Get Mystery Box with random crypto!

ቤተ-ዕንዚራ

የቴሌግራም ቻናል አርማ betenzira — ቤተ-ዕንዚራ
የቴሌግራም ቻናል አርማ betenzira — ቤተ-ዕንዚራ
የሰርጥ አድራሻ: @betenzira
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.08K
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን "ቤተ-ዕንዚራ" ወደ ተሰኘው የቴሌግራም ቻናላችን በደህና መጡ።ይህ "የበገና መዝሙሮችን እና ለበገነኞች ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን ብቻ "የምታገኙበት ቻናል ነው።በዚህ ቻናል የተረሱ
(የተዘነጉ) የጥንት የበገና መዝሙሮችን እንዲሁም የአሁን ዘመን የበገና መዝሙራትን በአንድ ላይ አሰባስበን ለበገነኞች እንዲሁም ለሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እህት ወንድሞቻችን የምናካፍልበት የሁላችን የበገና ቤት ነው።

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-11 18:23:35
2.1K views15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 18:22:48
1.7K views15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 18:22:12
1.5K views15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 17:34:51 የኢትዮጵያ አብያተ መንግሥታት እና በገና

እስከ ቅርብ ዘመን ድረስ የኢትዮጵያ ቤተ- መንግሥት የፆም ወራት ሲመጣ በገና ክፉኛ ለምዶ ነበር። ምሽት ከእራት በኃላ መሪዎቿ ለጥቂት ሰዓትም ቢሆን በገና ያስደረድሩበት ነበር። በበገና ድርደራ አጋንንት ይርቃሉ። ቅዱስ ዳዊት የሳኦልን እርኩስ መንፈስ ያሸንፍበት የነበረው በበገና ድርደራ ነበር። ይህንን ያወቁ የኢትዮጵያ መሪዎች በተለይ በዐቢይ ፆም ወቅት ቤተ-መንግስቱን ከበገና ድርደራ ፆም አያሳድሩትም ነበር።


ጌታቸው በቀለ፣ጉዳያችን ድህረ ገጽ፣ የካቲት ፳፬/፳፻፮


═════◉❖◉═════

╭══•|❀:✧๑♡๑✧:❀|•══╮
#ቤተ_ዕንዚራ
╰══•|❀:✧๑♡๑✧:❀|•══╯

@betenzira
@bete_enzira
1.4K viewsedited  14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 17:34:40
1.3K viewsedited  14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 17:34:24
1.1K views14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 17:34:24
1.1K views14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 17:34:13 ነፍስ የዘራው በገና

የጥንቱን አቆይተን ከቅርቡ ከ፲፱ኛው ምዕት ዓመታት ጀምሮ ብንመለከት እንኳ በገና በነገሥታቱና በመኳንንቱ ቤት አገልግሎት ይሰጥ ነበር። የበገናው መምህር ሲሳይ ደምሴ ገብረ ጻድቅ “የበገና መማሪያ” በተሰኘው መጽሐፋቸው እንደጻፉት አፄዎቹ ቴዎድሮስ፣ ተክለ ጊዮርጊስ፣ ዮሐንስ፣ ምኒልክ፣ ንግሥታቱ እቴጌ ጣይቱ፣ ዘውዲቱ፣ ራስ መኰንን በገና ይደረድሩ ነበር። ሌሎች ነገሥታትና መሳፍንት፣ መኳንንትም መደርደር ባይችሉ እንኳ በገና ደርዳሪዎች እንደነበራቸው ይነገራል።

°°°
ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ በ፲፱፻፶ ዎቹ በአክሱም የኅዳር ጽዮን ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ በተገኙ ጊዜ ታቦተ ሕጉን ካጀቡት መካከል አንዱ የሆኑትን አለቃ ተሰማ ወልደ አማኑኤልን በገና ሲደረድሩ በትኩረት ይመለከታሉ፡፡ ይህ የበገና ሙያ አገርንና ቤተ ክርስቲያንን የሚጠቅም ሙያ ስለሆነ መስፋፋት ይገባዋል በማለትም አለቃ ተሰማ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ያደርጋሉ፡፡ በወቅቱ የሙዚቃና ስፖርት ሥልጠና ይሰጥ በነበረው በቀድሞ ስሙ አምኃ ደስታ ትምህርት ቤት (የአሁኑ እንጦጦ አምባ) የበገና ድርደራን እንዲያስተምሩ ይመድቧቸዋል፡፡

