Get Mystery Box with random crypto!

ቤተ- ተክለ ሃይማኖት"ወኢያኅጥኦሙ አምዘ ፈቀዱ።"

የቴሌግራም ቻናል አርማ beteteklehaimanot24 — ቤተ- ተክለ ሃይማኖት"ወኢያኅጥኦሙ አምዘ ፈቀዱ።"
የቴሌግራም ቻናል አርማ beteteklehaimanot24 — ቤተ- ተክለ ሃይማኖት"ወኢያኅጥኦሙ አምዘ ፈቀዱ።"
የሰርጥ አድራሻ: @beteteklehaimanot24
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 961
የሰርጥ መግለጫ

ቤተ- ተክለ ሀይማኖት

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-05 16:39:44 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሠላሳ በዚህችም ቀን የንጉሥ ናዖድ ሚስት ንግሥት ማርያም ክብራ አረፈች::

እርሷም መንፈሳዊ የሆነ በጎ ተግባርን ሁሉ የጠበቀች ትሩፋትንና መጋደልንም በጾምና በጸሎት የፈጸመች ነበረች::

በሕይወቷ በዘመኗ ሁሉ ከምትመኝበት የፃድቁን የቃል ኪዳን ምድር ቅበሩኝ አለች በደብረ ሊባኖስም ገዳምም ተቀበረች:: በረከቷ በእውነት ከእኛ ጋር ይሁን አሜን!

የተባረከው የሐምሌ ወር በሰላም በእግዚአብሔር ፍቃድ ተፈጸመ::

ወድ የዚህ ጹሑፍ ቤተሰቦች ይህን ጹሑፍ ለስንት የቤተ ክርስቲያን ልጆ "ኮፒ" በማድረግ እንዲያውቁ አድርገው የዚህ ጹሑፍ ቤተሰብ አደረግዋቸው?

በጣም አመሰግናሁ መልዕክቶቹን ለሌላ ስላሳወቃችሁ እርሷም የሐዋርያነትን ሥራ ስለሠሩ አስበ ሐዋርያትን ይክፈልልኝ::

እኛስ በመልዕክቶቹ ምን ያክል ተጠቀምንባቸው?

ከቅዱሳኑስ ቃል ኪዳን ስማቸውን ጠርተን ማረን ብለናል በስማቸውስ መልካም ሥራ አደርገናል?

ስለ ሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን:: መልካም የሱባኤ ጊዜ ይሁንልን! በጸሎታችሁ አስቡኝ!

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባቶቻችን ነቢያትና ሐዋርያት በጻድቃንና በሰማዕታት በደናግልና በመነኰሳት በቅዱሳን መላእክትም በተመረጡ ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጴስ ቆጶሳት በቀሳውስትና በዲያቆናት ሃይማኖታቸው በቀና በአህሩግ ሕፃናት በነዚህ ሁሉ ጸሎት ይማረን::

አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ በሁላችን በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጆች ላይ ይደር ለዘላለሙ አሜን::


እንሆ የሱባዔው በረከት

ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ፀጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

ቅድስት፣ ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት፣ ልዩ ሲል ነው፡፡
1. ንጽሕት አለ

ሌሎች ሴቶች ከነቢብ ከገቢር ቢነፁ ከሐልዮ አይነጹም፡፡ እርሷ ግን ከነቢብ፣ ከገቢር፣ ከሐልዮ ንጽሕት ናትና፡፡

2. ጽንዕትም አለ

ሌሎች ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው፡፡ ኋላ ግን ተፈትሖ አለባቸው፡፡ እርሷ ግን ቅድመ ፀኒስ፣ ጊዜ ፀኒስ፣ ድኅረ ፀኒስ፤ ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ፣ ጽንዕት ናትና፡፡

3. ክብርትም አለ

ሌሎችን ሴቶች ብናከብራቸው ጸድቃንን ሰማዕታትን ወልደዋል ብለን ነው፡፡ እርሷን ግን እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ብለን ነውና፡፡

4. ልዩም አለ

እናትነት ከድንግልና አስተባብራ የምትገኝ ከእመቤታችን በቀር ሌላ ሴት የለችምና፡፡

የእመቤታችንን ጣዕሟን በአንደበታችን፣ ፍቅሯን በልቡናችን ይሳልብን ያሳድርብን፤ አሜን!

