Get Mystery Box with random crypto!

የሀገር ሉዓላዊነትን እና ህልውናን የማስጠበቅ ግዳጅ ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም በተኩስ አቁሞ | በኩር ጋዜጣ Bekur Newspaper

የሀገር ሉዓላዊነትን እና ህልውናን የማስጠበቅ ግዳጅ
ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም
በተኩስ አቁሞ ስምምነት ለወራት ከግጭት ርቆ የቆየዉ የሕወሓት እና የመንግሥት ግንኙነት በንግግር ወደ ሰላም አማራጭ ይሄዳል የሚል ተስፋ ነበር።
የኢትዮጵያ መንግሥትም በየትኛም ቦታ እና ጊዜ በምንም ሁኔታ ለንግግር ዝግጁ እንደሆነ አቋሙን ገልፆ ነበር። መንግሥት ያለቅድመ ሁኔታ ለመደራደር ፍላጎቱን ከመግለፁ በተጨማሪ፣ የታሰሩ የሕወሓት አባላት እና ደጋፊዎች እንዲፈቱ አድርጓል። የሰብዓዊ እርዳታዎች ተደራሽ እንዲሆኑ፣ የትግራይ ክልል 12 ቢሊየን ብር እንዲበጀትለት፣ በትግራይ ክልል ለወደሙ መሰረተ ልማቶች ግንባታ የሚውል ወደ ሦስት መቶ ሚሊየን ዶላር በዓለም ባንክ በኩል ተመድቦ እንዲሠራ ተወስኖም ነበር።
ሕወሓት ግን ወደ ውጤት የማያመጣ ቅድመ ሁኔታ አስቀመጠ። ይኸውም ወልቃይት እና ራያ መጀመሪያ ይመለስልኝ፣ ካሳ ይሰጠኝ፣ ሕዝበ ውሳኔ ይመቻችልኝ፣ ጦሬ እንደታጠቀ ይቀጥል፣ በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ጥፋት ያደረሱ ይጠየቁ፣… የሚል ቅድመ ሁኔታ አዘጋጀ። ይሄን ቅድመ ሁኔታ ይዞም የምደራደረው በአፍሪካ ህብረት አይደለም የሚል ሐሳብ አነሳ። የምሥራቅ አፍሪካ የአፍሪካ ህብረት ወኪሉን ናይጀሪያዊዉን ኦሊሴጎን ኦባሳንጆን ለመንግሥት ያደላሉ ሲል ወቀሰ። በመሆኑም ከአፍሪካ ህብረት ይልቅ አውሮፓ እና አሜሪካን፣ ከአፍሪካ ሀገራት ደግሞ ኬኒያ እና የቀድሞ ፕሬዝዳንቷን ኡሁሩ ኬኒያታን መረጠ።
እንዲህ እና እንዲህ እያለ የቀጠለው የሕወሓት እና የመንግሥት ግንኙነት ነሀሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በይፋ የተኩስ አቁሙ ስምምነት መሻሩ ታወጀ። ሕወሓት በሌሊቱ በራያ በኩል ተኩለሽ በተባለ የሰሜን ወሎ አካባቢ ሀይሉን አንቀሳቅሶ ወረራውን መጀመሩን አወጀ። ራሱ ወሮ ተኩለሽ ራያ አካባቢ ሆኖ ተወረርኩ ብሎም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሌባ አይነደረቅ እንዲሉ አስተጋባ። ሕወሓት ከሰው ማጀት ገብቶ ሌባ ገባ ብሎ ጮኸ:: የኢትዮጵያ መንግሥት በኮሙኒኬሽን አገልግሎት በኩል ሕወሓት ወረራ ስለመጀመሩ እና የተኩስ አቁሙን እንደጣሰው ይፋ አድርጓል።
ሀገር፣ ሕዝብ፣ ሕግን ለማስጠበቅ እና ታሪካዊ እንዲሁም ሞራላዊ ግዴታየን ለመወጣት ሲል አፀፋዊ እርምጃ እንደሚወስድ መንግሥት የገለፀ ሲሆን፣ ከዚያ በፊት የትግራይ ሕዝብ ሕወሓትን እንዲያወግዝ፣ ዓለምአቀፉ ማህበረሰብም የሕወሓትን ጦር ቀስቃሽነት እንዲያወግዝ፣ የኢትዮጵያ ህዝብም ሁኔታውን በአፅንኦት እንዲከታተል ጥሪ ቀርቧል።