°°°
"መጽሐፈ በገና" በሚል ርዕስ መጽሐፍ ያሳተሙት ዲያቆን ዳዊት ዮሐንስ እንደገለጹት፣ በወቅቱ ከመሳፍንቱና ከመኳንንቱ፣ ከካህናት ወገን የሆኑና ሌሎች ወንዶችና ሴቶች በገና ድርደራን ለመማር ወደ አለቃ ተሰማ ዘንድ ይዘልቁ ነበር፡፡ ነገር ግን ትምህርቱ የሚሰጥበት መንገድ ሥርዓተ ትምህርት ተቀርፆለት፣ መማሪያ ቦታ ተዘጋጅቶለት፣ ቋሚ መምህር ተመድቦለት አይደለም፡፡

°°°
ይሁን እንጂ በዚህ ዘመን ከአለቃ ተሰማ ትምህርት የቀሰሙት ተማሪዎች መጋቤ ስብሐት ዓለሙ አጋ፣ አቶ ገብረ ኢየሱስ፣ አቶ አድማሱ ፍቅሬ፣ አቶ ታፈሰ ተስፋዬ፣ አቶ ደምሴ ደስታ፣ አቶ ሥዩም መንግሥቱና አቶ ተድላ ተበጀ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከነዚህ ተማሪዎች መካከል በተለይ ዓለሙ አጋ በ፲፱፻፷፭ ዓ.ም. ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በጂኦግራፊ በባችለር ዲግሪ ከተመረቁ በኋላ ከሠለጠኑበት ሙያ በተጨማሪ በገናን በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ማስተማር የጀመሩበት ጊዜ ነበር፡፡

°°°
በ፲፱፻፷፮ ዓ.ም. ለመጀመርያ ጊዜ መጋቤ ስብሐት ዓለሙ አጋ፣ ጸጋዬ ደባልቄና ፣ሲንትያ ቲንበርሊን (ዶ/ር) የበገና ሥርዓተ ትምህርት በእንግሊዝኛ ቋንቅ ማዘጋጀታቸውን፣ በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ለ፫ኛ እና ፬ኛ ዓመት ተማሪዎች በሳምንት ሁለት ቀን ትምህርቱ ይሰጥ እንደነበረ መጽሐፈ በገና ዘክሮታል፡፡

°°°
የ፲፱፻፷፮ቱን አብዮት ተከትሎ በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ይሰጥ የነበረው የበገና ሥልጠና እየተዳከመ በመምጣት በ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. ተቋረጠ፡፡ በኋላ ላይ በተለያዩ አጋጣሚዎች በታዋቂው የበገና ደርዳሪና የመሰንቆ ተጫዋች በሆኑት መምህር ዓለማየሁ ፋንታ ትምህርቱ በውስን መልኩ መሰጠቱ ቀጠለ፡፡

°°°
በቀጣይ ሁለት አስር ዓመታት የበገና ሙያ የተመናመነበት የደርዳሪዎች ቁጥርም ያነሰበት ቢሆንም፣ ውስን መምህራን ልጆቻቸውንና ፍላጎቱ ያላቸውን ሁሉ ያስተምሩ ነበር፡፡ ከእነዚህም መካከል የበገና ደርዳሪው ገብረ ኢየሱስ ልጅ የሆነችው ዘማሪት ሶስና ገብረ ኢየሱስ፣ መምህር ሲሳይ ደምሴ፣ዘማሪት የትምወርቅ ሙላት ይገኙበታል፡፡

°°°
ፒያሳ በሚገኘው የታዋቂው በገና ደርዳሪ መጋቤ ስብሐት ዓለሙ አጋ መሥሪያ ቤት በመሄድ ሙያቸውን የሚያሳድጉም ነበሩ፡፡ በገናን ከመጥፋት ካዳኑት መካከል እሳቸውን በቀዳሚነት የሚጠቅሱ አሉ፡፡

