Get Mystery Box with random crypto!

ማርክሲዝም በአጭሩ ============= ክፍል 1: የሄግል የታሪክ አረዳድ ማርክስ ላይ ያሳደረው | ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ማርክሲዝም በአጭሩ
=============
ክፍል 1: የሄግል የታሪክ አረዳድ ማርክስ ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ
* Dialectic of history
=================
Biruk Mesfin
============
የፈላስፎችን ሀሳብ፣ በተለይ ደግሞ የcontinental ፈላስፎችን ሀሳብ ለመረዳት በጊዜያቸው የነበረውን ገዢ ፍልስፍና መረዳት ቁልፍ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም አብዛኛው ፍልስፍናቸው በጊዜአቸው ከነበረው ገዢ ፍልስፍና ጋር በሚደረግ ግጭትና ፍጭት የሚወለድ ነው። በማርክስ ዘመን የነበረው ገዢ ፍልስፍና የሄግል ፍልስፍና ነው። ማርክስ ራሱ በአንድ ወቅት ሄግሊያን ነበር። በኋላ idealistic ከሆነው የሄግል ፍልስፍና ወደ materialism በማዘንበል ከወጣት ሄግሊያንስ ማህጋር ራሱን አገለለ። ሆኖም የሄግልን ፍልስፍና መሉ በሙሉ ጠቅልሎ አልተወም።
"
ስለዚህ ሄግልን ቃኘት አድርገን እንመለስ። የሄግል ፍልስፍና ከውስብስብነቱም በላይ እጅግ ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ ለመረዳት አዳጋች ነው። ስለዚህ ከፍልስፍናዎቹ መሀል ከማርክስ ፍልስፍና ጋር የሚያያዙትን ክፍሎች ብቻ ነጥለን በጥቂቱ እንመለከታለን።
"
ማርክስን እና ሄግልን ከሚያመሳስሏቸው ወሳኝ ጉዳዮች አንዱ ለታሪክ የሚሰጡት አጽንኦት ነው። ለሄግል ታሪክ የራሱ የሆነ ግብ እና ትርጉም ያለው ምክንያታዊ ሂደት(process) ነው፤ ትርጉም አልባ የሆነ የክስተቶች ጥርቅም አይደለም። ለአንድ የዚህ ዘመን ኢአማኒ ታሪክ ማለት ባለፉት ዘመናት የኖሩ ሰዎች የሰሯቸው ስራዎችና ክስተቶች ጥርቅም ከመሆን ያለፈ ትርጉም ላይኖረው ይችላል። ለአንድ ክርስቲያን አማኝ ግን ታሪክ ማለት ጅማሬው፣ ሂደቱ እና ፍጻሜው በአምላክ ቁጥጥር ስር ያለ፣ ግብ አላማ እና ትርጉም ያለው ነገር ነው። “በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው የእግዚአብሔር ሀሳብ በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።” እንዲል መጽሐፉ።
"
የሄግል የታሪክ እይታም ከክርስቲያኖቹ ጋር ይመሳሰላል። ነገር ግን ታሪክ ትርጉም አልባ ስላለመሆኑ ያላቸው አቋም ነው የሚያመሳስላቸው። በዝርዝሩ ይለያያሉ። ሄግል የታሪክን ጅማሬ፣ ሂደት፣ ፍጻሜ እና ግብ የሚቆጣጠረው ከአለም የተነጠለ የራሱ ኑባሬ ያለው አምላክ ነው የሚል አቋም የለውም።
"
በምን መሠረት ነው ታድያ ሄግል ታሪክ ትርጉምና ግብ ያለው ሂደት ነው የሚለው? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። ተገቢ ጥያቄ ነው። ነገር ግን ይህንን ጥያቄ በሙላት መመለስ ውስብስብ የሆነውን የሄግል ፍልስፍና በስፋት መተንተንን የሚጠይቅ ይመስለኛል፤ ስለዚህ ከያዝነው ርዕስ ጋር ተያያዥነት ያለውን ክፍል ብቻ መዝዘን እንመልከት።
"
በምን መሠረት ነው ታሪክ ትርጉምና ግብ ያለው ሂደት ነው የሚሆነው? ታሪክ ወደ ግቡ የሚያደርገውን ጉዙ የሚቃኘው እና የሚገዛው ሀይል ምንድነው? ለዚህ ጥያቄ 'dialectic of history' የተሰኘው የሄግል ፍልስፍና መልስ ይሰጣል። dialectic of history ውስጥ thesis, antithesis እና synthesis የተሰኙ ሶስት ቁልፍ ሀሳቦች አሉ።
"
