Get Mystery Box with random crypto!

በደባርቅ ከተማ 16 ሰርጎ ገቦች ተያዙ የደባርቅ ከተማ አሥተዳደር በምሽት የኬላ ጥበቃ 16 የአሸ | ሰበር ዜና

በደባርቅ ከተማ 16 ሰርጎ ገቦች ተያዙ

የደባርቅ ከተማ አሥተዳደር በምሽት የኬላ ጥበቃ 16 የአሸባሪው የህወሓት ቡድን አባላት የሆኑ ሰርጎ ገቦችን በቁጥጥር ስር አውሏል።**

የአሸባሪው ህወሓት ቡድን እኩይ ዓላማ ለማስፈፀም በተለያየ ምክንያት ወደ ከተማዋ ገብተው እየተንቀሳቀሱ የመረጃ ማቀበል ሥራ የሚሠሩ 16 ተጠርጣሪ ሰርጎ ገቦች እና ሶስት ህገ-ወጥ መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደባርቅ ከተማ ከንቲባ ብርሃን ፀጋየ ገልፀዋል።

የአሸባሪው ቡድን ለመከላከል በሚደረግ ዘመቻ የመጀመሪያው ተግባር የከተማችን ከሰርጎ ገብ መጠበቅ እና የደጀንነት ሚና መወጣት ዋነኛ እና ቁልፍ ተግባር መሆኑ ታውቆ በአደረጃጀት ስምሪት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ከንቲባው ተናግረዋል።

Via:- EBC
@BreakingNewsEthiopiaa