Get Mystery Box with random crypto!

ታህሳስ 21/2015 በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ ዙር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰ | Bule Hora University

ታህሳስ 21/2015
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ ዙር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ።

ታህሳስ 18 ቀን 2015ዓ.ም የተጀመረው የ2ኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተና በተለያዩ ምክኒያቶች ሳይፈተኑ የቆዩ ወንድ 2682 እን ሴት 1344 በድምሩ 4026 ተማሪዋች ፈተናውን በሰላም አጠናቀዋል።
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሰራተኛና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሮባ ደንቢ እንደተናገሩት በተለያዩ አካላት አስተባባሪነት በአራት ቀናት ውስጥ ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቅ እንደተቻለ የገለፁ ሲሆን የፈተናው አጠቃላይ አስተባባሪም አቶ አሸናፊ አበበ እንደገለፁት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛና ታችኛው አመራሮች ትብብር በተሳካ ሁኔታ ፈተናው መጠናቀቁን ገልፀዋል።
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
ለላቀ ለውጥ እንተጋለን!!