Get Mystery Box with random crypto!

ባንካችን አቢሲንያ በአሰላ ከተማ የቨርችዋል ባንኪንግ ማዕከል አስመረቀ:: በሀገራችን ከሚገኙ ባን | Bank of Abyssinia

ባንካችን አቢሲንያ በአሰላ ከተማ የቨርችዋል ባንኪንግ ማዕከል አስመረቀ::

በሀገራችን ከሚገኙ ባንኮች በቴክኖሎጂ የታገዙ የባንክ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ቀዳሚ የሆነው ባንካችን በአሰላ ከተማ አይሻ ጊጊ ህንፃ ላይ የቨርችዋል ባንኪንግ ማዕከል አስመርቆ ሥራ አስጀምሯል።
በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የአሰላ ከተማ ከንቲባን ጨምሮ አባገዳዎች ፣ ሀደ ስንቄዎች ፣ የዲስትሪክት የስራ ሃላፊዎች እና የባንካችን ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን ማዕከሉ በአካባቢው ያለውን ማኅበረሰብ ከግምት በማስገባት 24/7 የባንከ አገልግሎት የሚሠጥ ማዕከል በመገንባት ተደራሽነቱንም በማስፋፋት በአካባቢው ለሚንቀሳቀሰው ማኅበረሠብ የተሻለ እና የተመረጠ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ።

በዚህም መሰረት ሀሙስ ጥር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. በአሰላ ከተማ የገነባውን ማዕከል አስመርቆ በይፋ አገልግሎት አስጀምሯል፡፡ ባንካችን በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች መሰል የቨርችዋል ባንኪንግ አገልግሎት በማስፋፋት ላይ ይገኛል፡፡