Get Mystery Box with random crypto!

Bisrat-Media - ብስራት ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ bisratmedia — Bisrat-Media - ብስራት ሚዲያ B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bisratmedia — Bisrat-Media - ብስራት ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @bisratmedia
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.65K
የሰርጥ መግለጫ

የዩቲዩብ ቻናሌን subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCaeqEXNxSDUhu7poziD8vAQ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-29 20:51:56
የለገዳዲና ድሬ ግድብ የ11ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እድሳት ሊደረግላቸው ነው።

የአዲስ አበባን የውሃ አቅርቦት 40 ከመቶ አካባቢ በመሸፈን ካለ በቂ ጥገና ሃምሳ ዓመታትን ያገለጠሉት የለገዳዲና ድሬ ግድቦች እድሳት ሥራ ሊከናወንላቸው መሆኑ ተገልጿል። የማሻሻያ እና የጥገና ስራዉ 18 ወራት የሚፈጅ ሲሆን በአለም ባንክ በተገኘ ብድር የሚከናወን ነው፡፡

እድሳቱ ሁለቱም ግድቦች አስቀድሞ በሰራቸው በሳሊኒ ኩባንያ የሚካሄድ ሲሆን የ11ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር (በወቅቱ ምንዛሪ 600 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ) ስምምነትም በዛሬው ዕለት ተፈጽሟል።

ለግማሽ ምእተ-ዓመት በማገልገል እርጅናና እየገጠመው ያለው የለገዳዲ ግድብ ስራ በሚደረግለት የጥገና እና የማሻሻያ ስራ የግድቦቹን እድሜ ለተጨማሪ 50 አመት ከማራዘም በተጨማሪ የለገዳዲን ውሃ የማምረት አቅም በቀን በ30ሺህ ሜትር ኪዩብ ከፍ የሚደርገው መሆኑም በስምምነቱ ወቅት ተጠቁሟል፡፡
50 views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 17:17:46
ሩሲያ ለኢትዮጵያ የ162 ሚሊዮን ዶላር ብድር እዳ ሰረዘች

ሩሲያ ለኢትዮጵያ 162 ሚሊዮን ዶላር ብድር መሰረዟን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ትናንት በሰጡት መግለጫ፤ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ከሩሲያ የተበደረችውን 162 ሚሊዮን ዶላር መሰረዙንና በብድር መልክ ሊከፈል የነበረው ገንዘብ ለምን አገልግሎት መዋል እንዳለበትም ሁለቱ ሀገራት ተስማምተዋልም ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለሩሲያ በብድር መልክ ልትከፍለው የነበረው 162 ሚሊዮን ዶላር ባልቻ ሆስፒታልን እና መልካ ዋከና የሀይል ማመንጫ ጣቢያ ለማዘመን እንዲውል መስማማታቸውም ተገልጿል።

ቃል አቀባዩ አቶምባሳደር መለስ በመግለጫቸው አክለውም፣ በኢትዮጵያ በህገወጥ መንገድ ይኖሩ የነበሩ የውጭ ሀገራት ዜጎች ምዝገባ መጀመሩን እና እስካሁን 60 ሺህ ሰዎች መመዝገባቸውን ተናግረዋል። በእስካሁኑ ምዝገባ የካናዳ፣ አሜሪካ፣ኮንጎ፣ ናይጀሪያ ፣ የመን፣ ሶሪያ፣ ኤርትራ ፣ሱዳን፣ቻይና፣ ቡሩንዲ ጋና፣ ህንድ፣ ባንግላዲሽ፣ ላይቤሪያ፣ ጣልያን እና የካሜሩን ዜግነት ያላቸው ህገወጥ ሰዎች መገኘታቸው ተገልጿል።
50 views14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