Get Mystery Box with random crypto!

ማዕከላዊ ዕዝ ሀገርን ሊያሸብር የሚያስብ ማናቸውንም የጠላት ኃይል መደምሰስ የሚያስችል ወታደራዊ አ | ቤተ መከላኪያ @ETHIOPIA

ማዕከላዊ ዕዝ ሀገርን ሊያሸብር የሚያስብ ማናቸውንም የጠላት ኃይል መደምሰስ የሚያስችል ወታደራዊ አቅም ገንብቷል።

ዕዙ በተለያየ የመሬት ገፅታ ላይ ሊያጋጥም የሚችል ጠላት ላይ ድል ለመቀዳጀት እና ለመደምሰስ የሚያስችለውንም ወታደራዊ ልምምድ ማድረጉ ተገልጿል።

የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ እንዳሉት በተለያየ መንገድ ሃገር የማፍረስ አጀንዳ ይዘው በመንቀሳቀስ የህዝቡን ሰላም ለማወክ በሚዳክሩ የጥፋት ሃይሎች ላይ የማያዳግም ርምጃ ለመውሰድ እና የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሰራዊታችን ወታደራዊ አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ ገንብቷል።

በዕዙ የኮር አዛዥ የሆኑት ብ/ጀኔራል ተስፋዬ ረጋሳ በበኩላቸው ሰራዊቱ ከዚህ ቀደም ከጠላት ጋር ባካሄዳቸው የአውደ ውጊያ ውሎዎች በርካታ ልምድና ተሞክሮችን እንዳገኘበት ገልፀው፣ አሁን ላይ የተፈጠረለትን ፋታ እደመልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ ያደርጋቸው ወታደራዊ ልምምዶች የዝግጁነት ደረጃውን አሳድጎበታል።

በዕዝ ደረጃ በተካሄደው ወታደራዊ ልምምድ ላይ የተገኙ የዕዝ፣ የኮር እና የክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራሮች ሰራዊቱ የደረሰበትን ግዳጅ የመፈፀም አቅም አድንቀዋል።

ማዕከላዊ ዕዝ ለኢትዮጲያ ሰላም መጠበቅ እስከ ህይወት ዋጋ መክፈል የሚችሉ የቁርጥ ቀን ልጆች ያሉበት፣ ህብረት ያደመቀው የሰራዊት ክፍል ነው።

ኤፍሬም አድማሱ
ፎቶግራፍ እምነ ጋሻው