2023-03-29 23:19:08
ብትመጣም ……
ባትመጣም ……
እስካለህ ሸንግለኝ እስካለህ ደልለኝ
ትመጣለህ ስልህ “አዎ እመጣለው”በለኝ
ብትክደኝ እንኳ አንተን ለመጠበቅ መኖሬን አትርሳ ለጥያቄዬ መልስን መቅረትን አታንሳ
“ረሳውሽ”እንዳትል ብትረሳኝ ባትረሳኝ
ሳቅ ያበደረኝን ተስፋዬን አትንሳኝ
እኔ ምን ቸገረኝ ብትቀር ባትቀር
ብቻ ግን አደራ “ተይኝ”እንዳትለኝ ከጠብቂኝ በቀር
ከእልፍ ህመም መሃል……
ነገን እንድናፍቅ ልቤን ተስፋ አክሞት
ብትመጣም ባትመጣም……
እመጣለው በለኝ እየሳኩ እንድሞት
https://t.me/BrocknHearts
808 views~Unforgettable~, edited 20:19