Get Mystery Box with random crypto!

_ ፳፭) እብድ ማግባት አይገባውም። _ ፳፮) አካላትን የሚቆራርጥ ደ | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

_
፳፭) እብድ ማግባት አይገባውም።
_
፳፮) አካላትን የሚቆራርጥ ደዌ ሥጋ ያለባቸው ሰዎች ማግባት አይገባቸውም።
_
፳፯) ስትሰስን ተገኝታ የተፈታችውን ሴት ንስሓ መግባቷ እስኪታወቅ ድረስ፣ ጎረቤቶቿ መመለሷን እስኪመሰክሩላት ድረስ። ከተመሰከረለት በኋላ ፍትሐት ዘወልድ ተደግሞላት ታግባ።
_
፳፰) ሚስት ባሏ ከሞተ ከ፲ ወር በፊት ሌላ ማግባት አይገባትም። በዚህ በ፲ ወር ውስጥ መተጫጨት ግን ይቻላል።
_
፳፱) ከሐፃኒ ከመጋቢ በታች ያለ ሕፃን ሐፃኒ መጋቢ ሳይፈቅድለት ማጨት አይገባውም። በባልና በሚስት ፈቃድ ነው እንጂ ያለሁለቱ ፈቃድ ጋብቻ አይጸናም አይፈጸምም።
_
፴) አካለ መጠን ያልደረሰችን ሴት ማግባት አይገባም። ከመተጫጨት ግን አይከለክልም።
_
፴፩) ያጨ ሙሽራ ማጫ ከሰጠ በኋላ ሊመነኩስ ቢወድ ለሙሽራይቱ የሰጠውን ማጫ መቀበል ይገባዋል።
_
፴፪) ለማግባት አስቀድሞ መተጫጨትና ቃል መጋባት በፍጹም ምክር በፍጹም ፈቃድ ይፈጸም ዘንድ ነው። መልኩን ግብሩን ጸባዩን አጥንቱን ለመመርመር ነው። ለሠርግ የሚያስፈልገውን ለማዘጋጀት ነው።
_
፴፫) ባልና ሚስት እርሱም ሌላይቱን እርሷም ሌላውን ሳያውቁ የተጋቡ እንደሆነ ፍቅር ይጸናል።
_
፴፬) መነኵሴን ማግባት አይገባም። ከስልሳ ዓመት በላይ የሆናትን ሴት ማግባትም አይገባም።
_
፴፭) ማጨት ቃል ኪዳን መጋባት ነው። ከጋብቻ አስቀድሞ የሚሆን አለኝታ ነው። በደብዳቤም ያለ ደብዳቤም ይሆናል። በእጮኝነት ጊዜ ካህናት እጅ ለእጅ አያይዘው፣ አንድ የሚያደርጋቸውን መስቀል አስጨብጠው፣ አንድ ቀለበት አድርገው በደብዳቤ ይወስኑላቸው።
_
፴፮) ያለ ትልወት፣ ያለ ማጫ ማግባትም ይገባል [ይቻላል]።
_
፴፯) ሰባት ዓመት ላልሞላው ሕፃን ማጨት አይገባም።
_
፴፰) አጭቶ ለማግባት ቀን ያልወሰነ ሰው በሀገር ያለ ቢሆን ሁለት ዓመት ይጠብቁት። ሩቅ ሀገር የሄደ ቢሆን ሦስት ዓመት መጠበቅ ይገባል። በታወቀ ምክንያት የቀረ ቢሆን አራት ዓመት መጠበቅ ይገባል። ከዚህ ያለፈ ቢሆን ግን ለሌላ ማጋባት ይገባል።
_
፴፱) በፈቃዷ የምትኖር ሴት የፈለገችውን መርጣ ማግባት ትችላለች። በእናት በአባቷ ቤት ያለች ከሆነች ግን በቤተሰቦቿ ፈቃድ ይሁን።
_
፵) የሚጋቡ ሰዎች አካለ መጠን ያላደረሱ እናት አባት አሳዳጊ የሌላቸው ድኆች ቢሆኑ ፲፭ ዓመት እስኪሆናቸው ይጠብቁ። ከዚያ የፈቀዱትን ያድርጉ።
_
፵፩) አንዲትን ሴት ከታጨች በኋላ ሌላ ወንበዴ አስገድዶ ቢደፍራት እና ያጫት አልቀጥልም ካለ አስገድዶ የደፈራት ሚስት የሌለው ከሆነ ከወደደችው ሊያገባት ይገባል።
_
፵፪) ወንዶች ፈጽመው አካለ መጠን የሚያደርሱበት 20 ዓመት ነው። ይህም ባይሆን 25 ዓመት ነው። ሴቶች ደግሞ 12 ዓመት ነው። ይህም ባይሆን 15 ዓመት ነው።
_