የድንግል ልጆች የሆንን ወዳጆች ዘወትር በስሟ ብንችል አቅማችን የፈቀደውን ከሌለንም ንጹዕ ውሃ በስሟ በመዘከር በእምነት የቃል ኪዳኗ በረከት እንቀበል::

በጾመ ፍልሰታ በሱባዔው ወቅት ያፈስነውን በረከት ያራገፍነውን ኃጢአት ወደኛ እንዳይቀርብ ሁሌ በክርስቶስ ቃል በቃለ ወንጌሉ እየለመለምን እያደግን እያፈራን ጠላታችንን ዲያብሎስ ድል መንሳት አለብን::

ለዚሁም አምላከ ተክለ ሃይማኖት ይርዳን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን::


ቤተ ተክለ ሃይማኖት
ወኢያኅጥኦሙ እምዘ ፈቀዱ።
አሁኑኑ join ያድርጉ ሁሌ መረጃ ይደርሶታል
@beteteklehaimanot24
79 viewsedited  13:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 18:52:28
እምዬ ደብረ ሊባኖስ ትጣራለች

በተክለ ሃይማኖት ደጅ ወድቃችሁ ቸርነቱ የጎበኛችሁ የበዛላችሁ፣ ቃለ እግዚአብሔር ተምራችሁ በአገልግሎት ላይ ያላችሁ፣ ገዳሙንና አባቶችን ለማገልገል ማይ ውኃ የቀዳቹ፣ በየጉብር ጥዱ አናኮ በመሆን ያገለገላችሁ፣ በየተግባር ቤቱ ሙጋድ እንጨት ፈልጣችሁ የተራዳችሁ፣ በግብረ ዲቁና ገዳሙን ያገለገላችሁ፣ ስጋ ማርያምን ቅናተ ዮሐንስን የታጠቃቹ፣ ቆበ አስኬማን የደፋችሁ፣ ልብሰ ምንኩስና የለበሳችሁ፣ ዕጣን ጧፍ ዘቢብ የተራዳችሁ፣ ጠበሉን ተጠብላችሁ፣ ገድሉን ሰምታችሁ ተሻሽታችሁ፣ በኪዳኑ ማኅጠንት የተፈወሳቹ፣ ወንጌሉን ሰምታችሁ በቃሉ ያመናችሁ፣ በሥጋና በደሙ የዘለዓለም ሕይወት ያገኛችሁ፣ በጻድቁ ቃል ኪዳን የተጎበኛችሁ፣ በተክለ ሃይማኖት መንገድ ወድቃችሁ ከሞት የተረፋችሁ፣ በተክለ ሃይማኖት ወንበር የተቀመጣችሁ አባቶቻችን፣ በጻድቁ ፍቅር የተጠመዳችሁ ምእመናን እምዬ ደብረ ሊባኖስ አባታችን አባባ ተክለ ሃይማኖት በዋሻ አኑረዋት ይማጸኑባት፣ ድንኳን ተክለው፣ ዳስ ሠቀላ ሰርተው ይቀድሱና ያቆርቡባት የነበረችውን፣ ዘወትር ከፊቷ ቆመው ይማጸኑባት ለነበረችው ታቦተ ማርያምን አምዬ ደብረ ሊባኖስ እጅግ ግዙፍና በ3400 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ የተንጣለለ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን እየገነባ ወደ ሦስተኛው ምዕራፍ እየደረሰ ነውና ቤተ መቅደሷን ከፍጻሜ ለማድረስ በተቻላችሁ አቅም እግዚአብሔር የፈቀደለችሁ እርዱን ትላለች እምዬ ደብረ ሊባኖስ!

