Get Mystery Box with random crypto!

ትክክለኛው መስመር ለማስገባት መሞከር ግን ያስቸግራል:: ስለዚህ በራስ እቅድ፣ በራስ ፖለቲካዊ እሳ | በኩር ጋዜጣ Bekur Newspaper

ትክክለኛው መስመር ለማስገባት መሞከር ግን ያስቸግራል:: ስለዚህ በራስ እቅድ፣ በራስ ፖለቲካዊ እሳቤ እና በራስ ተቋም ከመመራት ባለፈ አጠናክሮ ብልጫ ወስዶ ሕወሓትን ልክ ማስገባት ተገቢ ነው ባይ ናቸው መምህሩ::
በድሬድዋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር የሆኑት መምህር በፀሎት አዲሱ በበኩላቸው ሕወሓት ድርድርን እና ሰጥቶ የመቀበል መርህን የማይቀበል የፖለቲካ ታሪክ ያለው ድርጅት ነው ይሉታል። በልጦ እንጂ እኩል ሆኖ መቀመጥ ለሕወሓት ጭቆና ነው የሚሉት መምህሩ ለዚህ ደግሞ ከሕወሓት የበለጠ ተገዳዳሪ ሆኖ መገኘት አስፈላጊ ስለመሆኑ ይናገራሉ፡። ሕወሓት ለመወያየት ያቀረባቸው ቅድመ ሁኔታዎች በገሀዱ ዓለም የማይሆኑ እና አፍራሽ ናቸው። ይህም ሕወሓት ለሰላም ሳይሆን ለጦርነት ስለመዘጋጀቱ ማሳያ ነበር ይላሉ::
መምህሩ “በሕወሓት ጉዳይ መዘናጋት አስፈላጊ አልይደለም፣ አሁንም ፈፅሞ መዘናጋት ተገቢ አያስፈልግም” ይላሉ። የውይይት ጊዜን እንደ ጦር መዘጋጃ፣ የትግራይን ሕዝብ መራብ እንደ ፖለቲካ መነገጃ እና እንደ ዲፕሎማሲ ማሸነፊያ ይጠቀምበታል።
አቶ በጸሎት ሕወሓት በጦርነቱ ከገፋ አቁስሎ ሳይሆን ሕልውናውን አጥፍቶ ለትግራይ ሕዝብም ሆነ ለመላው ኢትዮጵያ እረፍት እና ሰላምን መስጠት የችግሩ ቁልፍ መፍትሄ አድርገው ያቀርቡታል::
የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ኤታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያ ሚዲያ ሰርቢስ ለተባለ በይነ መረብ በሰጡት ቃለመጠይቅ “ሕወሓት ሁሌ አንደኛ እና የመጀመሪያ መሆንንን ብቻ የሚመርጥ ባለበት የቆመ ቡድን ነው” ብለውታል:: አሁን በአዲስ የከፈተው የውጊያ ስልትም በ17 እና 18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የቀረ በሰው ኀይል ማጥለቅለቅ እና የመቆጣጠር ስልት ሲሆን ይህም ሕወሓት ለራሱ ትውልድ ያለማሰቡ ማሳያ ነው ብለውታል:: ነሃሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም “አንቶኖቭ 26” የተባለ የጦር አውሮፕላን ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ በሁመራ አድርጎ ወደ መቀሌ ሲሄድ በኢትዮጵያ አየር ኀይል ተመቶ ወድቋል:: አውሮፕላኑ በሱዳን የአየር ክልል አልፎ የመጣ በመሆኑ ሱዳን ለምን ይሄን እንደፈቀደች ንግግር ይደረጋልም ብለዋል::
የዓለም ምግብ ፕሮግራም ድርጅትም 570 ሺ ሊትር ነዳጅ በመቀሌ ሐምሌ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በሕወሓት መዘረፉን ይፋ አድርጎ፣ በሕወሓት ድርጊት ማዘኑን ገልጿል:: የአፍሪካ ሕብረትም ሆነ የአውሮፓ ሕብረት አሜሪካን ጨምሮ ሕወሓት ዳግም በጀመረው ጦርነት አዝነው አስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት እና የሰላም አማራጮች እንዲጀመር ጠይቀዋል::

(የሺሃሳብ አበራ)
በኲር ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ዕትም
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ
በhttp://www.amharaweb.com/Bekur ላይ ማግኘት ይችላሉ።