Get Mystery Box with random crypto!

የለገዳዲና ድሬ ግድብ የ11ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እድሳት ሊደረግላቸው ነው። የአዲስ አበባን የው | Bisrat-Media - ብስራት ሚዲያ

የለገዳዲና ድሬ ግድብ የ11ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እድሳት ሊደረግላቸው ነው።

የአዲስ አበባን የውሃ አቅርቦት 40 ከመቶ አካባቢ በመሸፈን ካለ በቂ ጥገና ሃምሳ ዓመታትን ያገለጠሉት የለገዳዲና ድሬ ግድቦች እድሳት ሥራ ሊከናወንላቸው መሆኑ ተገልጿል። የማሻሻያ እና የጥገና ስራዉ 18 ወራት የሚፈጅ ሲሆን በአለም ባንክ በተገኘ ብድር የሚከናወን ነው፡፡

እድሳቱ ሁለቱም ግድቦች አስቀድሞ በሰራቸው በሳሊኒ ኩባንያ የሚካሄድ ሲሆን የ11ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር (በወቅቱ ምንዛሪ 600 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ) ስምምነትም በዛሬው ዕለት ተፈጽሟል።

ለግማሽ ምእተ-ዓመት በማገልገል እርጅናና እየገጠመው ያለው የለገዳዲ ግድብ ስራ በሚደረግለት የጥገና እና የማሻሻያ ስራ የግድቦቹን እድሜ ለተጨማሪ 50 አመት ከማራዘም በተጨማሪ የለገዳዲን ውሃ የማምረት አቅም በቀን በ30ሺህ ሜትር ኪዩብ ከፍ የሚደርገው መሆኑም በስምምነቱ ወቅት ተጠቁሟል፡፡