Get Mystery Box with random crypto!

የ6ኛ ዕዝ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦሮች የሚሰጣቸውን ግዳጅ በድል ለመወጣት በሚያስችላቸው ዝግጁነት ላይ | ቤተ መከላኪያ @ETHIOPIA

የ6ኛ ዕዝ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦሮች የሚሰጣቸውን ግዳጅ በድል ለመወጣት በሚያስችላቸው ዝግጁነት ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ።

በ6ኛ ዕዝ የሜካናይዝድ ዋና አዛዥ ኮ/ል ደሳለኝ ፈይሳ እንደተናገሩት በህግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት የሜካናይዝድ ክፍሎቻችን የጠላትን አንገት በማስደፋት እና ለተዋጊው የጦር ክፍሎቻችን የተኩስ ድጋፍ በመስጠት አኩሪ ስራዎችን ሰርተዋል።

የታጠቅናቸውን ከባድ መሳሪያዎች በማጠናከር እና የተለያዩ ስልጠናዎችን በማካሄድ ብቃት ያለዉ የመሳሪያ ምድብተኞችን በማፍራት በጠላት ላይ የበላይነትን መጎናጸፍ የሚያስችል የዝግጁነት ስራዎችን በሚፈለገው ልክ ሰርተናልም ብለዋል።

በቀጣይ የሚሰጡንን ማንኛውንም ግዳጆች ለመፈጸም የሚያስችል በቂ የሆነ አቅም መገንባት ችለናል ያሉት ኮ/ል ደሳለኝ ፈይሳ የሰራዊቱ ሞራልና ስነ ልቦናዊ ዝግጁነቱም በከፍተኛ ደረጃ መገንባቱን ገልፀዋል።

አለባቸዉ ዳኘ
ፎቶግራፍ ሺመልስ ሹምዬ