Get Mystery Box with random crypto!

H~M~B: #የተነሳው_እሳት_አሁንም_እየከበደ ነው .......... #የዛሬ_ውሎ በታላቁ በአሰቦት | እለታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ

H~M~B:
#የተነሳው_እሳት_አሁንም_እየከበደ ነው
..........
#የዛሬ_ውሎ በታላቁ በአሰቦት ደብረ ወገግ ገዳም።
...........
#የእሳቱ_ፍጥነት አሁንም በተለያየ አቅጣጫ ከመነገረው በላይ እየጨመረ ነው። በታኛው እሁዳድ በአርምሞ ላይ (ዘግተው የነበሩ) አባቶች ከበአታቸው ተሰደው ከአንድነት ገዳሙ መነኮሳት ጋር ተቀላቅለዋል።

ረፋድ 6:00 አካባቢ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ወደ ገዳሙ መጥቶ የነቀረው እሳት የኔታ መርዓዊ ቤታ ጋር ሲደርስ በቁጥጥር ውሏል።

#ነገር_ግን ትኩረት

1ኛ በልዩ ስሙ #በተክለ አረጋዊ የተነሳው እሳት አሞራ ገደል የሚባለው ቦታ ከፍተኛ ገደል ውስጥ ስለገባ በሰው ሃይል ማጥፋት የማይቻልበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህ አካባቢ ሺ አመታትን ያስቆጠሩ የስውራን መጠለያ እንደ #ዝግባ #ጥድ #ወይራ ያሉ ዛፎች ያሉበት ቦታ ነው።

2ኛ በልዩ ስሙ #መስቀል በሚባለው ቦታ ያለው እሳትም ወደ ገዳሙ እንዳይመጣ መቁጣጠር ቢቻልም ነገር ግን ስፍራ እየቀያየረ፣ ገደላማ አካባቢ እየገባ ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር አልተቻለም።

3ኛ #በዴሪ አድርጎ #መንዲሳ ወንዝ ውስጥ የገባው እሳት ከሁሉም በባሰ ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል። በሂሊኮፕተር ካልሆነ በሰው ሃይል ከባድ ነው።

#መውጫ_ሀሳብ:- ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ዝም ያለው አካል ከተኛበት እንዲነቃ #ከደንነት በአንዴ ወደ ምድረበዳነት እየተቀየረ ያለውን፣ እንደ #ዝግባ #ጥድ #ወይራ ያሉ ሺ አመታትን ያስቆጠሩ እጽዋት ታሪክ ሆነው ሳይቀሩ በሂሊኮፍተር በውሃ ካልሆነ ማጥፋት ስለማይቻል ሂሊኮፍተር እንዲላክ በቻላችሁት መንገድ ሁሉ #ስለ_ገዳሙ ጩኹ ! ድምጻችሁን አሰሙ የሚወጡ መረጃዎችን አይታችሉ አትለፉ #share አድርጉ። ወደ ገዳሙ ያልመጣችሁ ወጣቶች ተደራጁ ለመምጣትና ለማገዝ ተዘጋጁ።

#Share በማድረግ #ለገዳሙ ድምጽ #ይሁኑ!

መምህር ኤፍሬም ዘደብረ ወገግ
0917 55 96 69