የጻድቁ ወዳጆች ይኽን መልዕክት ሼር ያርጉ!

ለበለጠ መረጃ በዚህ ይደውሉ
0991747474
የደብረ ሊባኖስ ገዳም ሕንፃ አሰሪ ኮሚቴ!

የደብረ ሊባኖስ ገዳም!
ወኢያኅጥኦሙ እምዘ ፈቀዱ።
አሁኑኑ join ያድርጉ!
@DebreLibanosGedam24
722 views15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 18:28:09 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሃያ ዘጠኝ ክብር ይግባውና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ መታሰቢያ ነው::

አባቶቻችን በዛሬው ዕለት መልካም ነገር እንድንሠራበት አዘዙን፣ ድሀ እንድንጠይቅባት፣ ቤተ ክርስቲያን እንድንሳለምባት አዘዙን።

በዛሬው ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበን እግዚአብሔር የፈቀደልንና ያደለን ሥጋ ወደሙን የምንቀልበት ያልተፈቀደልን ደግሞ ንስሐ ገብተን ለመጪው ጾመ ፍልሰታ የምንዘጋጅበት ዕለት ነው።

የተጣላን የምንታረቅባት÷ ንስሐ ያልገባን ንሰሐ የምንገባባት÷ የታሠረ የታመመ የምንጠይቅባት÷ የታረዘ የምናለብስበት÷ ለሱባኤ የምንዘጋጅበት ዕለት ነው:: ቅበላም አይደል ቅበላችን በዚህ ነው።

የቤተ ክርስቲያን ልጆች በዛሬው ዕለት ሱባኤ የሚይዙበትን ቦታ የሚቀመጡበት ለሱባኤ የሚጠቀሙበት ዕቃ የሚያዘጋጅበት ቀን ነው።

ለመሆኑ የቤተ ተክለ ሃይማኖት ቤተሰቦች እርሶ ለጾመ ፍልሰታ እንዴት እየተዘጋጁ ነው?


ቅበላ ወይስ ብቀላ
አባቶቻችን ከሐምሌ 28-30 ለጾመ ፍልሰታ ጾምን በመጾም ቅበላ ያደርጋሉ::

ቅበላ ማለት በእንግድነት ለሚመጣው እንግዳ ለእንግዳው የሚመጥነውን ያህል ክብር ለመስጠት አዘጋጅቶና ተዘጋጅቶ እንግዳውን መቀበል ነው::

እንደ ቤተ ክርስቲያናችን አስተምሕሮ ቅበላ ለጾም ነውና መንፈሳዊ በሆነ በመንፈሳዊ ሕይወት ጸድቶ መዘጋጀትና መቀበል ነው::

መጪው ጾም ከሆነ ለዚህ እንግዳ ንስሐ በመግባት፣ በመጾም፣ በመስገድ፣ በጾሙ ወቅት ለሚፈጸሙ ሥርዓቶች ራስን አዘጋጅቶ መቀበል ቅበላን ትክክለኛ ትርጉም ይሰጠዋል::

በዚህም ምክንያት ቅበላን በመብል በመጠጥ ሳይሆን ጾምን ሯሷን ጹመው ቅበላ ያደርጉባታል የቀደሙት አበው::

ምክንያቱም በጉጉት የሚጠብቋት የሚጠቀሙባት በዓመት የሚናፍቋትን የጾም እንግዳ ሊቀበሉ ነውና!

እንግዳ ሲመጣ እንደ እንግዳው ክብር መዘጋጀት ተገቢና አስፈላጊም ጠቃሚም ነው::

እኛ ልጆቻቸው ዛሬ እንደሚታየው እንደነርሱ ባንሆን እንኳ እነርሱ የሰሩትን ሥራ ሠርተን ልንመስላቸው ይገባናል።

ዛሬ ዛሬ አይደለም መንፈሳዊነት ጊዜው በማይፈቅደው መልኩ መጠጥ ቤቱን ጭፈራ ቤቱን የዝሙት መንደሩን ልናጨናንቅ አይገባም::

