Get Mystery Box with random crypto!

#እረኛዬ #ኢየሱስ #ክርስቶስ እስኪ አስቡት ጥልን ለመቋጨት አንተ ሙተህ ለሌላው አንድነትን ፍቅርን | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

#እረኛዬ #ኢየሱስ #ክርስቶስ እስኪ አስቡት ጥልን ለመቋጨት አንተ ሙተህ ለሌላው አንድነትን ፍቅርን መስጠት አያስገርምም ነው የምትሉ? አንድ ባለቅኔ የተቀኙት አንድ ቅኔ ትዝ አለኝ። ቅኔው ሚበዝኁ ይባላል። እና ምን ይላሉ መሰላችሁ "በይነ ጣዕዋሃ ሐንካስ ትትበላእ ላሕም አምስጦ ዘይትከሃላ" ብለው ይጀምራሉ። ትርጉሙ "ስለ አንካሳ ጥጃዋ ብላ ማምለጥ የምትችለው ላም (በአውሬ) ትበላለች" እንደማለት ነው። ላሚቱ አንካሳ ጥጃዋን ስለምትወድ ጥጃዋን ለማዳን እርሷ ትበላለች። እረኛዬ ይህንን ነው ያስተማረን ስለ ሕዝብ አንድነት እና ፍቅር ራስን እስከ ሞት ማድረስ ድንቅ ነው። በአሁኑ ዘመን ሌላውን መሥዋእት አድርጎ ራሱን ማዳን የሚፈልግ ትውልድ ነው ያለ። እረኛዬ ግን ራስን ለሌሎች መዳን ሲሉ አሳልፎ መስጠትን በተግባር አስተምሮናል።

እረኛዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በእርሱ ደም መፍሰስ ከፈጣሪው ተጣልቶ የነበረው አዳም ታረቀ። የፍቅር ትርጉሙ ራስን ለሌላው ሲሉ አሳልፎ መስጠት ነው። ዮሐ. ፲፣፲፬ "መልካም እረኛ እኔ ነኝ" ብሏል። የእረኛቸውን ሞት እያሰቡ ሰማእታት ራሳቸውን ለስለት አሳልፈው ሰጡ መነኮሳት ግርማ ሌሊቱን ድምጸ አራዊቱን ታግሠው ይኖራሉ። ምእመናን ጥረው ግረው ካገኙት እየመጸውቱ ይኖራሉ።ይልቁንም ዮሐንስ ወንጌላዊ እረኛው ተሰቅሎ ካየው በኋላ እስከ ዕለተ ሞቱ ፊቱ በኀዘን ተውጦ (ቊጹረ ገጽ ሆኖ) ይኖር ነበር። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ጥቅም ያለው እንባ እና ልቅሶ ሞተ ወልደ እግዚአብሔርን ግፍዐ ሰማእታትን አስቦ ማልቀስ ነው ብሏል። እንዲሁም ኃጢኣትን እያሰቡ ማልቀስ ጥቅም ያለው ልቅሶ ነው ብሏል።

ባለቅኔው ቀጥሎ ለይእቲ ላሕም መድኃኔዓለም ተመሰላ ብሏል። ይህችን ላምም መድኃኔዓለም መስሏታል ይላል መድኃኔዓለም አዳምን ለማዳን በመስቀል ተሰቅሏልና።