ከጦርነቱ መራዘም ጀርባ
በጦርነቱ መራዘም እና በአጠቃላይ በጦርነቱ ድባብ ዙሪያ አስተያይታቸውን ለበኩር ጋዜጣ የሰጡት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝም እና ሕግ መምህር የሆኑት አይተነው ፈንታ እንደተናገሩት ጦርነት እንዲራዘም እና በኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት ላይ አየር እንዲገባ በማድረግ በኩል የውጭ እጆችም አሉበት። ሕወሓት ለድርድር በሩን ዘግቶ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ያቀረበውን ነዳጅ ዘርፎ ለጦርነት ተሰማርቷል። የሚገርመው ለሰብዓዊ እርዳታ የሚቀርበውን ምግብ እና ነዳጅም ለጦርነት በመጠቀም ፣ ለትግራይ ሕዝብ የረሀብን እና ስቃይን ዕድሜ አራዝሞበታል።
መምህር አይተነው “ሕወሓት የታሪካዊ ጠላቶችን እሳቤ ተሸክሞ ሀገረ መንግሥቱን አዳክሞ፣ ራሱን አውራ ማድረግን አልሟል።” የሚል አመክንዮ ያነሳሉ:: ለዚህ ማሳያ ደግሞ የውጭ ሚዲያዎች ፕሮፖጋንዳ እና የኢትዮጵያን አየር ክልል ጥሶ የገባው አውሮፕላን ነው። ይህ አንቶኖቭ የተባለ የጦር አውሮፕላን ነሐሴ 17 ቀን ከሌሊቱ 4፡00 በሁመራ በኩል ወደ መቀሌ ሲሄድ በኢትዮጵያ አየር ኃይል ተመቶ ወድቋል።
በሌላ በኩል ጦርነቱ ከተጀመረበት ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ሕወሓት የጦርነቱ እቅድ መሪ መሆኑ ጦርነቱን አራዝሞታል ይላሉ መምህር አይተነው። ይህንንም በማሳያ ሲያቀርቡ ሕወሓት ትንኮሳ ይከፍታል፣ መንግሥት መከላከል ያደርጋል። ሕወሓት በአማራ በኩል ዘመቻ ይከፍታል፣ መንግሥትም በአማራ በኩል ለአጻፋ ይሰማራል። ሕወሓት ውጊያ ያቆማል። መንግሥትም አብሮ ያቆማል። ከዚህ አንፃር የጦርነቱ ዕቅድ የሚመራው በሕወሓት ሆኗል፤ መንግሥት መከላከልን መሰረት ያደረገ ውጊያን ይከተላል። ይህ በመሆኑ በውጊያው ሕወሓት የበለጠ ሕዝቡን እያነቃነቀ ወደ ጦርነት እንዲማግድ፣ ጊዜም እንዲገዛ፣ እስከመጨረሻው የሚዘልቅ የማጥቃት እርምጃ እንዳይወሰድበት አድርጎታል።
ለዚህ አብነት ለማንሳት ያህል ባለፈው ታህሳስ 2014 ዓ.ም የመጀመሪያዉ ምዕራፍ ዘመቻ የተጠናቀቀው በአፋርም፣ በአማራም የተወሰኑ ግዛቶች በሕወሓት እንደተያዙ ነበር። መንግሥት ለሠላም ብየ ነው በሚል መከላከያ ወደ ትግራይ ክልል አይገባም ብሎ አወጀ። ሕወሓት በአንፃሩ የተኩስ አቁሙን ተጠቅሞ ለሰባዊ እርዳታ የሚገባውን ሁሉ አሟጦ የራሱን ታጣቂ ለማደራጀት በማዋል አሁንም ወደተለመደ የጥፋት ስምሪቱ ዙሯል። መምህር አይተነው እንዳብራሩት ጦርነቱ ሶስት ምዕራፎችን ይዟል። የመጀመሪያው ምዕራፍ ከጥቅምት 24 እስከ ሕዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም መቀሌ መያዝ እና ሕወሓት ከመንግሥትነት ወደ ጫካ ሽፍታነት የተቀየረበት ሲሆን፣ ሁለተኛዉ ምዕራፍ ደግሞ መንግሥት ከትግራይ ክልል የጦር ሀይሉን ያስወጣበትና ሕወሓት በጫካ ተደራጅቶ ዳግም ወደ መቀሌ የገባበት ከሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 2014 ዓ.ም ያለው የጦርነት ምዕራፍ ነው። በዚህ ሂደት ሕወሓት ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች በመስፋፋት ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት አድርሶ ተመልሷል። በአንደኛዉ እና በሁለተኛዉ ምዕራፍ መካከል የስምንት ወር አንፃራዊ ጦርነት የቆመበት ጊዜ ነበር። ይሁን እንጂ በዚህ ጊዜ ሕወሓት ወጣቱን እያደራጀ፣ በጫካ ታጣቂ ሲመለምል፣ በአንፃሩ በመንግሥት በኩል ሕወሓት ተኗል፣ ዱቄት ሆኗል በሚል አንፃራዊ መዘናጋት ነበር ማለት ይቻላል።
እንደመምህር ዓይተነዉ ገላፃ በወቅቱ በትግራይ ክልልም የፖለቲካ ሥራ በመሥራት ሕዝቡን ከፌዴራል መንግሥት ጋር እንዲናበብ፣ በትግራይ ክልል ተቋማት ወደ አገልግሎት ተመልሰው ከሕወሓት ውጭ እንዲሆኑ፣ ትጥቅ በፌዴራል መንግሥት ቁጥጥር ሥር እንዲሆን ወዘተ ባለመሠራቱ ሕወሓት ወጣቱን እንዲሰበስብ እና የድጋፍ መሠረቱ እንዳይሟሽሽ፣ በሌላ መልኩ ደግሞ መከላከያ ማህበረ መሰረቱ በትግራይ ክልል እንዲላላ አድርጓል።
ይህም ከሰኔ መጨረሻ ጀምሮ ሕወሓት ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች እንዲስፋፋ ዕድል ከፍቶለታል።
ሕዝባዊ አንድነቱ መጎልበቱ፣ በፍጥነት የፀጥታ ኃይል በማሰልጠን በቂ ኃይል መፍጠር መቻሉ፣ ሕወሓት የፖለቲካ ቅቡልነት በማጣቱ እና መከላከያ የቴክኖሎጂ ብልጫ በመውሰዱ ሕወሓት ሰሜን ሸዋ ደብረሲና አካባቢ ቢደርስም ተመቶ ተመልሷል። ከደብረሲና ተመትቶ የተመለሰው ሕወሓት አሁንም በድጋሜ ከነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ይፋዊ ጦርነት ጀምሯል። መንግሥትም አጸፋዊ ምላሽ እየሰጠ ነው።
የሕወሓትን ጉዳይ በዘላቂነት እልባት ለመስጠት በራስ እቅድ መመራት እና የፀጥታ ኃይልን ከማጠናከር እኩል የጎለበተ የፖለቲካ እሳቤ እና አሠራር ያስፈልጋል ይላሉ መምህር አይተነው። መምህሩ አክለው እንደተናገሩትም የተሻለ እና ተቀባይነት ያለው ፖለቲካ በጦርነት ለማሸነፍም ሆነ በዲፕሎማሲዉ ለመርታት የተሻለ ነው ፣ ሕወሓትን ለማሸነፍ ከሕወሓታዊ ተቋማዊ ውቅር እና ሥርዓት መውጣት አስፈላጊ ስለመሆኑ ያሰምሩበታል። ይህ ሲሆን ሕወሓት የጨዋታ ሜዳው ስለሚቀየርበት አጥቂም ሆነ ተከላከይ ለመሆን ልምድ ያንሰዋል:: በራሱ የፖለቲካ እሳቤ፣ ተቋም እና ሥርዓት እየተመሩ ሕወሓትን ወደ