ጌዜው ጽሙና፣ ርጋታ፣ ጾምና ጸሎት፣ ልቅሶና እግዚኦታ የሚያስፈልግበት እንጂ እንደፈለጉ የሚበላበትና የሚጠጣበ፣ የሚጨፈርበትም ጊዜ አይደለም።

መፅሐፍ ከእንደዚህ ካለ ግብርም መንደርም ራቁ ተለዩ ነው የሚለው።

ቅበላ ምግብን በመበቀል አልነበረምም አይደለምም:: በጾም እንደ አበው ነው እንጂ መንፈሳዊ ዝግጅትን በማድረግ።

ነገር ግን ለክርስቲያኖች በማይገባ በመብል፣ በመጠጥ፣ በዝሙት፣ በጭፈራና በዳንኪራ ጾምን መቀበል ነውርም የአህዛብም ግብር ነው:: ኽረ ድብን ያለም ኃጢአት ነው።

አንድ መንፈሳዊ ሰው ክርስቶስን ነው የተሸከመው በክርስቶስ ነውና ክርስትናን ያገኘው እና ክርስቲያን መሆን አለበት::

አብዝቶ መብላትና መጠጣትን በማንኛውም ቀን ቢሆን ክርስቲያን በዚህ ግብር መታደም መታየትም ማሰብም አይገባውም::

በክርስቶስ ደም የከበረን ሰውነት በዝሙት፣ በሥካር፣ በጭፈራ በእንደዚህ ያሉ ግብር ማቆሸሽ ተገቢ አይደለም::

በጸሎታችሁ አስቡን
በየደብሩና በየገዳሙም ሱባኤ ያሰብን ንስሐ ገብተን የበደልነውን ክሰን የቀማነውን መልሰን በፊት ከምልበላው ከምንጠጣው ቀንሰን በመጥን ብቻ ሳይሆን በዓይነትም ቀንሰን አስመሳይ ሳንሆን ሆነን መጾም መጸለይ መስገድ መመጽወት በረከትም መታደልም ነው:: በጸሎታችሁ አስቡኝ።

አበው "ከምግብ ብቻ በመከልከል እንጾማለን አትበሉ .. ከክፉ ግብር መራቅ ጾማችንን ትክክል ታደርጋለች" ይላሉ::

ለዚህም አምላከ ተክለ ሃይማኖት ይርዳን አሜን! ይቅርታውና ቸርነቱ ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን።



ቴሌግራም ላይ ይኽን ተጭነው ሎድ ያድርጉ ከዚያም ጆይን ያድርጉኝ ዕለት ዕለት መረጃ ይደርሶታል።
@DebreLibanosGedam24
@DebreLibanosGedam24
@beteteklehaimanot24
@beteteklehaimanot24
119 views15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 16:27:37
እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ፊልጶስ
679 ኛው ዓመት የበዓለ ዕረፍት
መታሰቢያ በዓል አደረሰን አደረሳችሁ!

የቃል ኪዳን ምድር የብጹአን በዓት የአባባ ተክለ ሃይማኖት ደብረ ሊባኖስ አንድነት ገዳም ሐምሌ 28 ቀን በገዳሙ ቅጽር በሚገኘው በስማቸው በተሰየመው ቤተ መቅደስ ዛሬ ዋዜማውን በማኅሌት፣ ሌሊቱን ገድሉን በማንበብና በመተርጓም፣ በማኅሌትና በሰዓታት ጠዋት ሲረፍድ ታቦተ ሕጉ ወጥቶ በዑደት ከሰአትም በቅዳሴ በዝክር በየዓመቱ በድምቀት ይከበራልና እግዚአብሔር ከፈቀደሎ በዋዜማው አልያም በጠዋት ከዚህ በረከት እንዳይቀሩ።