ይህንን ትንሽ አስቸጋሪ የሆነ ሀሳብ በቀላሉ ለማስረዳት ያህል፦ Thesis ማለት አንድ ጭብጥ ነው፤ antithesis ደግሞ ከዚህ ጭብጥ ጋር የሚቃረን ሌላ ጭብጥ ነው፤ synthesis ማለት በthesis እና antithesis ተቃርኖ የሚወለድ አዲስ ጭብጥ ነው፤ synthesisም በተራው thesis ይሆንና ሌላ antithesis ይነሳበታል፤ ከዚያም ሌላ synthesis ይወለዳል። በዚህ ሁኔታ ሀሳብ ወደ ፊት ይጓዛል።
"
የታሪክን ሂደት ወይም ጉዞ ከጀርባው ሆኖ የሚዘውረው ሀይል ይህ thesis, antithesis and synthesis የተሰኘ የሀሳብ ኡደት ነው ይላል ሄግል፤ ከቅድመ ታሪክ ጀመሮ እርሱ እስከኖረበት ዘመን ድረስ የተከሰቱ ዋነኛ የአለም ታሪኮችን አንድ በአንድ አጣቅሶ ይህንን ሀሳቡን ለማስረገጥ ይሞክራል፤ ታሪክ ከጊዜ ጊዜ እንዴት እየተሻሻለ እና ወደ ግቡ እየቀረበ እንደመጣ ያሳያል። ሄግልን ማንበብ ከፍልስፍና ባለፈ ታሪክንም ማንበብ ነው የሚባለው ለዚህ ነው።
"
የታሪክን ሂደት ወይም ጉዙ ከጀርባው ሆኖ የሚዘውረው thesis, antithesis እና synthesis የተሰኘው የሀሳብ ኡደት እንደሆነ ተመልክተናል። ይህ የሀሳብ ኡዱት እንዴት ነው በዘመናት መካከል ባለማቋረጥ እያውጠነጠነ ሊቀጥል የቻለው? ይህንን የሀሳብ ሁደት በቋሚነት ከጀርባው ሆኖ የሚዘውረው ሀይል ምንድነው? ሀሳቦች ያለማቋረጥ እየተፋጩ፣ እየታደሱ እና ደግሞ እንደገና እየተፋጩ ወደፊት የሚቀጥሉ ከሆነ የሚያውጠነጥኑበት አንድ ቋሚ ጉዳይ አለ ማለት ነው፤ ይህ ጉዳይ ነጻነት ነው። የነጻነት ጥያቄ ነው ይህንን የሀሳብ ኡዱት በዘመናት መካከል ባለማቋረጥ እያውጠነጠነ ወደፊት እንዲቀጥል የሚያደርገው።
"
ሄግል ታሪክ ትርጉም እና ግብ ያለው ሂደት ወይም ጉዞ ነው የሚል አቋም እንዳለው ከላይ ተመልክተናል፤ ይህ የታሪክ ግብ ነጻነት ነው። ታሪክን ከጀርባው ሆኖ የሚዘውረው የሀሳብ ኡደት ታሪክን ወደ ነጻነት ነው የሚነዳው። የባርያ ንግድን ክላልኝ እያለ፣ ፊውዳሊዝምን ወግድልኝ እያለ፣ ፍጹም ነጻ ወደ ሆነ የማህበረሰብ ስርዓት ነው ታሪክ የሚያንደረድረው። ይህ የሄግል ሀሳብ dialectic of history ይሰኛል። ነጻ የሆነ ማህበረሰብ ምን አይነት ነው ለሚለው ጥያቄ የሄግል መልስ የምትጠብቁት አይነት ላይሆን ይችላል። በዚህ ጉዳይ ማርክስም ከሄግል ጋር ተቀራራቢ አቋም አለው።"

ማርክሲዝም በአጭሩ
==============
ክፍል 2: ሄግላዊ የማርክስ የታሪክ አረዳድ Historical Materialism
"
Biruk Mesfin
===========
ክፍል 1 ላይ ሄግል «ታሪክ ግብ እና ትርጉም ያለው ሂደት ነው፤ ግቡም ነጻነት ነው።» የሚል አቋም እንዳለው ተመልክተናል። የማርክስም የታሪክ አረዳድ ከሄግል የተቀዳ ነው፤ ሆኖም ማርክስ materialist፣ ሄግል ደግሞ idealist ስለሆኑ የታሪክ አረዳዳቸውም በዛው ልክ ይለያያል።
"
ሄግል «የታሪክን ጉዙ ከኋላው የሚዘውረው የሀሳብ ፍጭት ነው፤ የታሪክ ግብ ደግሞ ነጻነት ነው» የሚል አቋም ሲኖረው፣ ማርክስ ደግሞ «የታሪክን ጉዙ ከኋላው የሚዘውረው የማህበረሰብ የኢኮኖሚ ሁኔታ ነው፤ የታሪክ ግብ ደግሞ ኢኮኖሚያዊ ነጻነት ነው» ብሎ ይከራከራል።
"
ማርክስም ልክ እንደ ሄግል የራሱ የሆነ thesis, synthesis and antithesis አሉት። ለምሳሌ፣ ፊውዳሊዝም ጠቅላላውን ሀብት ለንጉሡ ሰጥቶ ሰፊውን ህዝብ ጭሰኛ የሚያደርግ ጨቋኝ ስርዐት ሲሆን፣ እንደ thesis ወሰዱት። በከበርቴው መደብ እና በሰፊው ህዝብ መሀል ባለው ሰፊ የኢኮኖሚ ልዩነት ምክንያት የሚፈጠረውን የተዛባ የኢኮኖሚ ሁኔታ ደግሞ እንደ antithesis ውሰዱት። በthesis እና በantithesis ግጭት ምክንያት የተወለደው ካፒታሊዝም ደግም synthesis ነው።
"
ካፒታሊዝም ደግሞ በተራው thesis ሆነ። ይህንን በዝባዥ ስርዐት ተቃውሞ የተነሳውና የብዝበዛው ሰለባ ሰራተኛው መደብ ደግሞ antithesis ነው። በthesis እና antithesis ተቃርኖ የሚወለደው communism ደግሞ synthesis ነው።