°°°
በአሁኑ ዘመን ከተነሱ የበገና ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት መምህር ሲሳይ ደምሴ ገብረ ጻድቅ በ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. የበገና ትምህርታቸውን አጠናክረው በመያዝ ከድርደራ ባለፈ ራሱን የዜማ መሣሪያውን በማምረት የነበረውን ዕጥረት ማቃለላቸው ይነገርላቸዋል፡፡

°°°
በገና ለመስፋፋት ዕድል ያገኘበት ፲፱፻፺፮ ዓ.ም. ለበገና ታሪካዊ ዓመት ነበር፡፡ ከዚህ ዘመን በኋላ የበገና ሙያ እንዲስፋፋ የሚያደርጉ ብዙ ለውጦች ታይቶበታል፡፡ በአዲስ አበባ በሰኔ ፲፱፻፺፮ ዓ.ም. የተዘጋጀው ጉባዔ "በገና ለምን ይጥፋ?" በሚል መሪ ቃል ነው፡፡ ከጉባዔው በኋላ በገናን የማስተማር አስፈላጊነት በመጥቀስ ትምህርቱ እንዲሰጥ ምክረ ሐሳባቸውን ለማኅበረ ቅዱሳን ያቀረቡት መምህር ሲሳይ ደምሴ ናቸው፡፡ በዚያው ዓመት በሐምሌ ወር "የአቡነ ጎርጎርዮስ የዜማ መሣርያዎች ማሠልጠኛ ማዕከል" ተቋቁሞ በይፋ በገናን ማስተማር ሲጀምር ቀዳሚዎቹ መምህራን ሲሳይ ደምሴ፣ ሶስና ገብረ ኢየሱስና ዘውዱ ጌታቸው ነበሩ፡፡

°°°
ከሦስት ዓመት ቆይታ በኋላ ከአዲስ አበባ ውጭ በጉራጌ ዞን በሚገኘው የምሑር ኢየሱስ ገዳም "ቤተ እንዚራ" የሚባል የበገና ትምህርት ቤት በመምህር ሲሳይ አስተባባሪነት በሀገረ ስብከቱ አማካይነት ሲቋቋም የመጀመርያዎቹን ሠልጣኞች ያስተማሩት አስተባባሪው ናቸው፡፡ ትምህርት ቤቱ እስካሁን ሥልጠና እየሰጠ ሲሆን በርካቶችን አፍርቷል፡፡ በየዓመቱም የበገና ጉባዔ በእኩሌታ ጾም (ደብረ ዘይት) እያከናወነ ይገኛል፡፡

°°°
በሌላ በኩል የበገናን ዕጥረት ለመቅረፍም በ፳፻፭ ዓ.ም የተቋቋመው "ሲሳይና ፍጹም የዕደ ጥበባትና የዜማ መሣርያዎች ማምረቻ" ዓይነተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ መምህር ሲሳይ በቀጣይ ዓመትም የራሳቸውን "ሲሳይ በገና የዜማ መሣሪያዎች ማሠልጠኛ ተቋም" ን በአዲስ አበባ በማቋቋማቸው በስምንት ዓመታት ውስጥ በርካቶችን ከበገና ሙያ ጋር አስተዋውቀዋል፡፡ በአሁን ጊዜ አራት ኪሎ በሚገኘው የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ባሉት ክፍሎች ከበገና በተጨማሪ የመሰንቆና የክራር ትምህርት ይሰጡበታል፡፡

°°°
በሌላ በኩል በየክልሉ ከተሞችም የሚገኙት የማኅበረ ቅዱሳን ማዕከላትም የበገና ሙያን በማሠልጠን ሙያው እንዲስፋፋ አስተዋጽኦ እያደረጉ ናቸው፡፡

ሔኖክ ያሬድ፣ ሪፖርተር ጋዜጣ፣ መጋቢት ፲፰ /፳፻፲፬


═════◉❖◉═════

╭══•|❀:✧๑♡๑✧:❀|•══╮
#ቤተ_ዕንዚራ
╰══•|❀:✧๑♡๑✧:❀|•══╯

@betenzira
@bete_enzira
1.6K viewsedited  14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 17:33:59
1.1K views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 17:33:59
1.1K views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