የደብረ ሊባኖስ ገዳም!
ወኢያኅጥኦሙ እምዘ ፈቀዱ።
አሁኑኑ join ያድርጉ ሁሌ መረጃ ይደርሶታል
@DebreLibanosGedam24
153 views13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 15:40:37 ዕጨጌ ፊሊጶስ እና ቅበላ:-
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ዛሬ ሐምሌ ሃያ ስምንት የብርሃን ዓለም ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ከሆኑ ከ12ቱ ከዋክብት አንዱ የሆኑት 3ተኛው ዕጨጌ ፊሊጶስ እረፍታቸው ነው::

በደብረ ሊባኖስ ገዳሙ በወርሀ ግንቦት ያጥናሉ::ሀገረ ሙላዳቸው በሠላሌ ዝማ በምትባል ስፍራ ነው::

ከአባ ዮሓንስ ዲቁና ተቀበሉ መጽሐፈ ነቢያትንና ሐዋርያትን መዝሙረ ዳዊትን ተምረዋል::

በደብረ ሊባኖስ ገዳም በሥርዓተ ምንኩስና በትኀርምት መኖር ጀመሩ::

ተጋድሏቸውና መንፈሳዊ ሕይወታቸው ተነግሮ አያልቅም እፍኝ አተር በቀን እየተመገቡ ሦስት ዓመት ኖሩ በኋላ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት እጅ መንኲሰው ሢመተ ክህነት ተቀበሉ::

በጳጳሱ አባ ያዕቆብ ጵጵስና ተቀበሉ በሰላም ሲያስተዳድሩ ንጉሥ ዐምደ ጽዮን የአባቱን ዕቁባት ማግባት አይገባህም ሲሉ ተቃወሙት::

የንጉሡም አሽከሮች ደበደቧቸው ገረፏቸው ደማቸውም ፈሰሰ ከደማቸው እሳት ተነስቶ ከተማይቱን አቃጠላት::

ንጉሡም ፈርቶ ወደ ትግራይ አባረራቸው:: አባታችንም በተሰደዱበት በሔዱበት አገር እግዚአብሔር ከሳቸው ጋር ነውና ተአምር አደረጉ በአምልኮ ጣዖት ያሉትን ወደ ክርስትና መለሱ የሥነ ምግባር ድቀት ያለባቸውንም መክረው መለሱ::

ኋላም ንጉሡ ሲሞት ወደ ደብረ ሊባኖስ ተመለሱ በንጉሡ ፈንታ የነገሠው ልጁ ወደ ዛይ ደሴት ዝዋይ ለሰባት ዓመት አሰራቸው::

ከዚህ በኋላም አስጠርቶም ወደ ዳሞት አጋዛቸው በዛም የበዙ አረማውያንን ክርስቲያን አደረጎቸው እየመከሩና ወንጌልን እያስተማሩ አንድ ዓመት ተቀመጡ::

ዝናቸውን የሰሙ አቡነ ሰላማ አስጠሯቸው ብዙም መንፈሳዊ ጨዋታት ተጨዋወቱ ጳጳሱም አደነቁ ወደ ደብረ ሊባኖስ እንዲሄዱ ፈቀዱላቸው ንጉሡም ተስማማ::

በደብረ ሊባኖስ ገዳምም ብዙ ሥራ ፈጸሙ ዛሬ የምናየው የገዳሙን ሥርዓት የቀረጹት አባት አቡነ ፊሊጶስ ናቸው::

የደብረ ሊባኖስ ቤተ ምርፋቅ ሹመትና የሥራ ድርሻ የመጋቢው የቂሰ ገበዙ የሊቀ አበውና ሊቀ ረድ የሥራ ድርሻ የፀባቴው አሿሿምንና የሥራ ድርሻ ቀርጸው አስቀምጠው ገዳሙም እስከ ዛሬ በረከታቸው ይደርብንና እየተጠቀሙበት ይገኛሉ::

ስለ ቤተ ክርስቲያን መምህራን የሥራ ድርሻና ስላላቸው ክብር ስለ ድርጎ አሰጣጥና የጸሎት ሰዓታት በሥርዓት ቀርፀው ያስቀመጡ አባት ናቸው::

በዛሬው ቀንም ስለ ሰባቱ ቱሩፋታቸው ሰባት አክሊል ሰጥቷቸው ቃል ኪዳንም ሰጥቷቸው በ74 ዓመታቸው አረፉ::

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የአባታችን በረከትና ቃል ኪዳን ከኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን::

ቅበላ
አባቶቻችን ከሐምሌ 28-30 ለጾመ ፍልሰታ ጾምን በመጾም ቅበላ ያደርጋሉ::

ቅበላ ማለት በእንግድነት ለሚመጣው እንግዳ ለእንግዳው የሚመጥነውን ያህል ክብር ለመስጠት አዘጋጅቶና ተዘጋጅቶ መቀበል ነው::

ቅበላው መንፈሳዊ ከሆነ በመንፈሳዊ ሕይወት ጸድቶ መዘጋጀት ነው:: መጪው ጾም ከሆነ ለዚህ እንግዳ ንስሐ መግባትን በመጾም በመስገድ በጾሙ ወቅት ለሚፈጸሙ ሥርዓቶች ራስን አዘጋጅቶ መቀበል ነው::

በዚህም ምክንያት ቅበላን በመብል በመጠጥ ሳይሆን ጾምን ሯሷን ጹመው ቅበላ ያደርጉባታል አበው::

ምክንያቱም በጉጉት የሚጠብቋት የሚጠቀሙባት በዓመት የሚናፍቋትን የጾም እንግዳ ሊቀበሉ ነውና! እንግዳ ሲመጣ እንደ እንግዳው ክብር መዘጋጀት ይገባልና::

እኛ ልጆቻቸው ዛሬ እንደሚታየው እንደነርሱ ባንሆን እንኳ እነርሱ የሰሩትን ሥራ ሠርተን ልንመስላቸው ይገባ ነበር::

ቅበላ ምግብን በመበቀል አልነበረም:: በጾም እንደ አበው ይገባ ነበር:: ግን ለክርስቲያኖች በማይገባ በመብል በመጠጥ በዝሙት በጭፈራ በዳንኪራ ጾምን መቀበል ነውር ነው::

አንድ መንፈሳዊ ሰው ክርስቶስን ነው የተሸከመው በክርስቶስ ነውና ክርስትናን ያገኘው እና ክርስቲያን መሆን አለበት::

አብዝቶ መብላትና መጠጣትን በማንኛውም ቀን ቢሆን ለክርስቲያን በዚህ ግብር መታደም መታየትም ማሰብም አይገባም::

በክርስቶስ ደም የከበረን ሰውነት በዝሙት በሥካር በጭፈራ በእንደዚህ ያሉ ግብር ማቆሸሽ ተገቢ አይደለምና::

በየደብሩና በየገዳሙም ሱባኤ ያሰብንም ንስሐ ገብተን የበደልነውን ክሰን የቀማነውን መልሰን በፊት ከምልበላው ከምንጠጣው ቀንሰን በመጥን ብቻ ሳይሆን በዓይነትም ቀንሰን አስመሳይ ሳንሆን ሆነን መጾም መጸለይ መስገድ መመጽወት በረከትም መታደልም ነው::

አበው "ከምግብ ብቻ በመከልከል እንጾማለን አትበሉ .. ከክፉ ግብር መራቅ ጾማችንን ትክክል ታደርጋለች" ይላሉ::

ከጾም በኋላ በሚኖረው ሕይወታችን በረከታችንን ሳናስወስድ የተውነውን ግብር ተመልሰን ሳንደግመው ልንጓዝ ያስፈልጋል::

በዚህም የአባቶቻችን ልጆች እንባላለን አባቶቻችን የወረሷትን መንግስት በእውነት እንወርሳለን::

ለዚህም አምላከ ተክለ ሃይማኖት ይርዳን አሜን! ይቅርታውና ቸርነቱ ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን::


