Get Mystery Box with random crypto!

ክፉ መንፈስ ከሃይማኖት ፊት ሲቆም ቀድሞውኑ ሃይማኖትን እንዳታገኘው፣ አግኘተህ እንዳትቀበለው፣ ተቀ | በማለዳ ንቁ !

ክፉ መንፈስ ከሃይማኖት ፊት ሲቆም ቀድሞውኑ ሃይማኖትን እንዳታገኘው፣ አግኘተህ እንዳትቀበለው፣ ተቀብለህም እንዳታውቀው ሲል ነው የሚታገለው፡፡ ዞሮ መጥቶ ከኋላህ ከቆመ ግን (ወደኋላ ሄዶ የሚጎትተው ከፊት ሆኖ መዝጋት ሲያቅተው ነው፤ በሌላ አገላለጥ ሃይማኖትን ስታውቀውና አውቀህ መኖርን ስትጀምርበት ነው)፤ ስለ ሃይማኖት በሆነ ደረጃና መጠን ያወከውን እንዳትኖረው ይፋለማል፡፡ መንፈሳዊ እውቀቶችህ በልቦና መዝገብ እንዳይታተሙና በየመቼታቸው እንዳይተረጎሙ አስሮ ይይዛሃል፡፡ ሕይወትና መንፈስ የሆነቺው ወንጌል በኑሮህ ላይ እንዳትነበብ ይፋለምሃል፡፡

               3•  ዲያቢሎስ ከሃይማኖት ጎን ይቆማል

ከክርስቶስ የሕይወት ታሪክ እንደምንገነዘበው፥ አይሁዶች የዳዊትን ልጅ የገደሉት በዳዊት ስም ነው፡፡ የአብርሃምን አምላክ ያሳደዱት የአብርሃም ዘሮች ነን በማለት ነው፡፡ ይሄ፥ ዲያቢሎስ ሃይማኖት አለን የሚሉ ሰዎችን በመጠቀም ሃይማኖትን እንደሚፋለም ይነግረናል፡፡

አንድ ሰው ከጎኔ ቆሟል የምንለው አባባል ብዙ ጊዜ ወዳጅነትን ለመግለጽ የምንጠቀምበት አነጋገር ነው፡፡ እህሳ ዲያቢሎስ ከሃይማኖት ጎን ይቆማል ስንል፥ ሃይማኖትን እንደ ወዳጅ ተጠግቶ ነውን እንይዛለን፡፡ ሃይማኖት ከኛ ወዲያ ላሳር የሚሉ ወገኖችን በመጠቀም፣ ሃይማኖት በኛ ቢሮ ካላለፈች ተሳስታለች ከሚሉት ጀርባ በመከለል፣ የሃይማኖትን ሥርዓትና ወግ እናስጠብቃለን የሚሉ ፍቅር አልባ ሰዎችን በማሰለፍ፣ ሃይማኖትን ለሥጋ ትርፍና ለቁስ አምልኮት ከሚገለገሉባት የቤተ መቅደስ ነጋዴዎች አጠገብ በመሆን፣ ሃይማኖትን እንደ ቡድን መመደቢያ ወይንም እንደ ጎራ መለያ ድርጅት የሚቆጥሩ ተከታዮችን ተገን በማድረግ፥ ዲያቢሎስ የዓለምን ምሪት ወደርሱ የዓለማ አቅጣጫ እንዲያጋድል ተግቶ ይሠራል፡፡

ይቀጥላል..

@bemaleda_neku