Get Mystery Box with random crypto!

አቅም ሲኖርህ የመደራደር አቅምህ ይጨምራል፡፡ የለመድነው ስኬታማ ወንድ እና submissive የሆነ | ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

አቅም ሲኖርህ የመደራደር አቅምህ ይጨምራል፡፡ የለመድነው ስኬታማ ወንድ እና submissive የሆነች ሴት ስለሆነ በድራማው ውስጥ የሴቷ ስኬታማ መሆን፣ ተደራድራ ጥቅሞቿን የምታስከብር ሴት መሆኗ፣ ኢፍትሃዊ የመሰላትን ነገር ለማስተካከል በመሞከሯ፣ ድምጿ ጎላ ብሎ የሚሰማ ሴት መሆኗ፣ ባሏን/ወንድን ለማኮሰስ ሆን ተብሎ የተሸረበ ሴራ ይመስለናል፡፡

ሂሩት የምትደነቅ፣ ባሏን የምትወድ፣ ልጆቿን የምትወድ፣ ቤተሰቧን የምትወድ ለፍቶ አዳሪ ሴት ናት፡፡ ልንረዳት የምፈልገው ግን እኔ ብቻ ያልኩት እንደምትል እንደ ጨቋኝ፣ ከመሬት ተነስታ ወንድን/ባሏን እንደማታከብር ስድ ሴት ነው፡፡ በስንቱንም ክብር እንዳጣ፣ እንደተበደለ፣ እንደተናቀ ሰው ልናየው አእንጣጣራለን፡፡

በብዙ ቤቶችና ትዳሮች፣ ከሴቷ በታች የሚሰራ ወንድ (የስራ ጫና ያለበት ወንድ)፣ ከሴቷ የተሻለ ትርፍ ሰአት ያለው ወንድ ቁጭ ብሎ ቲቪውን እያየ ሚስቱ ከስራ መጥታ ምግብ አስክትሰራ ይጠብቃል፡፡ ይሄ ሊቀፈን፣ ሊያንገሸግሸን ይገባል፡፡

በስንቱ ለኔ ምርጡ ድራማ ነው፡፡ እያዝናና፣ እያሳቀ፣ አንዳንዴም እያናደደም ቢሆን የጾታ እኩልነትን ለማስረጽ ምርጡ ድራማ ሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡

ዘመናዊው ትዳር፤ ሴቶች ሰራተኛ የሆኑበት ትዳር፤ የተማሩና የራሳቸው ገቢ ያላቸው ሴቶች ሚስት የሆኑበት ትዳር እንዴት መመራት እንዳለበትበት የሚያሳይ እንጂ ፤ ሴቶችን የሚክብ ወንዶችን የሚያዋርድ ነገር አይቼበት አላውቅም፡፡

Embet Teshome (comment)