Get Mystery Box with random crypto!

ታኅሣሥ 27/2015 ዓ/ም በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ 'በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና' በሚል ርዕስ ሲደ | Bule Hora University

ታኅሣሥ 27/2015 ዓ/ም
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ "በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና" በሚል ርዕስ ሲደረግ የቆየው የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ።
የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሰላም ሚንስቴር ሚንስቴር ዴኤታ እና የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ስዩም መስፍን በመድረኩ የምክክር መነሻ ሰነድ አቅርበዋል።ዶ/ር ስዩም መስፍን ላለፉት 250 ዓመታት በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ላይ የምሁራን ሚና እና ተሳትፎ ታሪካዊ ዳራውን እና አሁናዊ ሁኔታዎችን በስፋት ዳሰዋል።የምሁር ምንነት እና አስፈላጊነት እንዲሁም ለትውልድና ለሀገር ግንባታ ከምሁራን የሚጠበቁ ሀሳቦችን በአካተተ መልኩ በዶ/ር ስዩም መስፍን የምክክር ሰነዱ ለምሁራኑ ተብራርቷል።
የኢ.ፍ.ድ.ሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ በበኩላቸው የትውልድ ግንባታ ላይ በማተኮር ለጋራ እና ዘላቂ ጥቅማችን ቅድሚያ በመስጠት ለሀገር ህልውና የሚበጁ ሀሳቦችን ማፍለቅ ከምሁራን እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።
የዩንቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታምሩ አኖሌ በበኩላቸው "ችግሮችን ለመፍታት የጋራ ውይይት ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን በመጠቆም የዩንቨርስቲው አንደኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም በቀጣይ ቀናት ለውይይት እንደሚቀርብ አስረድተዋል።
በቀረበው የምክክር ሰነድ ላይ እና አጠቃላይ ሀገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የዩኒቨርሲቲው ምሁራን በንቃት በመሳተፍ በርካታ አስተያየት እና ጥቆማዎችን እንዲሁም ጥያቄዎችን ሰንዝረዋል።
ከምሁራኑ ለተነሱ ጥያቄዎች ዶ/ር ስዩም መስፍን እና አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት 'መንግስት ለሀገር የሚበጁ የምሁራን ሀሳቦችን ለመቀበል እና ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ስለመሆኑ አስረድተዋል ።
የምክክር መድረኩ ለተከታታይ 4 ቀናት በዩኒቨርሲቲው ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፤ የዩንቨርስቲው ምሁራንም በመድረኩ በንቃት ተሳትፎ አድርገዋል።

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
ለላቀ ለውጥ እንተጋለን!