Get Mystery Box with random crypto!

እምዬ ደብረ ሊባኖስ ትጣራለች በተክለ ሃይማኖት ደጅ ወድቃችሁ ቸርነቱ የጎበኛችሁ የበዛላችሁ፣ ቃለ | ቤተ- ተክለ ሃይማኖት"ወኢያኅጥኦሙ አምዘ ፈቀዱ።"

እምዬ ደብረ ሊባኖስ ትጣራለች

በተክለ ሃይማኖት ደጅ ወድቃችሁ ቸርነቱ የጎበኛችሁ የበዛላችሁ፣ ቃለ እግዚአብሔር ተምራችሁ በአገልግሎት ላይ ያላችሁ፣ ገዳሙንና አባቶችን ለማገልገል ማይ ውኃ የቀዳቹ፣ በየጉብር ጥዱ አናኮ በመሆን ያገለገላችሁ፣ በየተግባር ቤቱ ሙጋድ እንጨት ፈልጣችሁ የተራዳችሁ፣ በግብረ ዲቁና ገዳሙን ያገለገላችሁ፣ ስጋ ማርያምን ቅናተ ዮሐንስን የታጠቃቹ፣ ቆበ አስኬማን የደፋችሁ፣ ልብሰ ምንኩስና የለበሳችሁ፣ ዕጣን ጧፍ ዘቢብ የተራዳችሁ፣ ጠበሉን ተጠብላችሁ፣ ገድሉን ሰምታችሁ ተሻሽታችሁ፣ በኪዳኑ ማኅጠንት የተፈወሳቹ፣ ወንጌሉን ሰምታችሁ በቃሉ ያመናችሁ፣ በሥጋና በደሙ የዘለዓለም ሕይወት ያገኛችሁ፣ በጻድቁ ቃል ኪዳን የተጎበኛችሁ፣ በተክለ ሃይማኖት መንገድ ወድቃችሁ ከሞት የተረፋችሁ፣ በተክለ ሃይማኖት ወንበር የተቀመጣችሁ አባቶቻችን፣ በጻድቁ ፍቅር የተጠመዳችሁ ምእመናን እምዬ ደብረ ሊባኖስ አባታችን አባባ ተክለ ሃይማኖት በዋሻ አኑረዋት ይማጸኑባት፣ ድንኳን ተክለው፣ ዳስ ሠቀላ ሰርተው ይቀድሱና ያቆርቡባት የነበረችውን፣ ዘወትር ከፊቷ ቆመው ይማጸኑባት ለነበረችው ታቦተ ማርያምን አምዬ ደብረ ሊባኖስ እጅግ ግዙፍና በ3400 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ የተንጣለለ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን እየገነባ ወደ ሦስተኛው ምዕራፍ እየደረሰ ነውና ቤተ መቅደሷን ከፍጻሜ ለማድረስ በተቻላችሁ አቅም እግዚአብሔር የፈቀደለችሁ እርዱን ትላለች እምዬ ደብረ ሊባኖስ!

የጻድቁ ወዳጆች ይኽን መልዕክት ሼር ያርጉ!

ለበለጠ መረጃ በዚህ ይደውሉ
0991747474
የደብረ ሊባኖስ ገዳም ሕንፃ አሰሪ ኮሚቴ!

የደብረ ሊባኖስ ገዳም!
ወኢያኅጥኦሙ እምዘ ፈቀዱ።
አሁኑኑ join ያድርጉ!
@DebreLibanosGedam24