ቤተ ተክለ ሃይማኖት
ወኢያኅጥኦሙ እምዘ ፈቀዱ።
አሁኑኑ join ያድርጉ ሁሌ መረጃ ይደርሶታል
@beteteklehaimanot24
359 views12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 09:33:23
ወኢያኅጥኦሙ እምዘ ፈቀዱ።
አሁኑኑ join ያድርጉ ሁሌ መረጃ ይደርሶታል
@DebreLibanosGedam24
116 viewsedited  06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 09:11:36
*" አባ ፊልዾስ ዘደብረ ሊባኖስ "*+

=>ታላቁ ኢትዮዽያዊ ጻድቅ: ሐዋርያና ሰማዕት
#አቡነ_ፊልዾስ የጻድቁ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሲሆኑ የተወለዱት በምድረ ሽዋ በ1266 ዓ/ም ነው:: ከልጅነታቸው ጀምረው ምሥጢር ተመራማሪና መጻሕፍትን መርማሪ የነበሩት ጻድቁ የመነኑት ገና በ15 ዓመታቸው ነበር::

+
#በደብረ_ሊባኖስ በአሞክሮ ለ3 ዓመታት ቆይተው መንኩሰዋል:: ለ22 ዓመታትም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሆነው አገልግለዋል:: አቡነ ተክለ ሃይማኖት በ1306 ዓ/ም ነሐሴ 24 ቀን ሲያርፉ የተተኩት አባ ኤልሳዕ ቢሆኑም ለ3 ወራት ቆይተው ዐርፈዋል::

+በ1307 ዓ/ም አቡነ ፊልዾስ የደብረ ሊባኖስ አበ ምኔት (እጨጌ) ሁነዋል:: ገዳሙንም ለ28 ዓመታት መርተዋል:: ከዚያም በዘመነ አፄ ዓምደ ጽዮንና በአፄ ሰይፈ አርዕድ ብዙ ስደት: መከራ: እሥራትና ግርፋት ደርሶባቸዋል:: ምክንያቱ ደግሞ እውነትን መናገራቸውና ነገሥታቱን መገሰጻቸው ነበር:: በስደትም ለ6 ዓመታት ከ9 ወራት ቆይተዋል::

+ሃገሪቱን በስብከተ ወንጌል ካበሩ
#12ቱ_ንቡራነ_እድ አንዱ የሆኑት #እጨጌ አባ ፊልዾስ በተወለዱ በ74 ዓመት ከ9 ወራቸው በ1341 ዓ/ም ዐርፈዋል:: የተቀበሩት #በደብረ_ዕንቁ ሲሆን ካረፉ በ140 ዓመት #አቡነ_መርሐ_ክርስቶስ ዐጽማቸውን አፍልሰዋል::

ገድላቸውን የደብረ ሊባኖስ አንድነት ገዳም አሳትሞታል በውስጡም መንፈሳዊ፣ አስተዳደራዊ፣ ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ ተመራማሪነት፣ መንፈሳዊ ፍልስፍና፣ ድንቅ መለኮታዊ ጸጋ የሚያድል ነውና አንብበው ይጠቀሙበት።

ሐምሌ 28 በዓለ ንግሣቸው በደብረ ሊባኖስ ገዳም በአቡነ ፊልጶስ ቤተ ክርስቲያን በደማቁ ይከናወናልና ፈጽመው እንዳይቀሩ።

የደብረ ሊባኖስ ገዳም
ወኢያኅጥኦሙ እምዘ ፈቀዱ።
አሁኑኑ join ያድርጉ!
@DebreLibanosGedam24
114 viewsedited  06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 08:51:14 ለሁሉም የጻድቁ ልጆች ታላቅ መንፈሳዊ የንግስ በዓል በደብረ ሊባኖስ ገዳም!

