Get Mystery Box with random crypto!

ቀን 05/01/2015 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው ቬንዳ ዩኒቨርሲቲ (Universi | Bule Hora University

ቀን 05/01/2015
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው ቬንዳ ዩኒቨርሲቲ (University of Venda) ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራረመ::

ስምምነቱ ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ በደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው ቬንዳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለመስራት የታሰበ ነው:: የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲቱዩት ኤክስኩትቭ ቺፍ ዳይሬክተር መ/ር ታከለ ኡቱራ እና ዶ/ር እያሱ ጌቱ በደቡብ አፍሪካ ቬንዳ ዩንቨርስቲ ቡሌ ሆራ ዩንቨርስቲን በመወከል የተገኙ ሲሆን አንባሳደር አንድሬ ዛፓይኬ (Andre Nzapayeke) የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ አምባሳደር የሆኑ እና ዶ/ር ደንዱለኒ በርናርድ (D/r Ndanduleni Bernard) የቬንዳ ዩኒቨርሲቲ ፒረዚዳንት ደግሞ ቬንዳ ዩኒቨርሲቲን ወክለው ስምምነቱን የፈረሙ ናቸው::
የሁለትዮሽ ስምምነቱ 12(አስራሁለት) አንቀፆች ያሉት ሲሆን በሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ለሚኖረው ተቋማዊ የስራ ትግበራ የላቀ ጠቀሜታ እንዳለው ተገልጿል:: በመማር ማስተማር፣ በጥናትና ምርምር ፣ በማህበረሰብ አግልግሎት እንዲሁም በጥናታዊ ፅሁፎች ህትመት እና ውጤት ተጠቃሚነት ዙሪያ ላይ ዩኒቨርሲቲዎቹ ስምምነትን አካሂደዋል።

ይህ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ እና በደቡብ አፍሪካው ቬንዳ ዩኒቨርሲቲ መካከል የተደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ የተቋማዊ ትስስር እና የአለም አቀፍዊነት አቅሙን እንዲያሳድግ የላቀ ጠቀሜታ አለው።
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
ለላቀ ለውጥ እንተጋለን!