Get Mystery Box with random crypto!

ጥር 09/2015 በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አመራር ሆነው የተመደቡ የስራ ሀላፊዎች ከዩኒቨርሲቲው ካውን | Bule Hora University

ጥር 09/2015
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አመራር ሆነው የተመደቡ የስራ ሀላፊዎች ከዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ጋር የትውውቅ መርሀ ግብር አከናወኑ።

ዶ/ር ፍቃዱ ወልደ ማርያም ውዴሳ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት፣ ዶ/ር ብርሀኑ ለማ ሮቤ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕ፣ ረ/ፕ ገመዳ ኡዶ የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕ በመሆን የተመደቡ ሲሆን ከዩኒቨርሲቲው የካውንስል አባላት ጋር ትውውቅ አድርገዋል ።
የዩንቨርስቲው ፕሬዚዳንት በመሆን ላለፉት ስድስት ወራት ያገለገሉት ዶ/ር ታምሩ አኖሌ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ከምደባ ወደ ቅበላ እንዲሸጋገር ለማድረግ እና በተቋሙ ያሉትን ክፍተቶች ለማስተካከል በጋራ እገዛ እንደሚያደርጉ በመግለፅ አዲስ ለተመደቡት የዩኒቨርሲቲው አመራሮች መልካም የስራ ጊዜን ተመኝተዋል።
ዶ/ር ፍቃዱ ወልደ ማርያም ውዴሳ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት እንዲሁም በዲላ ዩኒቨርሲቲ ላለፉት አምስት ዓመታት የአካዳሚክ ጉዲዮች ም/ፕ በመሆን አገልግለዋል። ዶ/ር ብርሀኑ ለማ ሮቤ በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ለበርካታ ዓመታት በመምህርነት እና የኮሌጅ ዲን በመሆን አገልግለዋል ።
አዲስ የተመደቡት የዩኒቨርሲቲው የስራ ሃላፊዎች ለካውንስል አባላቱ የስራ እና የህይወት ልምዳቸውን አጋርተዋል።
"በመተጋገዝ፣ያሉ ችግሮችን በመለየት ለችግሮቹ የጋራ መፍትሄ በማዘጋጀት ለተሻለ ተቋማዊ ለውጥ ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በጋራ እንደሚሰሩም አስረድተዋል።
አቶ ጫኔ አደፍርስ በትምህርት ሚኒስቴር የተቋማት አደረጃጀት እና አመራር ዴስክ ሲሆኑ በዩኒቨርሲቲው የስራ ሂደት ዙሪያ በመድረኩ ማብራሪያ ሰጥተዋል ።
ተሳታፊ የካውንስል አባላቱም አዲስ ለተመደቡት የስራ ሃላፊዎች አስተያየት እና መልካም የስራ ጊዜ ምኞትን በመድረኩ አንፀባርቀዋል።

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