Get Mystery Box with random crypto!

ጾመ ሐዋርያት ጾመ ሐዋርያት ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው በመላው ዓለም ተዘዋውረው | ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

ጾመ ሐዋርያት

ጾመ ሐዋርያት ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው በመላው ዓለም ተዘዋውረው ወንጌልን ከመስበካቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡ ጾመ ድኅነት ደግሞ ስያሜው እንደሚያመለክተው ‹የመዳን ጾም› ማለት ሲሆን ይህም በብሉይ ኪዳኑ አጽዋማት በጾመ አስቴር እና በጾመ ዮዲት የተተካ የሐዲስ ኪዳን ጾም ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን በሐማ ምክንያት በእስራኤል ላይ ታውጆ የነበረው ሞት በጾመ አስቴር እንደ ተሻረ ሁሉ በሐዲስ ኪዳንም በዕለተ ረቡዕ በጌታችን ላይ በተፈጸመው ምክር የሰይጣን ሴራ ፈርሷልና በጾመ አስቴር ምትክ ረቡዕን እንጾማለን፡

በዘንድሮ ዓመት ጾመ ሐዋርያት ሰኔ ፮፣ ጾመ ድኅነት ደግሞ ሰኔ ፰ ቀን ይጀመራሉ፡፡ በመሆኑም ‹ይሄ ቄሶች ወይም መነኰሳት የሚጾሙት ጾም ነው› የሚል ሰበብ ሳንፈጥር ሁላችንም በአንድነት ብንጾማቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቅርታ፣ ጸጋና ምሕረትን እናገኛለንና ራሳችንን ለጾም አዘጋጅተን እንጹም!
እንኳን አደረሳችሁ !