Get Mystery Box with random crypto!

' ትልቅ የሄግል ተጽዕኖ ያረፈበት ማርክስ ከሄግል የወረሰውን የታሪክ አረዳድ ከራሱ materiali | ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

"
ትልቅ የሄግል ተጽዕኖ ያረፈበት ማርክስ ከሄግል የወረሰውን የታሪክ አረዳድ ከራሱ materialism ጋር አዋህዶ እና አዋድዶ ይህንን የመሰለ የታሪክ አረዳድ ቀመረ። ይህ ለኮሙኒዝም ፍልስፍናው መሠረት የሆነው የማርክስ የታሪክ አረዳድ historical materialism ይሰኛል።
"
ብዙ ጊዜ «ካፒታሊዝም ነጻ ገበያ ነው፤ ነጻነት ላይ የተመሰረተ ነው» ሲባል እንሰማለን። ሄግል የዳበረ የነጻነት ፍልስፍና አለው፤ ነገር ግን የነጻነት ፍልስፍናው ከካፒታሊቶች የነጻነት ብያኔ ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም። ማርክስም የሄግልን የነጻነት ፍልስፍና ይከተላል። የሄግል የነጻነት ፍልስፍና መነሻው የታላቁ ፈላስፋ የኢማኑኤል ካንት ፍልስፍና ነው።"

ዘርዓያዕቆብ የፍልስፍና ት/ቤት