Get Mystery Box with random crypto!

ታህሳስ 21/2015 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በምርምር ውጤቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳድሮ 2ኛ ለወጣ | Bule Hora University

ታህሳስ 21/2015
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በምርምር ውጤቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳድሮ 2ኛ ለወጣው መምህር እውቅና ሰጠ።
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ መምህር የሆኑት መ/ር ጋናሌ ከድር በሀገር አቀፍ ደረጃ በምርምር ውጤቱ ተወዳድረው ሁለተኛ ደረጃም ከማግኘት አልፎ የዩኒቨርሲቲውንም ስም በማስጠራቱ ፣ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ እውቅና ሰጥቶታል።
መምህሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁለተኝነት አሸናፊ የሆነው “AGRICULTURAL TECHNOLOGY ADOPTION AND ITS IMPACT ON YIELD AND FARM INCOME: EVIDENCE FROM HARICOT BEAN PRODUCTION IN GUJI ZONE” በሚል ርዕስ ባደረጉት ጥናት ነው።
መምህር ጋናሌ ከድር በበኩሉ ከዩኒቨርሲቲው የተሰጠው እውቅና በጣም እንዳስደሰተው እና ይህ ሽልማት ለተሻለ የምርምር ሥራ ውስጥ እንድገባ የሚያደርግ ነው በማለት ደስታውን ገልጾዋል።
የእውቅና ሰርተፍኬቱን ያበረከቱት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታምሩ አኖሌ ሌሎች መምህራንም ጠንክራችሁ በመስራት እንድህ አይነት የሚያኮራ ስራ ልትሰሩ ይገባልም ብለዋል።
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲው
ለላቀ ለውጥ እንተጋለን!