘጋጀ ዕቅድ ሲኖር በመሆኑ እያንዳንዱ ባለ በጀት መ/ቤት የሚመለከታቸዉን አካላት በማሣተፍ እና ከበጀት ጋር ልጣጣም የሚችል ዕቅድ በማቀድ ወደ ሥራ መግባት እንደሚየስፈልግ ተናግሯል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አክለዉም በአዘገጃጀቱ ዙሪያ ተገቢዉን ትኩረት በመስጠትና እያንዳንዱን ሀሳብ በመተንተን ግልጽ በሆነ ቋንቋ መቀመጥ አለበት የሚል አስተያየት ሰጥቷል፡፡

በመጨረሻም እያንዳንዱ ዕቅድ ማጠንጠኛዉ ከጀት ጋር ስለሆነ የተመደበዉን በጀት ግልጽ በሆነ እና በቁጠባ መጠቀም የሚያስፈልግ መሆኑን በመጥቀስ በዕቅዱ መሠረት የተሠሩ ሥራዎችን አፈፃፀም በተቀመጠለት የጊዜ ሠለዳ መሠረት ለሚመለከተዉ አካል ሪፖርት ማድረግ እንደሚያስፈልግም ተናግሯል፡፡

ለላቀ ለዉጥ እንተጋለን !
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