Get Mystery Box with random crypto!

#አባዬ_ጎበዝ_ነህ! አንድ እውነተኛ ታሪክ ላጫውትህ። ከአመታት በፊት ፓሪስ ውስጥ በሚገኝ የኦፔራ | All Slots Free Spins How To Play Roulette Game Casino Free Slots Games Bet 25

#አባዬ_ጎበዝ_ነህ!

አንድ እውነተኛ ታሪክ ላጫውትህ። ከአመታት በፊት ፓሪስ ውስጥ በሚገኝ የኦፔራ አዳራሽ ውስጥ ሙዚቃውን ሊያቀርብ አንድ ታዋቂ ዘፋኝ ስምምነትን ፈጸመ። እሱ እንደሚመጣ የሰሙ አድናቂዎቹ የመግቢያ ትኬቶችን ተጋፍተው ገዙ። ሙዚቃው በሚቀርብበት እለትም፤ የመድረክ አስተናባሪው ንግግር ማድረግ ጀመረ -

"ክቡራት እና ክቡራን፤ በትዕግስት ስለጠበቃችሁን እናመሰግናለን፤ ሆኖም ለዛሬ ቀጠሮ የተያዘለት ሙዚቀኛ በህመም ምክንያት ሊገኝ አልቻለም። ነገር ግን በእርሱ ምትክ ሌላ ሙዚቀኛ ፕሮግራሙን የሚያስቀጥለው ይሆናል"

ታዳሚዎቹ አጉረመረሙ፤ ይህንን ጠብቀው አልነበረም የመጡት።

ተጠባባቂ የተባለው ሙዚቀኛ ሙዚቃውን አቀረበ። ሲጨርስም፤ አዳራሹ ምቾት በማይሰጥ ሰጥታ ተዋጠ። በመሃል አንድ ህጻን ልጅ ከወንበሩ ተነሳና -

"አባዬ፤ ጎበዝ ነህ!" የሚል ድምጽን አሰማ። አዳራሹን የሞሉት ታዳሚዎች ይህንን ሲሰሙ እንባ እያነቃቸው ማጨብጨብ ጀመሩ...

አንዳንዴ በህይወታችን ውስጥ "ጎበዝ ነህ፤ በርታ!" ብለው የሚገፉን ሰዎች ያስፈልጉናል። የመጣህበትን መንገድ ባላውቀውም፤ ያለፍካቸው ብዙ ችግሮች እንቅፋቶች እና መከራዎች አሉና አይዞህ በርታ፤ ጎበዝ ልልህ እወዳለሁ።

አይዞህ በርታ!!!

@cekuaa
ነገ መልካም ይሆናል !