Get Mystery Box with random crypto!

ታህሳስ 27/2015 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ በ2015 የትምህርት ዘመን ለሚመረቁ | Bule Hora University

ታህሳስ 27/2015
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ በ2015 የትምህርት ዘመን ለሚመረቁ ተማሪቹ ሞዴል የመዉጫ ፈተና አዘጋጀ።

የኢንፎርማትክስ ኮሌጅ በ2015 ዓ.ም የመዉጫ ፈተና ለሚወስዱ ተመራቂ ተማሪዎች ለመውጫ ፈተና ለማዘጋጀት በኮሌጁ ደረጃ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ እንደ ሀገር የተቀመጠውን አቅጣጫ መሰርት በማድረግ በመውጫ ፈተና (Exit exam) ዙርያ ለተማሪዎች እንዲሁም ለመምህራኖቹ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር በማካሄድ ነዉ የመማር ማስተማር ስራዉን እያስቀጠለ ያለዉ።

የዚህ ፈተና አላማ ምን እንደሆነ ሲገልጹ የኮሌጁ ዲን የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ደሳለኝ አወቀ እንዳሉት በሃገር አቀፍ ደረጃ ለሚሰጠዉ ፈተና ተማሪዎቹ ፈተናዉ አዲስ እንዳይሆንባቸዉ፣እራሳቸውን ችለው እንዲሰሩ እንዲሁም ምን ያህል ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸዉ እራሳቸዉን የሚገመግሙበት ነው ብለዋል።
በመሆኑም ተማሪዎችን ለመዉጫ ፈተና ለማነቃቃት ብሎም ብቁ ለማድረግ ታስቦ የታቀደውን የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ለተማሪዎቹ በመስጠት የመጀመሪያ ዙር Model Exam በ25/04/2015 ዓ.ም በOnline ለአራት ት/ት ክፍሎች ማለትም ለኢንፎርሜሽን ሲይስተም፣ለኢንፎርሜሽን ሳይንስ፣ለኮምፒዩተር ሳይንስ እንዲሁም ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በመስጠት በተሰካ ሁኔታ መጠናቀቁን የኢንፎርማትክስ ኮሌጅ ም/ዲን የሆኑት መ/ር አሰፋ ሰንበቶ ገልጿል።
ተማሪዎችን በE-Learning System በመጠቀም ለመውጫ ፈተና የማዘጋጀት ስራ በኢንፎርማትክስ ኮሌጅ ላይ እንደተጀመረው ለተቀሩት ኮሌጅ መምህራንና ተማሪዎች በሲስተም አጠቃቀም ላይ ስልጠና እንደሚሰጥ እንዲሁም ሌሎች ኮሌጆች እንደ ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ አረያነቱን በመከተል ተማሪዎቻቸዉን ለመውጫ ፈተና በማዘጋጀት ብቁ እንዲሆኑ በማድረግ እንዲያግዟቸዉ እኛም እንደ ICT ዳይሬክቶሬት የበኩላችን የምንወጣ መሆኑን የICT ባለሙያ የሆኑት አቶ ቴሶ ዲዶ ገልጿል።
ለላቀ ለዉጥ እንተጋለን
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