ከብርሃን ዓለም ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ከ 12ቱ ከዋክብት መካከል 3ኛ ዕጨጌ የሆኑ አቡነ ፊሊጶስ በዓለ ዕረፍታቸው በደማቅ መንፈሳዊ በዓል ሐምሌ 28 ደብረ ሊባኖስ ገዳም ይከበራልና ፈጽመው እንዳይቀሩ።

በደብረ ሊባኖስ ገደም አንድነት ገዳም ዛሬ የምናየውንና ገዳሙ በቅርስነት ጠብቆት ያለውን ሥርዓተ ገዳም የቀረጹ አቡነ ፊሊጶስ ናቸው።

እናም የጻድቁ ወዳጆች እግዚአብሔር የፈቀደላችሁ ሐሙስ ሐምሌ ሃያ ስምንት በዓመት አንድ ጊዜ በሚቀደሰው ቤተ ክርስቲያን ተገኝታችሁ ታከብሩ ዘንድ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ጥሪ ያድርጋል።

በዚሁም ገዳሙ ያሳተመውን ገድላቸውን ይዘው፣ ደዌ የሚፈውሰውን ማኅጠንታቸውን ታጥነው ይመለሳሉና ፈጽመው እንዳይቀሩ።

ለሁሉም የጻድቁ ልጆች አድ ያድርጉ ሼር ያድርጉ!

https://t.me/DebreLibanosGedam24
657 views05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 08:51:01
111 views05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 19:28:29 ሴት:-
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሃያ ሰባት በዚህች ቀን የአዳም ልጅም ሴት ያረፈበት ነው::

ሴትም 205 ዓመት ኖረ ሔኖስንም ወለደው:: ሔኖስንም ከወለደ በኋላ 709 ዓመት ኖረ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ:: መላ ዕድሜው 912 ዓመት ሆነ በሰላምም አረፈ::

እግዚአብሔር አምላክ የእኛንም የንስሐ ዕድሜ እንዲያረዝምልን በጊዜውም ያለ ጊዜውም በሃይማኖት እንዲያጸናን ከእግዚአብሔር ጋር መኖር አለብን::

አጥተንም አግኝተንም: ታመንም በጤና ሁነን:.በወጣትነታችንም በሽምግልና ወራትም ከእርሱ ጋር በመኖር እርሱን በመፍራት ሕጉን በመጠበቅ በቸርነቱ እቅፍ ውስጥ በረድኤት እንዲያኖረን ያለፈ ኃጢአታችንን ተናዘን ለመጪው ከክፋ ሥራ እንዲጠብቀን የበደልነውን ክሰን የቀማነውን መልሰን ቀሪ ዘመናችንን እንዲባርክልን መጸለይ አለብን::

ጊዜ በተለያዩ ምከንያቶች መንፈሳዊ ማንነታችንን ለማሳጣት በተለያዩ ዘዴዎች ነጣቂ ተኩላዎች እያሰፈሰፉ ያለበት ወቅት ነው።

ባለፈው በስንፍና የተመላለስንበት ጊዜ ይበቃናል፣ መንፈሳዊነታችን በመንፈሳዊ ትምህርት እናጠንክረው፣ መንፈሳዊ ማንነታችንን በነስሐ፣ በጾም፣ በጸሎትና በስግደት እናጠንክረው።

የዝም ብሎ ክርስትና ኋላ የመናፍቅም የሠይጣንም መጫወቻ ነው የሚያደርገን። ዘመናችን እንዲባረክ፣ ሕይወታችን፣ ትዳራችሁን፣ ኑሮአችንና ሥራችን እንዲባረክ በእግዚአብሔር ፊት በንጽሕና እንውደቅ።

በተለይ መጪውንም የፍልሰታን ጾም አበው እንደተጠቀሙባት ከፈቃደ ሥጋ ርቀን: ጾመን: ጸልየን: ሰግደን: መጽውተን መልካምና በጎ ነገራችን በቀሪው የዕድሜ ዘመናችን እንዲከተለን በዚህች ጾም እንድንጠቀምበት ፈጣሪ ይርዳን ያበርታን::

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ አባቶች ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን::


ቤተ ተክለ ሃይማኖት
ወኢያኅጥኦሙ እምዘ ፈቀዱ።
አሁኑኑ join ያድርጉ ሁሌ መረጃ ይደርሶታል
@beteteklehaimanot24
147 views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