፵፫) ከተጫጩ በኋላ የአንደኛው ግብሩ ጠባዩ የከፋ መሆኑን ተረድቶ እምቢ ቢል ይችላል። እምቢ ያለች ሴቲቱ ከሆነች ዓረቦኑን እጥፍ አድርጋ ትመልሳለች። ከሰጠ በኋላ አላገባም ያለ ወንዱ ከሆነ ዓረቦኑ ይቀርበታል።
_
፵፬) ልጁ በንጽሕና እኖራለሁ ካለ አባት ግድ አግባ ማለት አይገባውም።
_
፵፭) 25 ዓመት በላይ የሆናት ሴት ብትኖር አባት እናቷ ከማጋባት ቸል ቢሏት እርሷ ወደ ዳኞች አቤት ማለት ይገባታል። ራሷን የቻለች ከሆነች ግን ራሷ ማግባት ይገባታል።
_
፵፮) ጋብቻ ያለቁርባን አይጸናም።
_
፵፯) ለተጋቢዎች አንድ ልብስ ያለብሷቸዋል፣ ከጣታቸው አንድ ቀለበት ያገቡላቸዋል ጠባብ ከሆነ ፊት እርሱ አግብቶ ለእርሷ ይሰጣታል፣ አንድ መስቀል ያስጨብጧቸዋል። አንድ ዘውድ ይደፉላቸዋል እርሱ ደፍቶ ለእርሷ ይሰጣታል። ከዚያ እርሱ ቆርቦ ልብሱን ለእርሷ ይልክላትና ትቆርባለች። እሷም ከእናት ከአባቷ ቤት እርሱም ከእናት ከአባቱ ቤት ይቆያል። እንዲህ እያሉ ፵ ቀን ከኖሩ በኋላ ሠርግ ያደርጉላቸዋል። ልብስ የልጅነት፣ ቀለበት የሃይማኖት፣ ዘውድ የክብራቸው፣ መስቀል የመከራቸው ምሳሌ ነው።
_
፵፰) ሁለተኛ የሚያገቡ ካህናት ቢሆኑ ከሹመታቸው ይሻሩ። ከዚያ በኋላ ሦስተኛ ካገቡ ግን ርኩሳን ይሆናሉ።
_
፵፱) ሴት ስልሳ ዘመን ከሆናት በኋላ ተመልሳ አገባለሁ ብትል ከምእመናን ትለይ።
_
፶) ንጽሕ ጠብቀን ከሴት ርቀን እንኖራለን ብለው ከተሳሉ በኋላ ዳግመኛ የሚያገቡ ሰዎች ሕግ አፍራሾች ናቸው።
_
፶፩) አግብቶ ለፈታ ሰው መጽሐፈ ተክሊል ማድረስ አይገባም። ፍትሐት ዘወልድ ተደግሞለት በቁርባን ያገባል እንጂ።
_
፶፪) [ቁጥር ፱፻፮] ከሚጋቡት ሰዎች አንዱ ድንግል ቢሆን ለብቻው ተክሊል ያድርሱለት።
_
፶፫) ከሦስተኛ ጊዜ በላይ ማግባት የታወቀ ዝሙት ነው። ከአራተኛ ግቢ የተወለዱ ልጆች ለክህነት ለርስት አይገቡም።
_
፶፬) ብዙ ሴት ማግባት ዝሙት መውደድ ነው። በአንድ ጊዜ ሁለት ሴት ማኖር ለማንም አይገባውም። ይህን ያደረገ ካለ ግን ሁለተኛይቱን እስኪፈታት ድረስ ሥጋውን ደሙን ከመቀበል ቤተክርስቲያን ከመግባት ይከልከል።
_
፶፭) በሚስቱ ላይ ዕቁባት ያኖረ ካህን ቢሆን ከሹመቱ ይሻር፣ ጨዋ ቢሆን ከምእመናን አንድነት ይለዩት።
_
፶፮) ያመነች ሴት ያላመነውን ወንድ ብታገባ ከምእመናን ትለይ። ከእርሱ ተለይታ ንስሓ ብትገባ ግን ይቀበሏት። ልጁን ለኢአማኒ የዳረ ቢኖር ከምእመናን ይለይ።
_
፶፯) ወንድ ሚስቱ ከሞተች ጀምሮ አንድ ዓመት ሳይሆነው ማግባት አይገባውም። ዓመት ሳይሆነው ቢያገባ ግን ሚስቱ ከተወችው ሊወርሰው ከሚገባ ገንዘብ ሁሉ ይከልከል።
_
፶፰) ሴትም ባሏ ከሞተ ጀምሮ አሥር ወር ሳይሆናት ባል ብታገባ ከገንዘቡ ምንም ምን አትውረስ።
_
፶፱) ሳትሰስንበት ሰነፈች ደረቀች ብሎ ሚስቱን የፈታ ሰው ኃጥዕ ተብሎ ይፈረድበታል። በነውር የተፈታችውንም ንስሓ ሳትገባ ያገባት ሰው ቢኖር ኃጥዕ ተብሎ ይፈረድበታል።
_
፷) ባል ለሚስቱ የሚገባውን ፍቅር ያድርግላት፣ ሴትም ለባሏ የሚገባውን ፍቅር ታድርግለት።