Get Mystery Box with random crypto!

ባንካችን አቢሲንያ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ጉባዔውን በማካሄድ ላይ ይገኛል። ጥር 23 ቀን | Bank of Abyssinia

ባንካችን አቢሲንያ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ጉባዔውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም የ2023/24 በጀት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል መካሄድ የጀመረው ጉባዔ የባንካችን የበላይ አመራሮች፣ የዲስትሪክት ኃላፊዎች እና የተለያዩ የሥራ ክፍል ሥራ አስኪያጆች የተሳተፉ ሲሆን፣ በጉባዔው መጀመሪያ ላይ የዲስትሪክቶች የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ የዲስትሪክት ኃላፊዎች ከጉባኤው ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጉባኤው ጥር 24 /2016 ለሁለተኛ ቀን የቀጠለ ሲሆን አጠቃላይ የባንካችንን የሥራ አፈፃፀም ምዘና፣ እንዲሁም ለቀጣይ ግማሽ ዓመት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል።