Get Mystery Box with random crypto!

Bisrat-Media - ብስራት ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ bisratmedia — Bisrat-Media - ብስራት ሚዲያ B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bisratmedia — Bisrat-Media - ብስራት ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @bisratmedia
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.65K
የሰርጥ መግለጫ

የዩቲዩብ ቻናሌን subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCaeqEXNxSDUhu7poziD8vAQ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-02 19:49:44
በድሬዳዋ ታይዋን የገበያ አዳራሽ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ በመሸጫ ሱቆች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ ገለፀ።

ትላንት ምሽት ሀምሌ 25 ቀን 2014 ዓ/ም ከምሽቱ በ 3:30 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 07 ክልል በሚገኘው የታይዋን የገበያ አዳራሽ ለጊዜው ምክንያቱ ያልታወቀ የእሳት ቃጠሎ መከሰቱን የድሬዳዋ ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ፥ በቃጠሎውም ግምቱ ለግዜው ያልታወቀ ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ያለ ሲሆን ከድረሱት የንብረት ጉዳቶች ውስጥም በ5 የልብስ መደብሮች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን እንዲሁም አንድ የተለያዩ አልባሳት እና መገልገያ እቃዎች መሸጫ መደብር ሙሉ ለሙሉ መውደሙን አስታውቋል::

የእሳቱ ቃጠሎዉን ለመቆጣጠር የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የእሳት አደጋ አባላት ከቀጠናው የአፈተኢሳ ፖሊስ ጣቢያና የአድማ ብተና ፖሊስ እንዲሁም ከመላው ማህበረሰቡ ጋር በመሆን በሰጡት ፈጣን ምላሽ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ የተከሰተውን የእሳት ቃጠሎ ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር መቻሉንም ገልጿል::

የድሬደዋ ፖሊስ ጨምሮም እንዳስታወቀው በቀጣይ ግዜያት የእሳት ቃጠሎውን መንስዔና የደረሰውን የጉዳት መጠን አጣርቶ ይፋ እንደሚያደርግ ገልፆል።
43 views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 13:44:21
#Betking
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር የስፖርቱ ሚድያዎች በተገኙበት የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር እጣ የማውጣት ፕሮግራምን ዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 26/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 በፅ/ቤቱ አዳራሽ(ወንጌላዊት አካባቢ በሚገኘው ሜይስዊ ህንፃ 5ኛ ፎቅ) አከናውኗል።

የ15 ሳምንቱን መርሃ ግብር በምስሉ ላይ ተያይዟል።
44 views10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 16:39:44
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉዳይ አሳሳቢ ሆኖአል በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ አንድ ተማሪ በዚህ መልኩ ሞቶ ተገኝቷል ።

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለጓደኞቹ ፣መፅናናትን ፣ይመኛል ብስራት ሚዲያ

የብስራት ሚዲያ ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ። ባሉበት ሆነው ይከታተሉ
በዮቱብ
https://youtube.com/channel/UCaeqEXNxSDUhu7poziD8vAQ

በቴሌግራም:-https://t.me/BisratMedia
Telegram:-https://t.me/BisratMedia

በፌስቡክ
https://www.facebook.com/bisratmediatube
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ እናመሰግናለን ።
54 views13:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 20:27:56
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የአንድ መጋዘን ግንብ ተደርምሶ በሰው ህይወትና አካል እንዲሁም በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።


አደጋው የደረሰው ሐምሌ 24 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 9:30 ሰዓት ሲሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ክልል ልዩ ቦታው አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ ነው።

በመጋዘን ቤት ውስጥ ውሃ በመሙላቱ ግንቡ ተደርምሶ ከስር በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በነበሩ 3 ግለሰቦች ላይ ጉዳት በማድረስ የ1 ሰው ህይወት ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ሲያልፍ ፤ 2 ግለሰቦች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የመሳለሚያ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የዕለቱ ተረኛ መኮንን ምክትል ኮማንደር መዓዛ ገብረማርያም ገልፀዋል።

ኮማንደሯ አክለው እንዳስታወቁት በአፋጣኝ አደጋው በደረሰበት ቦታ በመሄድ ከሌሎች የፀጥታ አካላትና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች የማውጣትና ወደ ህክምና እንዲሄዱ የማድረግ እንዲሁም ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ሰዎችን ከአደጋው ቦታ የማሸሽ ስራዎች መሰራታቸውን ምክትል ኮማንደር መዓዛ አስረድተዋል።

ኃላፊዋ አያይዘው እንደተናገሩት ከክረምቱ ወቅት ጋር ተያይዞ ለአደጋ ስጋት የሆኑ ቦታዎችን በመለየት የሚመለከታቸው አካላት ጉዳት ከመድረሱ በፊት ትኩረት በመስጠት የመፍትሔ እርምጃዎችን መወሰድ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት የመጋዘኑ ግንብ ተደርምሶ በሰው ህይወትና በአካል ላይ ጉዳት በመድረሱ የተሰማቸውን ሃዘን ገልፀው ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ፖሊስ በፍጥነት ቦታው ላይ ደርሶ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የሰራውን ስራ አድንቀው ቀጣይም መጋዘኑ መፍትሔ ካልተበጀለት ስጋት እንደሆነባቸው ተናግረዋል።
61 views17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 08:21:44 "በአሸባሪው አልሸባብ ላይ የተወሰደው ዘመቻ ስኬታማ ነው" - የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር


ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን ያሉት በ6ኛው የሶማሌ ክልል ምክር ቤት 2ኛ ዓመት 3ኛ ዙር መደበኛ ስብሰባ የክልሉን መንግስት የ2014 ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል።

አሸባሪው ቡድን አልሸባብ የክልሉን ሰላምና ልማትን አደጋ ላይ ለመጣል አቅዶ የከፈተው የጥፋት እርምጃ የክልሉ ልዩ ኃይል በወሰደው ከፍተኛ የተቀናጀ እርምጃ የጥፋት ተልዕኮውን ማክሸፍና በሽብር ቡድኑ ላይም ከፍተኛ ኪሳራ ማድረሱን በሪፖርታቸው ገልፀዋል። በዚህም የመጀመሪያው ዙር ዘመቻ ስኬታማ መሆኑንና በቀጣይ የአካባቢውን ፀጥታው ለማጠናከር በቂ ዝግጅት እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በፍትህ ተቋማት በተያዘው አመት በ681 አቃብያነ ህጎች አሰራር ስነምግባር ላይ ግምገማ መደረጉንና የእርምት ውሳኔዎችም መሰጠታቸውን ገልጸዋል። በፖሊስና በማረምያ ተቋማት የታራሚን ሁኔታ አያያዝ መፈተሻቸውን የጠቀሱት አቶ ሙስጠፌ በዚህም ያለ በቂ ማስረጃ የታሰሩ 180 የሕግ ታራሚዎች መፈታታቸውን ገልፀዋል ።

ርዕሰ መስተዳድረሩ 224 ታራሚዎችን በምህረት መለቀቃቸውን ጠቅሰው በክስ ከታዩ 3 ሺህ 58 የምርመራ መዝገቦች ውስጥ 2 ሺህ756ቱ ውሳኔ ማግኘታቸውንና 302 ቱበሒደት ላይ መሆናቸውን ተናግለዋል። በጤናው ዘርፍ እና በድርቁ የቤት ዕንስሳትን ለመታደግ የተሰሩ ስራዎችንም በሪፖርታቸው ለምክር ቤቱ ማቅረባቸውን ከሶመብኤ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
56 views05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 06:46:47
በደቡብ ክልል የሚገኙት የወላይታ፣ ጌዲኦ፣ ጋሞ፣ የደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች አዲስ በሚቋቋም ክልል በአንድ ላይ ለመደራጀት በምክር ቤቶቻቸው ውሳኔዎችን አሳለፉ።

የአማሮ እና ባስኬቶ ልዩ ወረዳዎችም በምክር ቤቶቻቸው ተመሳሳይ ውሳኔ አጽድቀዋል።

በሌላ በኩል የሀድያ፣ ሀላባ እና ከምባታ ጠምባሮ ዞኖች እንዲሁም የየም ልዩ ወረዳ ምክር ቤት ከሌሎች ሁለት ዞኖች ጋር በመሆን አንድ የጋራ ክልል ለመመስረት ወስነዋል።

Via :- Ethiopia Insiders
56 views03:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 14:30:21 የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የአፍሪካ ስመጥር ዋና ስራ አስፈጻሚዎች ሽልማትን አሸነፉ

ዘ ቢዝነስ ኤግዚኪዩቲቭ የተሰኘ በጋና የሚገኝ የፓን ዌስት አፍሪካ ሚዲያ በሞሪሽየስ ባዘጋጀው የ2022 የአፍሪካ ስመጥር ዋና ስራ አስፈጻሚዎች ሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ በቴሌኮሚኒኬሽን ዘርፍ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የ2022 የአፍሪካ ስመጥር ዋና ስራ አስፈጻሚዎች ሽልማትን አሸንፈዋል።
57 views11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 14:14:37
በአዲስ አበባ ከ11ሺ በላይ የክላሽ፣ ከ6ሺ በላይ የሽጉጥ ጥይት እና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ!

ሦስት የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች ሁለት ተሽከርካሪዎችን ተጠቅመው ሲያዘዋውሩት የተገኘ ከ11ሺ በላይ የክላሽ፣ ከ6ሺ በላይ የሽጉጥ ጥይት እና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው ሃና ማርያም አካባቢ ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ላይ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2-69099 አ/አ ቶዮታ ተሽከርካሪ ብዛቱ 
6ሺ 494 የሽጉጥ ፣
11ሺ 275 የክላሽ ጥይት ፣
የ11 የተለያዩ መሳሪያዎች ጥይት ፣
በባለሙያ የተፈታቱ 9 የብሬን ሰደፍ ፣
4 የብሬን ተመላላሽ ሽቦ ፣
6 የብሬን ተመላላሽ ዘንግ፣
ልዩልዩ የክላሽ ኮቭ ጠብመንጃ አካሎች ፣ዝናር
ብዛቱ 37 የሽጉጥ ካርታ ከሌሎች የጦር መሳሪያዎች ጋር እንዲሁም በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-B-01563 አ/አ ቶዮታ ሎንግ ቤዝ በሆነ ተሽከርካሪ 465 የስታር ሽጉጥ ጥይት እና 1 ኢኮልፒ ሽጉጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረጉት ክትትል መያዛቸውን የአዲስ አበባፓሊስ አስታውቋል፡፡

ከሁለቱ ተሽከርካሪዎች 11ሺ275 የክላሽ እና 6ሺ 959 የሽጉጥ ጥቶችን ከልዩ ልዩ ጦር መሳሪያዎች ጋር መገኘቱ ታውቋል ፡፡ የጦር መሳሪያዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙት ሶስት ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራው ተጠናክሮ መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል ፡፡
59 views11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 20:53:40
ሰበርዜና!
የአልሻባብ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ኃላፊን ፏአድ መሐመድ ከሌፍ (ሼንጎሌ) ጨምሮ ሶስት የቡድኑ አመራሮች ተደመሰሱ!!

የአልሻባብ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ኃላፊን ፏአድ መሐመድ ከሌፍ (ሼንጎሌ) ጨምሮ ሶስት የቡድኑ አመራሮች መደምሰሳቸውን የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድፖስት አስተባባሪ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ተናገሩ።

ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ እንደተናገሩት፤ ባለፉት ቀናት ከኢፌዴሪ አየር ኃይል ጋር በመቀናጀት በተወሰደው ርምጃ የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ያዘጋጃቸውን የትጥቅና ስንቅ ዴፖዎች ማውደም ተችሏል፡፡

በተጨማሪም የአሸባሪ ቡድኑ አመራሮችና ታጣቂዎች በተወሰደው ርምጃ ተደምስሰዋል። ከተደመሰሱት ውስጥ የአልሸባብ ከፍተኛ ኮማንደሮች ውስጥ:-

1. ፏአድ መሐመድ ከለፍ (ሼንጎሌ) የአልሸባብ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ሃላፊ፣

2.አብዱላዚዝ አቡ ሙሳ የአልሸባብ ቃል አቀባይ፣

3.ኡቤዳ ኑር ኢሴ የአልሸባብ የቦኮል ዞንና የኢትዮጵያ ድንበሮች አዋሳኝ ሃላፊ መደምሰሳቸውን ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
68 views17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 20:52:33
ከሰኔ 29/2014 ዓ.ም ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ አሠራር በተመሳሳይ በነሃሴ ወር 2014 ዓ.ም እንደሚቀጥል ተገለጸ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከሐምሌ 23/2014 ዓ.ም እስከ ነሃሴ 30/2014 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ የሚሆን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ክለሳን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

በዚህም ከሰኔ 29/2014 ዓ.ም ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ አሠራር በተመሳሳይ በነሃሴ ወር 2014 ዓ.ም እንደሚቀጥል ለዋልታ በላከው መግለጫ ገልጿል።

በነሃሴ ወር 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ በሐምሌ ወር 2014 ዓ.ም እየተሸጠበት ባለው ዋጋ ያለምንም ለውጥ የሚቀጥል ሲሆን፤ ነገር ግን የአውሮፕላን ነዳጅን በሚመለከት በወቅታዊ የዓለም አቀፍ ዋጋ ተሰልቶ በመጣው አዲስ አበባ ላይ በሊትር 84 ብር ከ42 ሳ እንዲሸጥ የተወሰነ መሆኑን አስታውቋ
54 views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