Get Mystery Box with random crypto!

ለዚህ ደግሞ የሀብት ምንጮች ልየታ ጎን ለጎን እየተሠራበት መሆኑን ጠቁመዋል። ከዚያም ወደ ትግበራ | በኩር ጋዜጣ Bekur Newspaper

ለዚህ ደግሞ የሀብት ምንጮች ልየታ ጎን ለጎን እየተሠራበት መሆኑን ጠቁመዋል። ከዚያም ወደ ትግበራ የሚገባ ይሆናል:: የትግበራ ሥራው በተቋማት በኩል የሚከናወን መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር አባተ የተቋቋመው ጽ/ቤት ደግሞ በዋናነት የማስተባበር ኃላፊነቱን እንደሚያከናውን ጠቁመዋል። የሚገኘው ገንዘብም በአንድ የገቢ ቋት ብቻ ገቢ ይደረጋል ብለዋል።
የሀብት ማሰባሰብን በተመለከተም “ጋን በጠጠር ይደጋፋል ነውና ሁላችንም የምንችለውን እንደግፍ፤ ገንዘብ ያለን በገንዘብ፣ ሐሳብ ያለን በሐሳብ እንደግፍ” ብለዋል:: ዶክተር አባተ አያይዘው እንዳሉት የትግበራ ሥራው በሦስት ደረጃዎች ተከፍሏል፤ በረዥም፣ በመካከለኛ እና በአጭር ጊዜ (በአምስት ዓመታት) የሚከናወኑ ተግባራትን በመለየት ችግሮቹን ለመፍታት ይሠራል፤ የወደሙ ተቋማትንም ቀደም ከነበራቸው በተሻለ ለመገንባት እንደሚሠራ በማንሳት “ከዚህ በተጨማሪም ዋናው ነገር ችግሩ እንዳይደገም ማድረግ ነው፤ ለዚህም በልዩ ትኩረት ይሠራል” ብለዋል::

ትምህርት ሚኒስቴርም ሆኑ ጤና ሚኒስቴር በጦርነቱ የወደሙ ተቋማትን በተሻለ መንገድ መልሶ ለመገንባት ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል፤ ለአብነትም የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ በተገኙበት በደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል። የጤና ተቋማትም እንደ ጉዳት መጠናቸው ጥገና ተደርጎላቸው ወደ ሥራ ተመልሰዋል፤ የወደሙትን ደግሞ መልሶ ለመገንባት በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል። የመልሶ ግንባታ ሂደቱ በየደረጃው ሕዝብ እንዲያውቀው ይደረጋል። “እናግዛችሁ ብለው የመጡ አሉ - ምስጋናችን የላቀ ነው። የወደሙትን ተባብረን በተሻለ መንገድ እንገነባለን” ብለዋል ዶክተር አባተ::

(ጌትሽ ኃይሌ)
በኲር ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ዕትም
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ
በhttp://www.amharaweb.com/Bekur ላይ ማግኘት ይችላሉ።