#ድርሳነ #ቄርሎስ #ወጰላድዮስ #ክፍል5 ይህ መጽሐፍ በዋነነት ከቀድሞ ጀምሮ የተነሱ ከሃድያንንን | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

#ድርሳነ #ቄርሎስ #ወጰላድዮስ #ክፍል5
ይህ መጽሐፍ በዋነነት ከቀድሞ ጀምሮ የተነሱ ከሃድያንንን እና ስህተታቸውን አንጠርጥሮ የሚያሳይ መጽሐፍ ነው።በከሃድያን ክህደት እንዳንወሰድ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። ክርስቶስን ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ ያለ ንስጥሮስ፣ ቃለአብን ዝርው የሚሉ እነ መርቅያን፣ በነፍሱ ምትክ ቃል ሆነው የሚሉ እነ አቡሊናርዮስ እና ሌሎችም ከሃድያን ያነሷቸውን ጥያቄዎች በደንብ የሚመልስ መጽሐፍ ነው።ነገረ ክርስቶስ ነገረ ሥጋዌ በሰፊው የተዳሰሰበት መጽሐፍ ነው።እስከ ክፍል 5 የጻፍኩት መጽሐፉን ለመጠቆም ያህል ብቻ እና እንድታነቡት እንጂ እስከ ክፍል 1000 ቢጻፍም አያልቅም።

ቄርሎስ 21 በነፍሱ ምትክ መለኮት ሆነው ያለ አቡሊናርዮስ ክርስቶስ በመስቀል ሞተ በሚለው ቃል ይረታል።ሞት ማለት መለየት ማለት ነው።ይኽውም የነፍስ ከሥጋ መለየት ማለት ነው።ከሥጋ መለኮት ነው የተለየው እንዳይባል ቅዱስ ዳዊት ውስተ ኩሉ በሐውርት መለኮቱ።መለኮቱ በሁሉ ቦታ ነው ስለሚል።ከሥጋ ተለየ ከተባለ መለኮት ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን በሥጋ የልነበረበት ጊዜ ነበረ የሚያሰኝ ታላቅ ክህደት ነው።መለኮት ምሉእ በኩለሄ በሁሉ ያለ ነው የሚለውን የሚቃወም ክህደት ነው። መለኮት በሁሉ ቦታ ይኖራል። መለኮት የሌለበት ቦታ የለም።

ቄርሎስ 23 ላይ እኛስ ከተዋሕዶ በኋላ ሁለት አንልም።ንህነሰ ኢንቤ ክልኤቱ እምድኅረ ትድምርት።እንዲል ንሥጥሮስ ግን ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ ብሎ ከመጽሐፍ ያልተገኘ ልብወለድ ይናገራል። ሐዋርያው ጠላቶቹ ስንሆን እግዚአብሔር በልጁ ሞት ይቅር አለን ብሏል።ንሥጥሮስ ማርያም የወለደችው ሌላ ነው አብ የወለደው ሌላ ነው ከማርያም የተወለደው ይራባል ይጠማል ይሞታል ከአብ የተወለደው ግን አይራብም አይጠማም አይሞትም እያለ ይናገራል።ነገር ግን ይህንን ሀሳቡን የሐዋርያው ቃል ያፈርስበታል እግዚአብሔር በልጁ ሞት ይቅር አለን ብሏል።የእግዚአብሔር ልጅ ወልድ በሥጋ መሞቱን በልጁ ሞት ብሎ ስለገለጠበት ንስጥሮስ ይህን እና ይህን በመሳሰሉ ቃላት ይረታል። መጻሕፍትም ወልድ ዋሕድ አንድ ልጅ እያሉ አንድ አንድ እያሉ በነጠላ ቅጽል ተናገሩ እንጂ ክልኤቱ ብለው አልተናገሩም።

ማጠቃለያ፦ሃይማኖት በግል ፍልስፍና እና በይመስለኛል እንዲሁም በልብወለድ አይመሰረትም።ከአበው የተቀበልነውን ሳንበርዝ ሳንከልስ ለልጅ ልጆቻችን እናወርሳለን እንጂ የምንጨምረውም የምንቀንሰውም አይኖርም።ሃይማኖት አንዲት ናት። ኤፌ.4፥4።እስከ ምጽአት ድረስ ከስንዴው ጋር ተቀላቅለው የበቀሉ እንክርዳዶች እና ሌሎች አረሞች ይኖራሉ።በምጽአት ጊዜ ግን ስንዴውን ወደ ጎተራው (መንግሥተ ሰማያት) ጌታው ያስገባዋል። እንክርዳዱንና ሌሎችን አረሞችን ደግሞ በእሳት (በገሀነም) ያቃጥላቸዋል።እስከዚያው ግን ተዋቸው ይኑሩ ብሎ ለመላእክቱ ስለተናገረ።በዚች ዓለም ላይ እስከ ምጽአት ድረስ አማኙም፥ ከሀዲውም፣ አረሚውም፣ደጉም፥ ሌባውም፥ ገዳዩም፣ ጻድቁም በአንድነት ተቀላቅለው ይኖራሉ።በምጽአት ጊዜ ግን አምነው ምግባር የሰሩት ወደዘላለም ደስታ ከዚህ ውጭ የሆኑት ደግሞ ወደዘላለማዊ መከራና ጭንቅ ይገባሉ።

አነሳስቶ ላስጀመረን
አስጀምሮ ላስፈጸመን
ልዑል እግዚአብሔር
ምስጋና ይገባል።
በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

@betremariyamabebaw
49.20K ተመዝጋቢዎች
ሃይማኖት ምድብ
አቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር